የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች የፖሊስ ጽ/ቤት ላይ ጥቃት ፈፀሙ

ሀመሌ 30 ቀን 2009ዓ/ም ከምሽቱ 4:20 ሲሆን በደቡብ ጎንደር ዞን በእብናት ወረዳ የወረዳውን ፖሊስ ጽ/ቤ/ት በቦንብ ጥቃት ደረሰበት ::

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀጠናው የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች ተደጋጋሚ ጥቃት በመፈፀማቸው የወረዳው ፖሊስ አዛዥን ጨምሮ ሊሎች የፀጥታ አመራሮች እንደማዘዣ ጣቢያ የሚጠቀሙት ይህን ፖሊስ ጽ/ቤት ነው።

በመሆኑም በጥናት በተመሰረተ መልኩ በትናንትናው ምሽት ይህ ጥቃት ተፈፅማል ፣የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ዝርዝሩ እደደረሰን እንገልፃለን።

ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲሰደዱ በኮንጎ ህይወታቸው ያለፈ 19 ኢትዮጵያዊያን አስከሬን ቅዳሜ ሌሊት አዲስ አበባ መግባቱ ተነገረ

ስደተኞቹ በኬንያና በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አድርገው በዛምቢያ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ነበር ጉዞውን የጀመሩት።
ከኬንያ ሲነሱ አሳ እና ለውዝ በጫነ ኮንቴይነር ውስጥ የሞቱ 19 ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ 95 የተለያዩ አገራት ስደተኞች ለጉዞ አመቺ ባልሆነ ሁኔታ ነበር ታፍነው አስከፊውን የስደት ጉዞ የተያያዙት።
በኮንጎና ዛምቢያ ድንበር መካከል ከሉሳካ 300 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ በረሃማ አካባቢ ውጥናቸውን ሳያሳኩ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።
ከሞቱት አብዛኞቹ ወጣቶች ሲሆኑ ከነዚህም መካከል 14ቱ በሃዲያ ዞን ይኖሩ የነበሩና በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ለህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ከፍለው ነበር ጉዞውን ያደረጉት።
ከሟቾች መካካል የአንደኛው ስደተኛ አጎት አቶ ደባሱ ዋሌ እንደተናገሩት “ሟች በአገር ቤት የስምንተኛ ክፍል ተማሪ የነበረ ሲሆን በትምህርቱ ጎበዝና በደረጃውም አንደኛ የሚወጣ ነበር”።
ትምህርቱን አቋርጦ ደቡብ አፍሪካ ካለው ወንድሙ ዘንድ እሄዳለው በማለት ለጉዞ መነሳቱንና ቤተሰብ ከልክሎት እንደነበር ያስታውሳሉ።
ይሁንና ቤተሰብ ሳያውቅ በደቡብ አፍሪካ ከሚኖሩ ጓደኞቹ ጋር ተነጋግሮ ኬንያ ገብቶ “ሄጃለሁ” በማለት ለቤተሰብ ስልክ መደወሉን ይናገራሉ።

“ገና ሳይበላና ሳይጠጣ፣ በልጅነቱ ያሰበውን ቤተሰቦቹን የመርዳት ውጥን ሳያሳካ እለወጣለሁ ብሎ በለጋነቱ በረሃ ቀረ” ይላሉ አጎቱ።

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት አሽከርካሪዎችን ለዛምቢያ መንግሥት አሳልፎ እንዲሰጥ ጥያቄ መቅረቡንም አስታውቀዋል።

ስደተኞቹ ለደቡብ አፍሪካ ቅርበት ያላቸውን አገራት በህገ-ወጥ መንገድ እንደ መተላለፊያ በመጠቀማቸው ለሞትና ለእስር ይዳረጋሉ።
በቅርቡም በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ በታንዛንያና ዛምቢያ ፖሊስ ተይዘው ለወራት በእሥር ቤት የቆዩ 88 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

የአርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ታጋዬች በቆላድባ ከተማ ላይ ጥቃት ፈፀሙ ተባለ

የአርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ታጋዬች ሀምሌ 24 ቀን 2009ዓ/ም በሰሜን ጎንደር ዞን ደንቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ከምሽቱ 5:20 እስከ ለሊት 7:20 ለሁለት ሰዓት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ያደረጉ ሲሆን በከተማው በነበረው ወታደራዊ ካምፕ ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሳቸውን ተናግረዋል::

እንዲሁም በስርዓቱ አመራሮችና ስርዓቱ ህዝብን ለማሰር ፣ንብረቱን ለመዝረፍ የሚጠቀምባቸውን ተቋማት አጥቅተናል ብለዋል።

በዚህ ወረዳና ቆላድባን ጨምሮ በዙሪያው በሚገኙ ከተሞች ላይ
የአርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ታጋዬች በወያኔ ላይ ተደጓጓሚ ጥቃት የሚፈፅምበትና የስርዓቱ መዋቅርና ደህንነቶች ላይ በነሱና በንብረታቸው ጉዳት የሚፈፀምበት ቦታ በመሆኑ አካባቢው ዘመናዊ መሳሪያ በታጠቁ ወታደሮች የሚጠበቅ ነው ፣ይህም ሆኖ በቦታው የነበሩ ወታደርች ከ 1:00 በላይ መዋጋት ባለመቻላቸው ከነበሩበት ቦታ ለማፈግፈግና ለመልቀቅ ተገደዋል ከዚያም የድረሱልን ጥሪ አሰምተው ጎንደር አዞዞ ለሚገኘው የወያኔ ወታደር አቅርበው ከዚህ ቦታ በ5 ፒካፕ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ሓይል ተጭምሮ ውጊያው እስከ ለሊቱ 7:20 ድረስ ተካሂዳል የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ዝርዝሩ እንደደረሰን እንገልፃለን።

በ ህወሓት/ኢህአዴግ ውስጥ አለመረጋጋት መፈጠሩን ምንጮች ጠቆሙ

በሙስና ተጠርጥረው ታሰሩ የተባሉ ሰዎችን ተከትሎ፣ አንዳንድ አለመግባባቶች መፈጠራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተለይ እነማን መታሰር አለባቸው እነማን የለባቸውም በሚለው ጉዳይ አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር የገለጸሩት ምንጮች፣ በተለይ የታሳሪዎቹ ስም ዝርዝር ይፋ ከተደረገ በኋላ በህዝብ ዘንድ ብዙም ትኩረት አለመሳቡ ስርዓቱ የጠበቀውን ያህል ትኩረት መሳቢያ እንዳያገኝ እንዳደረገው ምንጮቹ ይገልጻሉ፡፡

እስሩ በትናንሽ የስራ ኃላፊዎች ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑ ያልጣማቸው አንዳንድ የስርዓቱ ቁንጮ ሰዎች፣ እና እስሩ ለጅማሬ ያህል በቂ ነው የሚሉ የስርዓቱ ከፍተኛ አመራሮች እርስ በእርስ እየተወዛገቡ እንደሚገኙ የገለጹት የመረጃ ምንጮች፣ በቀጣይ የሚታሰሩ ኃላፊዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ምንጮቹ ያረጋግጣሉ፡፡ በአሁን ሰዓት በስርዓቱ ውስጥ እርስ በእርስ መደማመጥ እና በሰከነ ሁኔታ መነጋጋር መጥፋቱን የጠቆሙት የመረጃ ምንጮች፣ ስርዓቱ አስራ አንደኛው ሰዓት ላይ መድረሱንም ያመላክታሉ፡፡

እንደ መረጃዎች ገለጻ፣ በተለይ የመከላከያውን እና የደህንነቱን ስልጣን የያዙት የህወሓት አመራሮች፣ ራሳቸውን ይበልጥ ለማደራጀት እየተሯሯጡ ይገኛሉ፡፡ በራሱ በህወሓት መካከል የተፈጠረ መሰነጣጠቅ እንዳለም ከመረጃዎች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ ከተባሉ ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ፣ ከአንድ ከፍተኛ የህወሓት አመራር ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሴት ወይዘሮ መኖራቸው፣ በአንደኛው የህወሓት ቡድን ዘንድ ቅሬታ መፍጠሩን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

የህወሓት መፈርከስ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያቀርባል !

በህወሓት/ኢህአዴግ ውስጥ የዓላማ ሳይሆን የጥቅም ግጭት ተፈጠረ። ” ጅብ ሲሰርቅ ይስማማል ሲካፈል ነው የሚጣላው ” እንደ ሚባለው ሰሞኑን የህወኃት/ኢህአዴግ ሰዎች በማን አለበኝነት ለ26 ዓመት እነሱ እና መሰሎቻቸው የዚችን ምስኪን አገር ሀብትና ንብረቷን በመዝረፍ እነሱ እንደሚሉት በእድገት ጎዳና ያለች አገር ሳትሆን እጅግ ኃላ ቀር ከሚባሉ አገሮች የአገር ጭራ አድርገዋት ትገኛለች።

በመሆኑም ይህ ስርዓት በከፍተኛ ደረጃ በሙስና የተዘፈቀና አገሪቱን ለከፋ ድህነት ከመዳረጉም በላይ ለዕዳ ዳርገዋት ይገኛሉ። ይህን አገራዊ ችግር የተናገሩ ሙሁራን፣የፖለቲካ ሰዎች፣የራሳቸው አባል የሆኑ ሳይቀር ተገድለዋል ፣ታስረዋል፣ከአገር በግፍ ተሰደዋል።

ከዚያም ጉዳዩ ይህ ስርዓት በስልጣን ላይ ካለ ሙስናን መከላከልም ሆነ ዘራፌዎችን በህግ ለመጠየቅ የማይቻል በመሆኑ በሁሉም መልኩ የተዘጉትን መንገዶች ማለትም የዴሞክራሲ( የፖለቲካ)፣የኢኮኖሚ፣የማህበራዊ መብቶችን ማስፈን የሚቻለው በኃይል እንጅ በሰላማዊ ወይም በልመና እንዳልሆነ ያመኑ የትጥቅ ትግልን በአማራጭነት በመያዝ በአሁኑ ሰዓት ስርዓቱን ለከፋ ችግር እንዲወድቅና በርካታዎቹን ከጎናቸው በማሰለፍ ለህዝብ አሊንታና መኩሪያ ለጠላት ደግሞ ድንጋጤና ፍርሃትን ለቆበት ይገኛል።

በሌላ በኩል የራሱ የስርዓቱ ሰዎችም ቢሆኑ ሙስናን፣ስልጣንን ያላግባብ መጠቀምን፣ በተለያዩ ፕርጀክቶች ስም የተመደበን ገንዘብ መዝረፍ ይቁም ማለትና መጠየቅ በራስ ላይ እንደመፍረድ የተቆጠረ ሆነ ፣ ከዚያም ዝርፊያውን በጋራ ተያያዙት ከዚህ ላይ ግን ግጭቶች ብቅ አሉ እሱም ቁልፍ እና በርካታ ገንዘብ የሚዘረፍባቸውን ቦታዎች እኔ ልያዝ እኔ ልያዝ በሚል፣ከዚያም ህወኃት ያለውን ጡንቻ በመጠቀም ቦታዎችን ጠቅልሎ ያዘ ከዚያም ከፍተኛ ገንዘብ የሚመደብላቸው ድርጅቶችን መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ሜቴክን መሰረቱ በዚህ ድርጅት አማካኝነት አገሪቱ እንዴት በዘራፊዎች እየተቦጠቦጠች እንደሆነ ሁላችንም እያየን ነው።

ከዚያም ህዝቦች ኧረ ባካቹህ ሙስና የስርዓቱ መገለጫ ሆነ፣ህዝብ ድህነት አጠቃው፣ ጥቂቶች እጅግ በለፀጉ ብሎ ሲጠይቅ ለተወሰነ መልስ ወይም ማስታገሻ ይሆን ዘንድ ምስኪኑን የበታች ሰራተኛ ሰብስቦ በማሰር በራሱ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ” ሙሰኞችን በቁጥጥር ስር አዋልናቸው” እያለ ይለፈልፋል ይህን የሰሙ አንድ አዛውንት አንድ የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣን በሚመሩት የህዝብ መድረክ ላይ የሚከተለውን ቃል ተናገሩ
” አንድ ሰው መንገድ ወጥቶ እየሄደ ሳለ ይመሽበትና ከእንድ ቤት አሳድሩኝ ብሎ ይገባል ሰዎችም እሽ ብለው የመሸበትን እንግዳ ተቀብለው ወደ ቤት አስገቡት በቤቱ ባል ሚስትና አንድ ልጅ ብቻ ይኖራሉ፣ ከዚያም ራት እየተበላ በጫወታ ላይ ድንገት ሚስት ያመልጣቸዋል ከዚያም ደንገጥ አሉ እና አንተ ልጅ ብለው ከእንግዳ ፊት እንዴት እንዴህ ታደርጋለህ ብለው ልጅን በኩርኩም ይመቱቷል፣ ከዚያም ትንሽ ይቆይና ባል ድንገት ያመልጣቸዋል እሳቸውም ደንገጥ በማለት አሁንም ልጃቸውን አንተ ባለጊ በማለት በኩርኩም ይመቱታል ከዚያም ጫወታው ያልቅና እንግዳው ከመቀመጫቸው ሲነሱ እሳቸውም ያመልጣቸዋል ሰውየው ደንገጥ ብለው የት አለ ያነ የፈረደበት ልጅ በሉ አምጡትና እኔም በኩርኩም ልበለው አሉ” በማለት ተረቱባቸው የናንተም የሙስናው ትግል እንዲህ ነው አሏቸው።

እንግዲህ በአገሪቱ ያለው የሙስና ሁኔታ ከህዝብ የተደበቀ እንዳልሆነና ሙሰኞች እነማን እንደሆኑ ጠንቅቆ ያውቃል ስለሆነም ይህን ህዝብ ማታለል የማይቻልበት ደረጃ ተደርሷል ህወሓት/ ኢህአዴግ በሚከተሉት ነገሮች አጣብቅኝ ውስጥ ገብቷል።
1ኛ፣ ጂቲፒ እያለ በየ አምስት ዓመት የሚያቅዳቸው እቅዶች ከወረቀት አልፈው ጠብ የሚል ነገር አላሳዩም ይባስብለው ህዝብን በማፈናቀል እና አገሪቱን ለዕዳ ከመዳረግ ያለፈ የፈየዱት አለመኖሩ
2ኛ፣ስርዓቱ ከዓመት ዓመት እየወረደና በተለይ በአሁኑ ሰዓት በነፃነት ታጋዬች በሁሉም ዘርፍ ( በትጥቅም ትግል፣በዲፕሎማሲ) መወጠሩ በስርዓቱ አገልጋዬች ላይ ለፍተኛ ስጋት በመደቀኑ እነዚህም ህዝቡ ቃል የገባንለት ነገር ባለማሳካታችን በጥያቄ እያስጨነቀን ነው የሚሉና እኛ ምንም ሀብት ሳንይዝ ሊሎች በዘረፉት የነሱ አገልጋይ ሁነን ነገ ልንጠየቅ ነው ስለዚህ ከአለንበት ከክልል ኃላፊነት ወደ ላይ አውጡን ወይም አባሳደር አድርጋቹሁ ሹሙን የሚል ጥያቄ በብዛት መምጣት ጀምራል።

በተለይ ለዛሬ መነሻ የሆነን በአገሪቱ የስኳር አቅርቦትን ይፈታሉ የተባሉ ፉብሪካዎች በልዩ መልኩ አደረጃጀትና አመራር ተመድቦላቸው የነበሩ ፉብሪካዎች የውሃ ሽታ መሆናቸውና የተበላው ገንዘብ ደግሞ የትየለሌ መሆኑ ከፍተኛ መነጋገሪያ ከሆነ ውሎ አድራል ወያኔም ለጥያቄው ቅድም አንድ አባት እዳሉት ዋናዎቹ መሪዎች እነ አባይ ፀሀዪ ተቀምጠው ታችኞችን ማሰሩ መፍቴሄ አለመሆኑ እውነታው እየተገለፀ መጥቶ በአሁኑ ሳዓት የነአባይ ፀሀዪ ቡድን እና የሌሎቹ ቡድኖች ትንቅንቅ ውስጥ ገብተዋል።

በመሆኑም ይህ የበሰበሰ ስርዓት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል በተለይ ሙስና መገለጫ የሆነበት” በሙስና የተጨማለቀ ስርዓት በሁለት ጎን ይወጠራል ይህም ሙስናን ልዋጋው ቢል ስርዓቱ ይፈርሳል፣ሙስናን ዝም ብሎ ቢመለከትም ይፈርሳል” ስለዚህ ይህ ስርዓት ፈራሽ መሆኑን አውቀን ግብዓተ መሪቱን የማፉጠን ስራ ከሚሰሩት የነፃነት ታጋዬች ጎን እድንሰለፍ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

%d bloggers like this: