ከ“ፎርጅድ” ፖለቲከኞች፣ባለሥልጣናት፣ ፓርቲዎች፣ … ይጠብቀን!

ሰሞኑን ፖሊስ በቁጥጥር ሥር የዋለውን የፎርጅድ “ስፔሻሊስት” ጉድ ሰምታችሁልኛል? የመቶ ምናምን መስሪያ ቤቶችን ማህተም፣ ቲተር፣ ወዘተ… በመቅረፅ ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ (ሳይማሩ ድግሪ እኮ ነው!)፣ መንጃ ፈቃድ፣ የጋብቻ ሰርተፊኬት፤ ውክልና፣ ሊብሬና ሌሎች ሰነዶችን “ሲያመርት” መክረሙን የሰማሁት ከኢቴቪ የፖሊስ ፕሮግራም ነው፡፡ (ፎርጅድ በፎርጅድ ሆነናላ!) ይሄኛውን የፎርጅድ “ስፔሻሊስት” ከቀድሞዎቹ ልዩ የሚያደርገው ምን መሰላችሁ? ያልደፈረው የመንግስት መስሪያ ቤትና የግል ተቋማት የለም፡፡ (አይዞህ ያለው ማነው?) የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ የፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የግል ክሊኒኮች፣ የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲዎች፣ ወዘተ (የማን ቀረ ታዲያ!) ማህተሞችን … ፎርጅድ እየሰራ የተለያዩ ማስረጃዎችን ያቀርባል ወይም ይቸበችባል፡፡ (ፎርጅድ ፈላጊው “በሽ” ነው ማለት እኮ ነው!)
የሚገርማችሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማህተምና ቲተር እንኳን አልቀረም እኮ፡፡ የእነ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ቲተርና የኦነግን (አደጋ አለው!) ማህተምም ሲያዘጋጅ እንደነበር ተገልጿል – የፎርጅዱ ስፔሻሊስት፡፡ እኔ የምለው ግን … በ“ፎርጅድ” ሙያ የሚያሰለጥን “ስውር ተቋም” አለ እንዴ? (ከሽብርተኝነት አይለይም እኮ!?) እዚህ አገር ታሪካዊቷን ጦቢያ “ፎርጅድ” የማድረግ አሻጥር (Sabotage) ተጠንስሷል ማለት ነው?
የፎርጅዱ ስፔሻሊስት ሲገርመኝ ሰሞኑን ደግሞ በዚያው የፖሊስ ፕሮግራም ላይ የመኪና ስርቆት የፈፀመች የአዲስ አበባ ኮረዳ ተመለከትኩና በግርምት ተሞላሁ፡፡ እንዴ… ማንን እንመን ታዲያ? (በፎርጅድ ኮረዶችም ተከበናል ማለት እኮ ነው!)
እኔ የምላችሁ … ይሄ የሌብነት ጉዳይ “ፕሮፌሽናል ቢዝነስ” መሰለ እኮ! (የሌቦች ማሰልጠኛ ተቋም ተከፈተ እንዴ?) በዚሁ ሰሞን 20 የሚደርሱ ከተለያዩ ሙያዎች የተውጣጡ ግለሰቦች በፎርጅድ ሰነዶች እየተጠቀሙ፣ የአፍሪካን መዲና ሲያጭበረብሩ እንደከረሙ ፖሊስ ተናግሯል፡፡ ይታያችሁ … ከመኪና አከራዮች ውሃ የመሰለች መኪና ይከራዩና ፎርጅድ ውክልና አሰርተው
ጆሮዋን ይሏታል፡፡ የድግስ ወንበሮችና ድስቶች እንዲሁም የግንባታ ማሽኖች እየተከራዩም  ቸብችበዋል፡፡ (8ኛው ሺ ገባ እንዴ?) የእነዚህ “ቁጭ በሉዎች” ሰለባ የሆነች አንዲት እመቤት ለፖሊስ ስትናገር፤ ሌቦቹ “ያሪስ” መኪና ይዘው ወደ ቢሮዋ እንደመጡ ገልፃለች፡፡ (ያሪሷም እኮ ፎርጅድ ናት!)
ለነገሩ የዚህ የፎርጂድ ነገር በሌቦች ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ በመንግስትም በተቃዋሚዎችም በምሁሩም በባለሙያውም … በሁሉም ዘንድ እየታየ ነው፡፡ ሰሞኑን አንዲት የስራ ባልደረባዬ መታወቂያዋን ለማሳደስ ወደ ቀበሌ ጐራ ብሎ የገጠማትን አጫወተችኝ፡፡ የቀበሌው ሠራተኞች ወደው ይሁን ተገደው (እነሱም አያውቁት!) የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ምስልና “የመለስን ራዕይ እናስፈፅማለን” የሚል መፈክር የተፃፈበት ቲ-ሸርት ለብሰው ተደርድረዋል-ቢሮአቸው ውስጥ፡፡ ችግሩ ግን ምን መሰላችሁ? ቲ-ሸርቱ ለስራ ሊነሽጣቸው (Inspire ሊያደርጋቸው) አልቻለም፡፡ እንደውም መልበሳቸውንም ሳይዘነጉት አልቀሩም፡፡ ለነገሩ የራሱ ራዕይ የሌለው ሰው “የታላቁን መሪ” ራዕይ ላስፈፅም ቢል እንዴት ይሆናል? (“የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር” አሉ!) እናም ባልደረባዬን በቅጡ ሊያስተናግዷት አልቻሉም፡፡ (መታወቂያ ማደስ እኮ ነው!) እሷ ተገትራ እነሱ ወሬያቸውን እያደሱ ነበር፡፡ የማታ ማታ ዱላ ቀረሽ ሙግት ገጥማ ነው መታወቂያዋን ያደሱላት፡፡ (የፎርጅዱ “ስፔሻሊስት” በቀን ስንት የቀበሌ መታወቂያ ያመርት ይሆን?)
በነገራችሁ ላይ አንድ ፖሊስ ኦሪጂናሉንና ፎርጅዱን የቀበሌ መታወቂያ አነፃፅረው ሲናገሩ “ፎርጅድ የሚመስለው የቀበሌው ነው” ብለዋል፡፡ (የፎርጅዱን ስፔሻሊስት ወደ ህጋዊ መስመር ማምጣት አይቻልም እንዴ?) በእርግጥ መጀመሪያ ቅጣቱን መቀበል አለበት፡፡ እናላችሁ … “የመለስን ራዕይ እናስፈፅማለን” የሚል ቲሸርት ለብሰው ወሬና ሃሜት ሲያነክቱ የሚውሉ የቀበሌና የወረዳ ሰራተኞች ሁሉ “ፎርጅድ ኢህአዴጐች” ናቸው፡፡ (ኢህአዴግም ፎርጂድ አለው እንዴ?)
ይሄውላችሁ … በቲቪ መስኮት “ኪራይ ሰብሳቢ… ፀረ ሰላም ሃይላት፣ የኒዮሊበራሊዝም አቀንቃኝ” እያሉ የሚያደነቁሩን ስንቶቹ ካድሬዎችና ባለስልጣናት ሙሰኞች ሆነው እንደተያዙ በዓይናችን በብሌኑ ዓይተናል፤ሰምተናልም፡፡ አሁን እነዚህ ምን ይባላሉ? “ፎርጂድ ባለሥልጣናት!”  (“made in” የት ይሆኑ?) አንዳንዴ ሳስበው የተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ፎርጅድ ሰነዶች ብቻ ሳይሆን ፎርጅድ ተቃዋሚዎችን የሚሰሩም ሳይኖሩ አይቀሩም፡፡ ጊዜ ፊቱን ያዞረባቸው ቀን ግን ቅሌት ቀለባቸው ይሆናል፡፡ (“የህዝብ ነኝ” እያሉ ህዝብን ማታለል አደጋ አለው!)
በየጊዜው የአገሪቱ የትምህርት ጥራት “ወድቋል” ሲባል እንሰማለን አይደል?! አንድም ቀን ግን ተጠያቂው “እገሌ ነው” ብለን ደፍረን አናውቅም (እኛም ራሳችን ፎርጅድ ሳንሆን አንቀርም!) እርግጥ ነው ኢህአዴግ መራሹን መንግስት የሚወነጅሉ ወገኖች አሉ፡፡ ይሄ ግን “ክሊሼ” ነው – የተሰለቸ፤ የታከተ ሰበብ! ነገርዬውን ጠልቃችሁ ስትመረምሩ ግን ዋንኞቹ ተጠያቂዎች “ፎርጅድ መምህራን” እንደሆኑ ትገነዘባላችሁ፡፡ እንዴ … ሴት ተማሪዎችን “እራት ልጋብዝሽና ስለ ግሬድሽ እንመካከር”፣ “250 ብር አምጣና ማርክ ልጨምርልህ” የሚሉ መምህራኖች እኮ በርክተዋል፡፡ እናም የትምህርት ጥራት እንጦሮጦስ የወረደው በእነዚህም “ፎርጅድ የቀለም ሰዎች” ምክንያት ነው፡፡ (መንግስትም ግን ከተጠያቂነት አያመልጥም-ጠያቂ ካለ!) የሰው ፈጠራ ወይም የጥበብ ሥራ አሊያም ሃሳብ፣ ወዘተ … መንትፈው የራሳቸው በማስመሰል እነሆ በረከት የሚሉን “ከያኒያን”ም እኮ “ፎርጂድ አርቲስቶች” ናቸው-የጦቢያ የጥበብ ቆሌ የተጣላቻቸው!
እንግዲህ ፎርጅድ ያልገባበት የህይወት ዘርፍ የለም፡፡ ለምሳሌ እዚህቹ መዲናችን ላይ የፍቅር ፎርጅድ የሚሰሩ እኮ በሽበሽ ናቸው – ከወንዱም ከሴቱም፡፡ መጀመርያ ላይ “እመቤቴ፣ ንግስቴ፤ ማሬ ወለላዬ …” እያለ የፍቅረኛውን እግር ለማጠብ የሚዳዳው የጦቢያ ወንድ፤ አግብቶ “ንብረቱ” ካደረጋት በኋላ ግን ውጭ ውጭውን ያያል፤ ኮረዳ ያማርጣል፡፡ ይሄንን እኔ “ፎርጅድ ባል” ብየዋለሁ፡፡ “ፎርጅድ ሚስቶችም” “በሽ” ናቸው!! (ዘመኑ እኮ ነው!)
ቁጥራቸው ባይበዛም መታወቂያቸው ወይም ፓስፖርታቸው ላይ “ፎርጅድ ኢትዮጵያዊ” በሚል መገለፅ ያለባቸው አንዳንድ በ “ሃሰት” የተሰሩ ዜጐችም አሉ – እዚህችው ጦቢያችን ምድር ላይ፡፡ ባለፈው ጊዜ የአገልግሎት ቀኑ (expiration date) ያለፈበት የታሸገ ምግብ ከውጭ አስመጥተው በሱፐርማርኬት ስለሚሸጡ ስግብግቦች አልሰማችሁም? እስቲ አስቡት … የተበላሹ የህፃናት ምግብና ወተት ለወገን እየሸጡ ትርፍ ማጋበስ … ምን ይባላል? እውነቴን ነው … እነዚህ ከሽብርተኞች በምንም አይለዩም፡፡ እንዲህ ዓይነቶቹን ህሊናቸውን ለገንዘብ የሸጡ ግለሰቦች “ሆዳም” ወይም “ስግብግብ”፤ በሚል ለመግለፅ መሞከር ዝም ብሎ ቃላት ማባከን ነው፡፡ ትክክለኛው መጠሪያቸው “ፎርጅድ ኢትዮጵያውያን” ነው-ተመሳስለው የተሰሩ! (“ሃሰተኛ” ኢትዮጵያውያን እንደማለት!) በዜጐቻቸው ሰቆቃ የከበሩ ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎችም እንዲሁ ከዚህ የተሻለ ስም ሊሰጣቸው አይችልም፡፡ እነሱም “ፎርጅድ ኢትዮጵያውያን” ናቸው (እንደ ፎርጅድ ብር ቁጠሯቸው!) ጥፋት እንጂ ልማት የላቸውም፡፡
እንዴ … ሰሞኑን በመከራና በችግር ተጠብሰው ከሳኡዲ እየተመለሱ ያሉት ዜጐች ለዚህ ጦስ የተዳረጉት እኮ በእነሱ ነው፡፡ እህቶቹን ሲኦል እየወረወረ በሚያጋብሰው ገንዘብ እንቅልፉን ለጥጦ የሚያድር ሰው ኢትዮጵያዊ ሊባል አይችልም … “ፎርጅድ ኢትዮጵያዊ” እንጂ!

addis admas

posted by Aseged Tamene

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

5 Responses to ከ“ፎርጅድ” ፖለቲከኞች፣ባለሥልጣናት፣ ፓርቲዎች፣ … ይጠብቀን!

  1. Pingback: https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/12/01/4553/ | Mesfinku Melachew

  2. Grmi says:

    ETHIOPIA IS THE FAILD NATION WHY? B/C 90 MILOON PEOPLE LIVE IN POVERTY LEADRSHIPE LIVE COPTTE 1000 OF 100%

    Like

  3. በለው! says:

    <<>>>
    **ነሐሴ ፲፭ ቀን ፲፱፻፹፯ በመፈቃቀድና በነፃ ፍላጎት በአንድ የፖለቲካ ጥላ ሥር ተሰባስበን ኢትዮጵያ የምትባል(ፎርጅድ) ሀገር ላይ ለመኖር ተስመምተናል ይላል። የህወአት (ማኒፌስቶ) ህገመንግሰት ከዚያ በኋላማ ብሔር ብሔረሰብ ለባሕላዊ ጭፈራና ለባሕላዊ ለቅሶ አለገደብ ሆነ መድብለ ፓርቲ ቀርቶ ደብል ፓርቲ (አውራ ፓርቲ) ሆኖ የተነሳውን ሁሉ እየቀናነሰ በላው!።
    “የተቸፈረለት መሬት ላራሹ” “መሬት ለኢህዴግ መራሹ” ሆነ እነኳንም ልትኖርበት ልትቀበርበትም በፍቃድ ሆነ፤ ጭሰኛው ጨሰ!
    **”በእኛ ያመናችሁና የተፈጠራችሁ ሁሉ ብሉና አብሉ ተባሉና “በምረቃ ተጀመረ….በ“ፎርጅድ” ሙያ የሚያሰለጥን “ስውር ተቋም” እራሱ ህወአትሻቢያ ሆነ። (ከሽብርተኝነትም ፎርጅድ እራሱ እያፈነዳና እየገደለ እያሰረ የሚጮህና የሚያጯጩህ ሆነ!)ከህወአት ሌላ ማንም የለም አይኖርም እዚህ አገር ታሪካዊቷን ጦቢያ “ፎርጅድ” የማድረግ አሻጥር (Sabotage) ተጠንስሷል ማለት ይህ ነው።

    ***የትውልዱን አመለካካት ህወአት ለመቀየርና ለማናወጥ ሲል ቀድሞ ደርግ ያሰረፀውን የፅንፈኝነት አመለካካት(አሸባሪዎች! ቀኝ መንገደኞች! ገንጣዮች! ድልድይ አፍራሾች!) የሚለውን “በልማታዊ አብዮታዊ የዶማክራሰያዊ መንግስት” በሚል ሙሉ ፍቃድ፤ አይናችሁን ጨፍኑ፣ አፋችሁንም በኳስ ጨዋታና በወሬ ሥራ ክፈቱ ፣ በጫትና በአደንዛዥ ዕጽ፣ ተዝናኑ አለ።የፎርጂድ ነገር በሌቦች ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ በመንግስትም በተቃዋሚዎችም በምሁሩም በባለሙያውም …በፎርጅድ ኮረዶችም ተከበናል…የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ምስልና “የመለስን ራዕይ እናስፈፅማለን” የሚል መፈክር የተፃፈበት ቲ-ሸርት ለብሰው ወሬና ሃሜት ሲያነክቱ የሚውሉ የቀበሌና የወረዳ ሰራተኞች፣ አርቲስቶች፣የመንገድ ላይ ተቀጣሪዎች፣ ሁሉ “ፎርጅድ ኢህአዴጐች” ናቸው፡፡ (ኢህአዴግም ፎርጂድ አለው እንዴ?) እራሳቸው መለስ እንዳሉት “ይህ አጭበርባሪ ሌባ ነው!።አራት ነጥብ። እደግመዋለሁ ኢህአዴግ አደለም አጭበርባሪ ሌባ ነው” ብለው ነበር። “ለመሌ ምን ደላት ያም አፈር ያም ድንጋይ ጫነባት በስምና በራዕዩ በፋውንዴሽኑ በጫማና በማበጠሪያው በፎቶው አድርባይ ከበረበት።መብራት ውሃ የለም!እንቁላል ዕንቁ ሆነ! የሻማና ጧፍ ኅይል ተቀጣጠለ… ወይ ጥጋብ!
    ይሄውላችሁ … በቲቪ መስኮት “ኪራይ ሰብሳቢ… ፀረ-ሰላም ኀይላት፣ የኒዮሊበራሊዝም አቀንቃኝ” እያሉ የሚያደነቁሩን ስንቶቹ ካድሬዎችና ባለስልጣናት ሙሰኞች ሆነው እንደተያዙ በዓይናችን በብሌኑ ዓይተናል፤ሰምተናልም፡፡ አሁን እነዚህ ምን ይባላሉ? “ፎርጂድ ባለሥልጣናት!” (“made in” የት ይሆኑ?) አንዳንዴ ሳስበው የተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ፎርጅድ ሰነዶች ብቻ ሳይሆን ፎርጅድ ተቃዋሚዎችን የሚሰሩም ሳይኖሩ አይቀሩም፡፡(አጋር ፓርቲ! )ባነር እየወጠሩ፣ የሚወጠሩ፣ ኢህአዴግ ጥላ ከለላ የሆናቸው እነሱም ከእሱ በፊት ልሙት ያሉ፣ አድርባይ ፎርጅድ ምሁራን፣ ብሄርተኞች፣ ተረስተውና ማንነታቸው ተዘንግቶ የነበር በእርሱ ሰው ሆኑ ፎርጅድ ብሄርተኞችም ከህወአት በላይ ታጋይ ሆነዋል። አቤት የተጋለጡ ዕለት ከደርግ የኢሰፓ አባልና ካድሬ በበለጠ በሀገር ክህደት (“የህዝብ ነኝ” እያሉ ህዝብን ማታለል አደጋ አለው!)

    **”ኢህአዴግ መራሹን መንግስት” በኢኮኖሚው፣ በንግድ፣ በሥልጣን፡በገንዘብ ምንጩ ኢንቨስተርና በነፍሱ ጠባቂው መከላከያ እጁን ያልጨመረ ሁሉ መልካም ወዳጁ ነው። ትምህርት፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ፣ባሕል፣ ሰንደቅ፣መብት፣ጤና፣ ፍትህ፣ሉዓላዊነት የሚባል ነገር ሁሉ የቅንጦት ናቸውና አይመለከተውም። የተደረገው ውል አብሮ ለመኖር ለማኗኗር እንጂ እኩልም ለመሆን አይፈቀድም። ይህንን ተቀብለው ህወአትሻቢያን በአማካሪነትም ይሁን በብሔር ወካይነት ተቀጥረው የሚያጭበረብሩ ከሁሉም ክልል የተሳተፉ ሸቃዮች (ሹምባሾች) ህሊናቸውን ለገንዘብ የሸጡ ግለሰቦች “ሆዳም” ወይም “ስግብግብ”፤ በሚል ለመግለፅ መሞከር ዝም ብሎ ቃላት ማባከን ነው፡፡ ትክክለኛው መጠሪያቸው “ፎርጅድ ኢትዮጵያውያን” ነው። ተመሳስለው የተሰሩ! (“ሃሰተኛ” ኢትዮጵያውያን እንደማለት!) በዜጐቻቸው ሰቆቃ የከበሩ ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎችም እንዲሁ ከዚህ የተሻለ ስም ሊሰጣቸው አይችልም፡፡ እነሱም “ፎርጅድ ኢትዮጵያውያን” ናቸው (እንደ ፎርጅድ ብር ቁጠሯቸው!) ጥፋት እንጂ ልማት የላቸውም፡፡ለዚህም ነው ፲፩ከመቶ አድገን ፮.፭ የደረስነው? አሁንም በስደትና በድንቁርና የዓለም ጭራ ነን… መካከለኛ ገቢ ካላቸው ጎን መሰለፍ!? እውነትም ሀገርና ፓርቲ ክልልና ሠፈር ተጠነባበሯል ወይ እየተራቡ ማግሳት!? ፎርጅዳዊ ዕድገት!እውነተኛ እብደት በለው! ከፎርጅድ ኖሮ ያውጣን ፎርጅዶችን ኦርጅናል ልብና ዜግነት ሰብዓዊነት ይኑራቸው። “ኢትዮጵያ እጆቻን ዘርግታ ቅን አሳቢ እውነተኛ ልጆቿን ትሰበስባለች ህሴትም ታደርጋለች!!
    በቸር ይግጠመን <<<<

    Like

  4. Matthew Mekonnen says:

    Wish Ato Aseged Tamene could re-size the font of his insightful political contributions. I am more scared with the huge efforts it takes to read THE SMAL SIZE of the fonts and there-by miss the fruits of the message.

    Like

  5. Pingback: ከ“ፎርጅድ” ፖለቲከኞች፣ባለሥልጣናት፣ ፓርቲዎች፣ … ይጠብቀን! - EthioExplorer.com | EthioExplorer.com

Leave a comment