ሰበር ዜና ጋዜጠኞቹና ጦማርያኑ ጥፋተኛ አይደለንም ሲሉ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ሁሉም በተከሰሱባቸው ክሶች ጥፋተኞች አይደለንም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡

ፍ/ቤቱም የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ካደመጠ በኋላ የሚቀጥለውን ቀጠሮ ለመጋቢት 21-23 ሠጥቶ ተበትኗል፡፡ ተከሳሾቹ እጃቸው ከተያዘበት ከሚያዚያ 2006 ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከቆዩ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ክስ የተመሰረተባቸው ጥር 28 ቀን 2007 ሲሆን ተከሳሾቹ ለመጀመሪያ ጊዜ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት እድል ያገኙት ግን በዛሬው ዕለት ነው፡፡

በተያያዘ ዜና የመሀል ዳኛው የነበሩት አቶ ሸለመ በቀለ ተከሳሾቹ ይቀየሩልን ባሉት መሰረት ሐሙስ ጥር 28 ቀን 2007 ዓ.ም ራሳቸውን በፈቃደኝነት ከችሎቱ ያገለሉ ቢሆንም በዛሬው ችሎት ላይ ግን ቀርበው እንደነበር በፍርድ ቤት ጉዳዩን የተከታተሉት የተከሳሽ ጓደኞችና ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡

posted by Aseged Tamene

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

2 Responses to ሰበር ዜና ጋዜጠኞቹና ጦማርያኑ ጥፋተኛ አይደለንም ሲሉ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

  1. Pingback: ሰበር ዜና ጋዜጠኞቹና ጦማርያኑ ጥፋተኛ አይደለንም ሲሉ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ | mekbib mekonnen

  2. Pingback: ሰበር ዜና ጋዜጠኞቹና ጦማርያኑ ጥፋተኛ አይደለንም ሲሉ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ - EthioExplorer.com

Leave a comment