የተወዳጁ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ፣ “ኢትዮጽያ” የተሰኘው አዲስ የሙዚቃ ሥራ ያልተነገሩ፣ ግን መታወቅ ያለባቸው እውነታወች።

የቴዲ አፍሮ 5ኛ አልበም እነሆ ለህዝብ ሊደርስ የቀናት ጊዜያት ቀርተውታል።ቴዲ ከምንጊዜውም በላይ ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ደጋግሞ ያነሳል፣ ሕዝቦቿ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በአንድነት ለዳር ድንበሯና ለሉዐላዊነቷ የከፈሉትን ከፍተኛ መስዋዕትነትና የአርበኝነት ውሏቸውን ፣ የቋንቋና የባህል ውበቷን፣ የሃይማኖቶችና የትውፊቶች ባለፀጋነቷን ፣ .. ጥንታዊነቷንና የሰው ልጅ መገኛ ቀደምትቷን በልዩ ዜማ ይመሰክርላታል ይቀኝላታል ይዘፍንተላታል ኢትዮጵያን።

በኢትዮጵያ አልበም ውስጥ የተካቱት ዘፈኖች ሁሉ። በአማርኛ ቋንቋ የተዜሙ ናቸው። የሙዚቃ ቅንብሩን ሙሉ በሙሉ የሃገራችን ታዋቂ የሙዚቃ አቀናባሪዎች የተሳተፉበት ነው። በተለይም የሙዚቃ አቀናባሪ አቤል ጳውሎስ አብላጫውን ስራ ሰርቷል። አቤል የተወዳጆቹን የጎሳዬ ተስፋዬን፣ የፀዴንያ ገ/ማርቆስንና የበርካታ ታዋቂ ድምፃውያንን ስራዎች ያቀናበረ ነው። ዝነኛው የሙዚቃ አቀናባሪ አበጋዝ ክብረወርቅም በቴዲ ኢትዮጵያ። አልበም ላይ አሻራውን ያሳረፈ ሲሆን እንዲሁም ተወዳጁ አቀናባሪ አማን ሌላው ተሳታፊ ባለሙያ ነው።

አልበሙ ለህዝብ ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቀው በትንሳኤ።ሳምንት በሚውለው በዳግሚያ ትንሳኤ (ሚያዚያ 14 /15 ቀን 2009 ዓ/ም) ነው። የቴዲ ማኔጅመንት አባላትና አልበሙን ለማከፋፈል ውል የፈፀሙት አካላት “ኢትዮጵያ” የሚለውን ዘፈን (Track) ብቻ ለትንሳኤ ለሕዝብ ለማድረስ ፍላጎት አላቸው። በዚህም መሰረት ለትንሳኤ ዋዜማ ቅዳሜ ሚያዚያ 7 ቀን 2009 ዓ/ም ለህዝብ እንደሚደርስ ይጠበቃል።

የሃገር ውስጥ የአልበም ሽያጩን በተመለከተ ከቴዲ ማኔጅመት ጋር ውል የፈፀሙት አካላት በውላቸው መሰረት በሃገር ውስጥ 3 የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ለመስራት የተስማሙትን ታሳቢ በማድረግ ለጊዜው 4 ከተሞች በዕቅድ ደረጃ ተይዘዋል። እነሱም በመዲናችን አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ደሴና ሃዋሳ ሲሆኑ ጊዜው ሲደርስ ከደሴና ከሃዋሳ አንዱ ከተማ ላይ የሙዚቃ ኮንሰርቱ ይካሄዳል።

የመጀመሪያው ኮንሰርት አዲስ አበባ ላይ በኢትዮጵያ አዲስ አመት ለማካሄድ የታሰበ ሲሆን ቀጣዩ በሳምንቱ ባህርዳር እንደሚደረግም ይጠበቃል። ቴዲ አፍሮ በዘንድሮው የማኀበረ ግሩያን ዘረ ኢትዮጵያ 25ኛ አመት ልዩ የክብር ሽልማት ተሸላሚ በመሆኑ ሽልማቱን ለመረከብ ከቤተሰቡና ከወዳጅ ጓደኞቹ ጋር በሜይ ወር መጨረሻ ወደ አሜሪካ ይሄዳል።በአሜሪካ
ቆይታውም ሲያትል ዋሺንግተን በሚካሄደው የዘንድሮው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሚያዘጋጀው ፌስቲቫል ላይና በአንዳንድ የአሜሪካ ከተሞች በጉጉት ለሚጠብቁት አድናቂዎቹ የሙዚቃ ስራዎቹን ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ አዲስ አመት ከመድረሱ አስቀድሞ ባሉትም ቅዳሜዎች በጥቂት የአውሮፓ ከተሞች አዲሱንና የማይሰለቹትን ቀደምት ስራዎቹን ለማቅረብም ዕቅድም አለ።

በመላው አለም የሚገኙ የቴዲ አድናቂዎች በጉጉት የሚጠብቁትን ይህን ታሪካዊ አልበም በተመሳሳይ ቀንና ሰዐት ለገበያ ለማቅረብ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን፤ በተለይም ከአገር ውጭ ለሚኖረው የሙዚቃ አፍቃሪ አልበሙ በአገር ውስጥ ለገበያ በሚቀርብበት በዚያው ዕለት የአልበሙ ተቋዳሽ ይሆናል ማለት ነው። እስካሁን ድረስ አልበሙን በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአውሮፓ፣ በመካከለኛው ምስራቅና በአውስትራሊያ ለማከፋፈል ፍላጎት ካለቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እየተደረገና ከተወሰኑትም ጋርም ውል የተፈፀመ ነው።

በሃገር ውስጥ የማከፋፈሉንና የማሳተሙን ድርሻ የወሰዱት አካላት የአልበሙን ማስተር ከአርቲስቱ ተቀብለው ወደ ህትመትና ማባዛት ሂደት የገቡ ሲሆኑ ፣ የህትመቱን ሃላፊነት በመውሰድ በኩልም በሃገር ውስጥ በቅርብ ጊዜ በዱከም ኢንዱስትሪ ዞን ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የድምፅና የምስል ኮምፓክት ዲስኮችንና ዲቪዲዎችን ለማተም የተቋቋመው ቆልያ ማኑፋክቸሪንግ ኩባንያ ባለአክሲዮኖች ድርሻ ይሆናል።

ቀደም ብሎ በተለቀቀው የአልበሙ ፖስተር ዙሪያ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ አስተያየቶችን ሲሰጡበት የከረሙ ሲሆን በተለይም በስዕላዊ ማስታወቂያው ላይ ጦርና ጋሻ ይዘው የሚታዩትን አርበኛ፤ የራስ ነሲቡ ዘአማኑኤል መደበኛ ያልሆነው ጦር አባል የነበሩ ተዋጊ አርበኛ ናቸው።አርበኛ ራስ ነሲቡ እ.ኤ.አ በሜይ 1936 ዓ/ም የኢትዮጵያን ልዑካንን በመምራት ወደ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ በመምጣት በሊግ ኦፍ ኔሽን ስብሰባ ላይ የተካፈሉ ሲሆን፣ ህይወታቸው ያለፈውም በዚያው አመት በጥቅምት ወር በረዷማዋ የስዊዘርላንድ ከተማ ነው።

የዚህ መረጃ ምንጭ © አቶ ጴጥሮስ አሸናፊ ነው። እኔም (ይድነቃቸው ከበደ) ይህ ጠቃሚ መረጃ ለተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ አድናቂዎችና አክባሪዎች እንዲዳረስ። ይህን አድርጊያለሁ። ለድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ካለኝ አክብሮት ብቻ ።

አዎ ! ፍቅር ያሸንፋል !!!

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: