ቴዲ አፍሮ ወንድ ልጅ አገኘ፤ ስሙንም ሚካኤል አለው!

(EMF) ዛሬ ኤፕሪል 6 ቀን፣ 2013 ዓ.ም. ወንድ ልጅ አግኝቷል። ሴፕቴምበር 27፣ 2012 አምለሰት ሙጬን በሰርግ ያገባው ቴዲ አፍሮ የመጀመሪያ ልጁን ስም ሚካኤል ብሎታል። በፎቶው ላይ አምለሰት ሙጬ ልጇን በሰላም እንደተገላገለች በነርሷ እየተረዳች ይታያል። በሁለተኛው ፎቶ ላይ ቴዲ አፍሮ ዛሬ የተወለደ ልጁን አቅፎ ይታያል። የሚገርመው ነገር ቴዲ አፍሮ አምለሰትን ከማወቁ እና ከማግባቱ አመታት በፊት ጀምሮ ወንድ ልጅ ካገኘ ስሙን “ሚካኤል” እንደሚለው ደጋግሞ ይናገር ነበር። አሁንም እንደተመኘው ወንድ ልጅ አግኝቶ ስሙን ሚካኤል ብሎታል። በዚህ አጋጣሚ ኢ.ኤም.ኤፍ.  አምለሰትን “እንኳን ማርያም ማረችሽ! ማርያም በሽልም ታውጣሽ!” ሲል፤ ቴዲንም “እንኳን ደስ ያለህ!” እንላለን።

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a comment