የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይል በወያኔ ኃይል ላይ ጥቃት መፈፀሙን ቀጥላል ተባለ

አገር ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይል ለትንሳኤ ሬዲዮ በላከው መልእክት ግንቦት 04 ቀን 2009ዓ/ም ምሽት 2፡00 ሰዓት ላይ የህውሐት የደህንነት አባል በሆነው ወርቁ ካሳሁን በተባለው የምዕራብ አርማጭሆ አብርሀጅራ ከተማ ቀበሌ 01 ነዋሪ ላይ በወሰደው እርምጃ ግለሰቡ ወዲያውኑ መገደሉን አስታውቋል።

እርምጃው የተወሰደበት ይህ ግለሰብ ሀምሌ 05 ቀን 2008ዓ/ም በተነሳው ህዝባዊ አመፅ ንፁሃንን ያስገደለ፤ ታፍነው አድራሻቸው እንዲጠፉ ያስደረገ እና በቅርብም የአካባቢው ተወላጅ የሆኑቱን እያሳደነ በርካታ ባላሃብቶችን ያፈናቀለ የሥርዓቱ ደህንነት አባል ነበር።

ከዚህ በተጨማሪ የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ ወጣቶችን ከትውልድ አገራቸው እንዲባረሩ አድርጓል። ለአብነት ያህልም ሁነኛው አበበ ፣ አየልኝ፣ በፈቃዱ የተባሉትን መጥቀስ ይቻላል ብሏል መልእክቱ ።

እርምጃው ከመወሰዱ በፊት ይህ ሰው ከድርጊቱ እዲታቀብ በተደጋጋሚ ቢነገረውም ጭራሽ የአካባቢውን ህብረተሰብ በመናቅ እና የሎሌነት ጭካኔ እርምጃውን አጠናክሮ በመቀጠል ሲንቀሳቀስ በትናንትናው ዕለት ምሽት የማያዳግም እርምጃ እንደተወሰደበትና እንዲወገድ እንደተደረገ ተገልጿል።

በተያያዘ ዜና አርበኛ ነጋ አዲሱ የተባለ የነጻነት ታጋይ ግንቦት 04 ቀን 2009ዓ/ም ከቀኑ 11፡20 ላይ በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ ወረዳ የህወሓት የሚሊሺያ ኮማንደር የሆነውን ማሩ ነጋሽ የተባለውን እና አብረውት የነበሩ 2 ሌሎች የሚሊሽያ አባላትን በድምሩ 3 ሰዎች ገድሎ 2ቱን ካቆሰለ በኋላ የጀግንነት ተግባር ፈጽሞ መሰዋቱን ከግንባሩ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

አርበኛ ነጋ አዲሱ ለቆመለት ዓላማ አረአያነት ያለው የጀግንነት ተግባር ፈጽሞ በማለፉ አብረውት የሚንቀሳቀሱ የትግል ጓዶቹ መኩራታቸውን የገለጸው መረጃ፥ የእርሱን የጀግንነት ቀንድል በመከተል ይዞት የተነሳውን ዓላማ ከግብ ለማድረስ እሰከ መጨረሻው የደማቸው ጠብታ እንደሚታገሉ ማረጋገጣቸውንና የህዝብ ጠላት የሆነውን የህወሃት አገዛዝ ሥልጣን ዕድሜ በማሳጠር ፍትህ እኩልነትና ነጻነት የሰፈነበት ማህበረሰብ በመገንባት ዘለዓለማዊ ህይወት እንደሚያወርሱት ቃል መግባታቸውን ያትታል።

Advertisements

የሚታገሉትን የማያቁ የአማራ ነን ባዮች የከሸፈ ስልት

ለሀያ አምስት አመት ተንሰራፍቶ ኢትዮጵያን በመግዛት ላይ የሚገኘው ትግራይን ለመገንጠል አላማ አድርጎ የተነሳ ግን የሚታገለው በማጣቱ የሀገሪቱ መራሒ መንግስት በመሆን በሀገሪቱን ዜጎች የፈለገውን በማሰር፣ ኣሰቃቂ ድብደባ በመፈጸም እና በመግደል እስከወዲያኛው ትውልድ ድረስ ተከፍሎ የማያልቅ ብድር በሀገሪቱ ስም በመበደር የሕወሓት ባለስልጣናት በየግል ካዝናቸው በስበብ አስባቡ ዘርፈው አከማችተውታል።

ግፍ የመረረው ህዝባችን በእልህ እና በቁጭት መሳሪያ አንግቦ ለነጻነት የትጥቅ ትግል ከሕወሓት ወታደር ጋር በሚያደርግበት ስአት ህዝቡን በሞራል እና በገንዘብ አይዞህ እንደማለት የነጻነት ትግል በሚያካሒዱ የፖለቲካ ድርጂቶች እና መሪዎቻቸው አልፎም በንቁ የማህበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶች ላይ ያነጣጠረ መንቻካ ዘመቻ ለበርካታ ሳምንት ማህበራዊ ሚዲያውን ለመበጥበጥ የነጻነት የትግል አቅጣጫውን እንዲስት ሆን ተብሎ ደጎስ ያለ ድጎማ ከህወኃት በሚያገኙ ጥቀመኞች ጥቃት ሲሰነዘር መቆየቱ ብዙዎችን አሳዝኗል፣አበሳጭቷል።

ስለሆነም በተለይ በአማራ እና በኦሮሞ መብት ተሟጋች ነን በሚሉ ኢትዮጵያዊነት ባህልን ያቆሸሸ እና ታሪኩን ያሳደፈ ምግባር የታየ ሲሆን የአግ፯ ደጋፊ ነን የሚሉ ጥቂት ሰዎችም ለተሰነዘረባቸው አላስፈላጊ ዘመቻ ምላሽ ለመስጠት በእልህ ውስጥ በመግባት ያደረጉት ምልልስ ተገቢ አልነበረም።

ለሀገር እና ለወገን መብት ውድ ህይዎታቸውን ለመገበር በርሃ የገቡ ጄግኖቻችን ሞራል በተራ ስድብ የሚፈታ የመሰላቸው ሽባ የወያኔ ቅጥረኞች ከዚህ ስራቼው እንዲታቀቡ አስቀድመን እንመክራለን። ማንኛውም ኃይል እና ጉልበታችን ወያኔ ላይ ለማሳረፍ በአዲሱ የፈረንጆች አመት ዳር እስከዳር መያያዝ አለብን።
ድል ለነጻነት ታጋዮች

14956437_220660495029930_1633004519583544399_n

%d bloggers like this: