በደም እጆቹ የጨቀየን ሰው ሕወሃቶች ኦህዴድን እንዲመራ ሾሙ – ግርማ_ካሳ

አዲሱ አመት ከመግባቱ በፊት ቱባ ቱባ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት በየማታው በቴሌቭዥን እየቀረቡ “እንታደሳለን” ሲሉን እንደነበረ ይታወቃል። ተሃድሶ መሆኑ ነው መሰለኝ የኦህዴድ ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀምነበር፣ አቶ ሙክታር ከድር እና ወ/ሮ አስቴር ማሞ፣ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል። ያው በሕዝብ የተመረጡ ናቸው ስለሚባል ፣ ፓርቲው አባረረ ማለት አስቸጋሪ ስለሆነ በፍቃዳቸው ራሳቸው ለቀቁ በሚል ነው ዜናው የቀረበው።

አቶ ሙክታርና ወ/ሮ አስቴር መነሳታቸው በምንም መስፈርትና ሚዛን የሚለውጠው ነገር አይኖርም። አንድ አስክሬን ከሆስፒታል ወጥቶ ወደ መቃብር ቢሄድ ፣ አስክሬንነቱን አይለውጠው። የሞቱ፣በራሳቸው ፍቃድ የማይንቀሳቀሱ ፖለቲከኞችን ከአራት ኪሎ አካባቢ አንስቶ ምናልባት አምባሳደር አድርጎ ወደ ዉጭ አገር መላክም እንደዚሁ ነው።

እነ ሙክታርን እንዲተኩ የተደረጉ ሰዎችን ስም ሳነበ በጣም አሳቀኝ። እነ ገበየሁ ወርቅነህን ነው የሾሙት። እግዚአብሄር ያሳያችሁ ገበየሁ ወርቅነህ የፌዴራሊስ ፖሊስ አዛዥ ሆኖ የአዲስ አበባን ወጣት ያስጨረሰ ለፍርድ መቅረብ ያለበት ወንጀለኛ ሰው። ከዚያም ምንም የኢንጂነሪንግ እውቅት ሳይኖረው፣ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሆኖ እንዲሰራ ተደርጓል። በርሱ አመራር በ2007 ይጠናቀቃል የተባለው በአምስት ኮሪዶር ሊገነባ የነበረው ወደ 2300 ኪሊሜተር የሚወስደው የባቡር ግንባታ ይኸው ስድስት አመት አለፈው አንድ አራተኛው እንኳን አልተጠናቀቀም። ከአዲስ አበባ መለስተኛ የባቢር ግንባት ዉጭ አንዱም ገና አገልግሎት አልጀመረም።

እንግዲህ እንዲህ አይነት በሕዝብ ደም እጆቹ የጨቀየን፣ ከፍተኛ የሥራ ጥራት የሌለውን፣ ያልተማራ፣ የሞያ ብቃት የሌልውን ደደብ ሰው ነው ሕወሃቶች ሃላፊ አድርገው እንደገና የሾሙት።

እንግዲህ የሕወሃት የ “እንታደሳለን” ቱልቱላ፣ ይኸው ብዙ ርቀን ሳንሄድ ከእሳት ወደ ረመጥ መሄድ እንደሆነ እያየነው ነው። እዚያው እርስ በርስ እየተገለባበጡ ፣ ከሚኒስቴር ወደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት፣ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤት ወደ ጠቅላይ ሚኒስተር አማካሪነት..እየተገለባበጡ “አመራር ቀየርን” እያሉ ሊቀልዱብን ይሞክራሉ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነርሱ ድራማ ጊዜና ቦታ አይኖረውም። እዚያው እርስ በርሳቸው ይቀፋፈሉ። ሕዝብ የሚፈለገውን ነገር ያውቃል። ጥገናዊ ለዉጥ ሳይሆን መሰረታዊን ለዉጥን ይሻል። የሕሊና እስረኞች በሙሉ በአስቸኳይ መፈታት አለባቸው። አጋዚ ከጎጃ፣ ጎንደር፣ ወለጋ፣ ሃረረጌ ካሉ ቦታዎች ለቆ መውጣት አለበት። ብሄራዊ እርቅ መደረግ አለበት። እንደ ምርጫ ቦርድ ያሉ ተቋማት እንደገና ተዋቅረው አዲስ ምርጫ መደረግ አለበት። እንደ ሳሞራ የነሱ፣ ጌታቸው አሰፋ ያሉ መባረር አለባቸው። እንደ አባይ ጸሃዬ ያሉ አራት ኪሎ ቤተ መንግስት አካባቢ ድራሻቸው መታየት የለበትም።

አንዳንዶች ሼም የሚባል ነገር የላቸውም። አይኖራቸውን በጨው አጥበው፣ “ሕወሃት የለበትም ራሳቸው ኦሮሞዎች ናቸው የብሄር ብሄረሰብ መብታቸውን ተጠቅመው እነ ወርቅነህን የሾሙት…”ማለትም ይዳዳቸዋል።

ያለውን ሁኔታ የሚከተለው ፎቶ ቅልብጭ አድርጎ ይገልጸዋል።

(በነገርችን ላይ ሕወሃቶች፣ ብአዴኖችም እየተሰባሰቡ ነው። እነ ስብሀት ነጋ አባይ ወልዱን ሊያነሱት ይችላሉ ነው የሚባለው። በዚያም የሚኖረው ለዉጥ እንደ ኦህዴዱ ቁም ነገር የሚኖረው አይደለም የሚሆነው። በብአዴን ዉስጥ ግን ያለው ሁኔታ ትኩርት ሊሰጠው የሚገባ ነው።እነ ስብሃት ነጋ ከምንም በላይ ገዱ አንዳርጋቸውን ለማንሳት በጣም ፍላጎት አላቸውም። ግን አቅም ያላቸው አይመስልም። በብአዴን ስብሰባ ገዱ ከሃላፊነቱ ሳይነሳ ከቆየ፣ እነ ገዱን የበለጠ የሚያጠናክር ነው የሚሆነው። ገዱ ከተገፋ ግን ፣ ብአዴንም እንደነ ኦህዴድ ኢረለቨንት ይሆናል። ሁሉንም በቅርብ የምናየው ይሆናል)

 
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: