የሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ የመጀመሪያ ልጅ የሆነችው ሰመሐል መለስ ልጅ ወለደች

ሰመሐል ወለደች
የሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ የመጀመሪያ ልጅ የሆነችው ሰመሐል መለስ ልጅ በሰላም መገላገሏን ምንጮች አስታወቁ። ሰመሐል ከወለደች በኋላ እናትዋ አዜብ መስፍን « አዋረድሽኝ» በማለት ከቤት እንዳትወጣ በማድረጋቸው በአሁኑ ወቅት ሰመሐል በፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ መኖሪያ ቤት እንደምትገኝ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። ሰመሐል ማታ ማታ ሲያስለቅሳት የነበረው መፀነሷ እንደነበረና ለእናትዋም ሳትናገር መቆየትዋ ታውቋል። “ሰመሐል” በኤርትራ ውስጥ የሚበቅል ሽታ ያለው ቅጠል ሲሆን በበአል ቀናት ይህን ቅጠል ይነሰነሳል። ለማንኛውም ሰመሐል እንኳን በሰላም ተገላገልሽ። ..የአቶ መለስ የቅርብ ታማኝና ወዳጅ የሆኑት ፕ/ር እንድርያስ መኖሪያ ቤት ሳር ቤት አካባቢ ይገኛል። ከቪላው ደጃፍ አንድ ትልቅ ግራር አለ። ከስሩ አንድ ነጭ አህያ ሁሌም ታስራ ስትግጥ ትታይ ነበር። አሁን ትኑር አትኑር አላውቅም። ነጯ አህያ ከ12 አመት በላይ ነበረች። ለፕሮፌሰሩ የቅርብ ወዳጅ የነበረው እስኬ ጓደኛዬን “አህያዋ ምንድናት?” ስል ደጋግሜ ጠይቄዋለሁ። እሱም እንድርያስን ሲጠይቅ መልስ ሰጥተውት አያውቁም። ነጭ አህያ ምን ትሆን?…በነገራችን ላይ ..ማራዘሚያ ከሚወስዱት ባለስልጣናት አንዱ ፕ/ር እንድርያስ እሸቴ ናቸው።

እየሩሳሌም አርአያ

posted by Aseged Tamene

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

3 Responses to የሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ የመጀመሪያ ልጅ የሆነችው ሰመሐል መለስ ልጅ ወለደች

  1. fkremariyam says:

    asafere chata mnchGr alew

    Like

  2. በለው ! says:

    “የተከበራችሁ የብሔር ብሔረሰብ ሕዝቦች አሁን አባት አልባ የልጆች እናት መሆኔን ተረድታችሁ የፈጠራችሁን የሞተ ባለቤቴን ራዕይ ሳይበረዝ ሳይከለስ ለማስቀጠል አንድትረዱኝ አደራ እላለሁ! ለሁለተኛው የሙት ዓመት ላይ የልጅ ልጅ ከተፍ አለ!። ” የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እዲያዋጡ መጠየቃቸውን ተቃወሙ። በኢትዮጵያ በወታደራዊ አዛዦችና በተራው ሰራዊት መካከል ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ልዩነት አለ። አብዛኞቹ የመከላከያ መኮንኖች የህወሃት አባላት ሲሆኑ፣ በአዲስ አበባ እና በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች ዘመናዊ ቪላዎችንና ፎቆችን ሰርተው በወር በመቶሺዎች የሚቆጠር የኪራይ ገቢ ያገኛሉ። በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄደውን የኮንትሮባንድ ንግድ የሚያስፈጽሙት፣ በመከላከያ ስም ያለቀረጥ የሚያስገቡዋቸውን እቃዎች በርካሽ በመሸጥ ህጋዊዎቹን ነጋዴዎች እያከሰሩ ከስራ ውጭ እያደረጉዋቸው መሆኑን በርካታ ነጋዴዎች ለኢሳት ይናገራሉ።” ራዕዩ ወይ ጭቁኑ ጉሮሮ ላይ ይሰካል ወይ ወ/ሮ አዜብ ጎላ እንዳሉት ፋውንዴሽኑ በአፈንዳጅ አድር-ባይ ይሳካል!?

    “የሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ የመጀመሪያ ልጅ የሆነችው ሰመሐል መለስ ልጅ በሰላም መገላገሏን ምንጮች አስታወቁ።“ሰመሐል” በኤርትራ ውስጥ የሚበቅል ሽታ ያለው ቅጠል ሲሆን በበዓል ቀናት ይህን ቅጠል በቤት ውሰጥ ይነሰነሳል(ይጎዘጎዛል)።በኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ውስጥ ስንት ኤርትራውያን ተነስነሰዋል(ተጎዝጉዘዋል?) ለማንኛውም ሰመሐል እንኳን በሰላም ተገላገልሽ።ማርያም ታኑርሽ ራዕዩ ተረካቢም አስቀጣይም አገኘ በለው! ግን ..የአቶ መለስ የቅርብ ታማኝና ወዳጅ የብሔር ብሔረሰቦች የብሔርና ቋንቋ ተኮር ፌደራሊዝም አስተማሪ የሆኑት ፕ/ር እንድርያስ ከውስጥ እመጫት ከውጭ ነጭ አህያ እያኖረ የመኖሩ ጉዳይ አይገርምም!?

    Like

  3. Pingback: የሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ የመጀመሪያ ልጅ የሆነችው ሰመሐል መለስ ልጅ ወለደች | EthioExplorer.com

Leave a comment