ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ በዛሬው እለት ታስሯል

ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ የከ3 አመታት በላይ በጋዜጠኝነት ሲሰራ የቆየ ሲሆን የቀዳሚ ገፅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ጋዜጣዋ እስክትዘጋ ድረስ ሰርቷል፡፡

ጋዜጠኝነት በሀገራችን አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ በመሆኑ የስራ አጋሮቹ ተሰደዋል፡፡ እሱ ግን ከፍተኛ ጫና ቢፈጠርበትም፤ ምንም ቢፈጠርበትም ለሀገሩ የቻለውን ለማበርከት ስደትን አልመረጠም፤ እዚሁ ሆኖ መታገልን መርጦ ከወራቶች በፊት አንድነት ፓርቲን ተቀላቅሎ የፓርቲው የንድፈ ሀሳብ ዳንዲ መፅሄት ላይ ዋና አዘጋጅ ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡

የቅርብ ጓደኛዮ የሆነው ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ ጋር ስደውልለት አናንያ እንደታሰረ አረዳኝ በጣም አዘንኩ አናንያ በጣም ይቅርብ ጓዴ ነው፤ ገና ብዙ የሚሰራ ይቺ ሀገራችን ተለውጣ በዲሚክራሲ አብባ የሁላችንም እንድትሆን የሞቀ ሀይል ነበረው፡፡ ሁላችንም ያንተን ያህል ብንሆን ይቺ ሀራችን ዛሬውኑ ትለወጥ ነበር፡፡

ከጎንህ ብዙዎች አለን እስር አይገድበንም አንተ ብትታሰርም ሀሳብህ ግን ከኛ ጋር ነው፡፡

posted by Aseged Tamene

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ በዛሬው እለት ታስሯል

  1. Pingback: ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ በዛሬው እለት ታስሯል - EthioExplorer.com

Leave a comment