የግብጽ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በአውቶብስ ተሳፍረው በጉዞ ላይ እንዳሉ ጭምብል ባጠለቁ ሰዎች ጥቃት ደረሰባቸው

የግብጽ ኦርቶዶክሶች ዛሬ በማለዳ 240 ኪ.ሜ ከካይሮ በስተደቡብ ወደሚገኘው ወዳ ጻድቁ አባ ሳሙኤል ገዳም በአውቶብስ ተሳፍረው በጉዞ ላይ እንዳሉ ጭምብል ባጠለቁ የወታደር ልብስ የለበሱ አስር ታጣቂዎች በተከፈተባቸው ቱኩስ አውቶብሱ ሲቃጠል 26 ክርስቲያኖች ወዲያው ሲሞቱ 25ቱ በጽኑ መቁሰላቸውን እና በአስጊ ሁኔታዎች ላይ ናቸው ሲል ቢቢሲ፣ሲኤን ኤን ዘግበውታል።እስከ አሁን ኅላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም አሸባሪዎች እንደሚሆኑም ተገምታል። ከሞቱትም መካከል ሴቶችና ህጻናት ይገኙበታል።

ውድ ክርስቲያኖች የግብጽ ቤተክርስቲያን ከመቸውም ጊዜ በላይ ትልቅ ፈተና ላይ ስትሆን የማያቌርጥ የሰማዕትነትን ዋጋ ክርስቲያኖች እየተቀበሉ ነው። በትጋት ልንጸልይ ይገባል።

 

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a comment