በወሎ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን ስብሰባ ወያኔ ድባቅ ተመታ፡

መህምራኑ ላለፉት 25አመታት የኢትዮጵያን ህዝብ ግፍ እና ጭቆናን በማንሳት በተለይም በአማራና በኦሮሞ ህዝቦች የዘር ጭፍጨፋ ወያኔ ያደረሰውን በደል በማስረጃ እየስደገፉ አብራርተዋል፡፡ የመማርያ መጽሃፉ ላይ የተገኘው የካርታ ስህተት ሆን ተብሎ የተፈጠረ መሆኑንና ወያኔ ገና ሲፀነስ አንግቦት የተነሳው አላማ ነው በማለት ተችተዋል፡፡ አያይዘውም ወያኔ በ 20 ሚሊየን ብር የኦሮሞ እና የአማራን ህዝብ ለማጣላት የተገነባው በአፄ ምኒሊክ ዘመን ተፈጽሟል የሚባለውን ኢ-ሠብአዊ ድርጊት ለማሳየት በኦሮሚያ አርሲ ዞን አኖሌ በተባለ ስፍራ የተገነባው ሃውልት፤ ወያኔ የሁለቱን ክልል ህዝቦች ለማለያየት የታሰበ ሴራ መሆኑን እና በጥናት ያልተረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ምሁራኑ በአፄ ምኒሊክ ዘመን ተፈጽሟል ከሚባለው ታሪክ ይበልጥ አፄ ዮሃንስ የወሎን ሙስሊሞች ቦሩ ሜዳ ላይ በግፍ የጨፈጨፈው እና ወደ ሃረር እንድሰደቱ ማድረጉን አፄ ምኒሊክ ፈጸመው ከተባለው ጥናት የማያስፈልገው የማይረሳ ታሪክ መሆኑን በስብሰባው ምሁራኑ ሲያንሸራሸሩት የዋሉት ጉዳይ ነው፡፡ የወልቃይት ጉዳይ፣ እራያ ፣የታሰሩ ንጹሃን ዜጎች፣ የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ ደም እኛንም ያመናል ካሁን በኋላ ምሁራኑ ዝም ብሎ የሚመለከተው ጉዳይ አይደለም በማለት ሃሳባቸውን ገልጸዋል፡፡ የድምጽ ቅጅ እንደደረሰን እንለጥፋለን፡፡ ድል ለጭቁን ህዝባችን!!!

14037783_10205234208373366_1048345346_o

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a comment