የፌደራል አቃቤ ህግ በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ የክስ መዝገብ ስር ባልተከሰሰ እና በሌለ ግለሰብ ላይ ምስክር አሰማ ( በጌታቸው ሺፈራው)

የፌደራል አቃቤ ህግ በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ የክስ መዝገብ ስር ባልተከሰሰ እና በሌለ ግለሰብ ላይ ምስክር አቅርቦ አሰምቷል።

ዛሬ ነሃሴ 10/2009 ዓም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በእነ ማስረሻ ሰጤ የክስ መዝገብ ላይ ምስክሮች የቀረቡ ሲሆን በአቃቤ ህግ ምስክር ዝርዝር 76ኛ ተራ ቁጥር ላይ የተጠቀሱት አቶ አለሙ በላቸው በክስ መዝገቡ ላይ ባልተከሰሰ እና በሌለ ግለሰብ ላይ እንዲመሰክሩ ተደርገዋል። አቃቤ ህግ ለማስመስከር ጭብጥ ሲያስይዝ ምስክሩ በ16ኛ ተከሳሽ አሸናፊ መለሰ ላይ ይመሰክራሉ ብሎ የነበር ቢሆንም ምስክሩ የሚያውቁትና እመሰክርበታለሁ ያሉት በክስ መዝገቡ ስር ክስ ያልቀረበበት ሌላ አሸናፊ የተባለ ግለሰብ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።

ምስክር ተከሳሽ ነው የተባለውን ግለሰብ አውቀዋለሁ ባሉት መሰረት ከተከሳሾች መካከል ለይተው እንዲያሳዩ ሲጠየቁ እንደሌለ የገለፁ ሲሆን እሳቸው የሚያውቁት አሸናፊ የተባለ ግለሰብ እግር ኳስ ሲጫወት አደጋ ስለደረሰበት በክራንች የሚንቀሳቀስ እንዲሁም አንድ አይኑ ላይ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን ገልፀዋል።

በመሆኑም በክሰ መዝገቡ ከተከሰሱት 38 ተከሳሾች መካከል ምስክሩ አውቀዋለሁ ያሉት ግለሰብ እንደሌለ ታውቋል። 31ኛ ተከሳሽ ጌታቸር እሸቴ ምስክሩ የጠቀሱትን ግለሰብ እስር ቤት ውስጥ እንደሚያውቀውና በመዝገቡ ስር እንዳልተከሰሰ በመግለፅ በሌለ ግለሰብ ላይ ምስክር በማሰማት የፍርድ ቤቱ ጊዜ እንዳይባክን አሳስቧል። በተመሳሳይ የተከሳሾች ጠበቃ በመዝገቡ በክራንች የሚንቀሳቀስና በአይኑ ላይ ጉዳት የደረሰበት ተከሳሽ ስለሌለ ፍርድ ቤቱ በሌለ ግለሰብ ላይ በማስመስከር ጊዜ ማጥፋት ስለሌለበት ምስክሩ እንደዲታለፉ ጠይቀዋል።

አቃቤ ህግ በበኩሉ ምስክሩ የጠቀሱት ግለሰብ ከሌለ የፍርድ ቤቱ ጊዜ መባከን እንደሌለበት ቢያምንም በክስ መዝገቡ ስር ሁለት አሸናፊ የሚባሉ ግለሰቦች በመኖራቸው ሁለቱ ግለሰቦች ቆመው ምስክሩ ከሁለቱ እንዲለዩ ከተደረገ በሁዋላ የተባለው ግለሰብ ከሌለ ምስክርነቱ ሊታለፍ እንደሚችል አማራጭ አቅርቧል። ይሁንና ፍርድ ቤቱ ምስክርነቱ ከተሰማ በሁዋላ ይጣራል በሚል ምስክርነቱ እንዲቀጥል ወስኗል።

የአቃቤ ህግ ምስክር አቶ አለሙ በላቸው የሚመሰክሩበት ግለሰብ ከተከሳሾቹ ጋር እንደሌለና ቢኖር ሊያውቁት ይችሉ እንደነበር ያስረዱ ሲሆን በሌለበት ከመሰከሩበት ግለሰብ ጋር ቂሊንጦ እስር ቤት ጎን ለጎን አልጋ ተሰጥቷቸው ለ9 ወር ያህል አብረው እንደኖሩ አስረድተዋል። ከአሁን ቀደም በተሰሙ ምስክሮች ላይ በመፈራረቅ መስቀለኛ ጥያቄ ሲጠይቁ የነበሩት ተከሳሾችና ጠበቆቻቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ምስክር ላይ መስቀለኛ ጥያቄ የለንም ብለዋል። በሌለበት የተመሰከረበት አሸናፊ የተባለ ግለሰብ እንዳልተከሰሰ እና ከእስር እንደተፈታ ታውቋል።

Advertisements

ምርምራ ሲደረግባቸዉ የነበሩ የመከላከያ አባላት ህይወታቸዉ አለፈ

ከሰሜን እዝና ከተለያየ ክፍለ ጦሮች የተጠለፉ እነርሱም ለጠላት መረጃ አሳልፋችሁ ሰጥታችኍል የተባሉ የመከላከያ አባላት ላለፉት ሁለት ወራት በአዘዞ ካምፕ በስዉር እስር ቤት ዉስጥ ሲቀጠቀጡ ቆይተዉ ባለፈዉ ሳምንት ማክሰኞ ወደ አዲስ አበባ ከተዘዋወሩ ወዲህ በፌደራል ፖሊስ ቅጥር ግቢ ምድር ቤት ዉስጥ በሚገኝ የመበለቻ ስፍራ ሲሰቃዩ ከነበሩት የመከላከያ አባላት መካከል ሁለት ዝቅተኛ መኮንኖች ህይወታቸዉ አልፏል።

አንድ የ10 አለቃ እና አንድ የምክትል 10 አለቃ መኮንኖች ላይ ከፍተኛ የሆነ ስቃይ እንደተፈጸመባቸዉና በዚህም የተነሳ ህይወታቸዉ ማለፉን የጠቆሙት ምንጫችን በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ 18 ወታደሮች በከፍተኛ ምርመራ ቶርች እየተደረገባቸዉ እነደሆነ ጠቅሰዋል።

ተለያዩ የህሊና እስረኞች በግፍ የታጎሩበት ማንም ሊጠይቅና ሊመለክት የማይችለዉ የፌደራል ፖልስ ድብቅ እስር ቤት ብዙዎችን እየበላ እንደሚገኝ መረጃዎች እየወጡ ነዉ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
ጉድሽ ወያኔ

የእንጀራ ልጁን አስገድዶ የደፈረ ግለሰብ በ11 አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

በምዕራብ ጐጃም ዞን ጃቢ ጠህናን ወረዳ የ15 አመቷን የእንጀራ ልጁን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ11 አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ፡፡
ተከሳሽ ታዘብ መለሰ አድራሻው ጃቢ ጠህናን ወረዳ ሽመበድ ወቄት ቀበሌ ኑዋሪ ሲሆን ነሐሴ 4 ቀን 2008 ዓ.ም የ15 አመቷን የእንጀራ ልጁን እርሻ ማሳ ላይ አስገድዶ ደፍሯል፡፡ ተከሳሹ በመድፈር ወንጀል ተከሷል፡፡

ተከሳሹ የ15 አመቷን የእንጀራ ልጁን አስገድዶ ከመድፈሩም በተጨማሪ ታዳጊዋ ካለፍላጐቷ ከመድፈሩም በተጨማሪ በማስረገዝ ወንድ ልጅ እንድትወልድ አድርጓል፡፡

የጃቢ ጠህናን ወረዳ ፍድር ቤትም ጉዳዩን በመያዝ በተከሳሹ ላይ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ጥፋተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ተከሳሹም የቀረበበትን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ማስተባበል አልቻለም ተከሳሹ የፈፀመው ወንጀል ከ10 አመት እስከ 12 አመት ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ቢሆንም ካሁን በፊት በቀበሌው ሲኖር ጥሩ ስነ-ምግባር ያለው መሆኑ፤ የቤተሰብ አስተዳደር መሆኑ፣ በፍቃደኝነት ላይ ተመሰረቶ ደም ልገሳ ስራ በመስራቱ እና አሸዋ በማውጣት ቤተሰቡን የሚያስተዳድር መሆኑ በቅጣት ማቅለያነት ተይዞለታል፡፡ 


የጃቢ ጠህናን ወረዳ ፍርድ ቤት ሐምሌ 18 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ የፈፀመው ወንጀል ከባድነቱን፣ የአፈፃፀም ሁኔታውን፣ በማመዛዘን ተከሳሹን ያስተምራል፣ ያርማል ሌሎችንም ያስተምራል ያስጠነቅቃል በሚል በ11 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ወስኖበታል፡፡

አርበኞች ግንቦት7 የወያኔን ሰራዋት ገጥሞድ ድል በድል ኦናል በዚህ ዉግያ የወንበዴዉ ቡድን እግሬ አዉጪኝ ፈርጥጠዋል

በመከላከያ ሰራዊት በተፈጠረ አለመግባባት ግዲያ ተፈፀመ። ሀምሌ 5 ቀን 2009ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሳዓት በሰሜን ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ማህበረ ስላሴ ሻሽጊ ቀበሌ ላይ ለስራ የወጡ ወታደሮች ላይ አንድ የክፍሉ አባል ሁለት አመራሮችን ተኩሶ ገደላቸው።

የጠቡ መንሰዔ የክፍሉ አመራር ሻምበል ማዐረግ ያለው የትግራይ ተወላጅ ከአንድ አርሶ አደር ቤት በመግባት ነብሰ ጡር የሆነችን እናት ከቤቷ አውጥቶ” አንቺ ሽፍታ ከቤትሽ ትደቢቂያለሽ፣ቀለብ ታቀርቢያለሽ፣ያረገዝሽው ልጅም የሽፍታ ነው ” በማለት በርግጫ ይመታታል እሷም ራሳን ስታ ስትወድቅ የኦሮሞ ተወላጅ የሆነው ወታደር “እቺ እርጉዝ ሴት ምን አደረገችህ እኛ የመጣነው በአካባቢው ገቡ የተባሉ ፀረ ሰላም ኃይሎችን ለመያዝ ነው አንተ ግን እየሰራህ ያለህው ስራ ስህተት ነው ” ይለዋል ከዚያም ይህ የህወኃት ሻምበል ብሄርና ሊላ ክብር የሚነካ ስድብ ይሰድበዋል ተሰዳቢው በቀጥታ ተኩሶ አመራሩን ገደለው፣ ከዚያም ሊላኛው የትግራይ ተወላጅ የሆነ የአምሳለቃ ማዐረግ ያለው ይህን ወታደር ለምን ትገድለውለህ በማለት ሲሰድበው እና ሊገድለው ሲል ቀድሞ በመምታት ገድለቷል።

የሁለቱ ሟቾች አስከሬን የዛኑ ቀን ማታ በሁለት ፔካፕ ወታደራዊ ተሽከርካሬ ተጭኖ ወደ ነጋዴ ባህር ጦር ካምፕ ከመጣ በኃላ በትናንትናው ቀን ወደ ጎንደር ተወስደው አዞዞ ሎዛ ማሪያም ቤተክርስቲያን ተቀብረዋል።

ይህ አይነት ድርጊት በተደጋጋሜ እየተከሰተ ይገኛል ይህም ወታደር በአንዴት ነብሰ ጡር አናት ላይ ይሂን አይነት ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ሲፈፀምባት ዝም ብሎ ማየት እና ህሊናው ሊቋቋመው ባለመቻሉ የጀግንነት ስራ ነው የሰራው በመሆኑም ለሊሎች ትልቅ አርዐያ ይሆናል እንላለን።

የኮንደሚኒየም ቤቶች ላይ ያደገው የዋጋ ጭማሪ ተመዝጋቢዎችን ማስቆጣቱ ተነገረ

የአዲስ አበባ አስተዳደር በመካከለኛ ገቢ ለሚኖሩ ሰዎች በገነባቸው የኮንደሚኒየም ቤቶች ላይ ያደገው የዋጋ ጭማሪ ተመዝጋቢዎችን ማስቆጣቱ ተነገረ ። አስተዳደሩ የ972 ቤቶችን እጣ ከማውጣቱ ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ መካከለኛ ገቢ ላላቸው የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዋጋን በፊት ከታቀደው 56 በመቶ ጭማሪ አድርጓል ። ለቤቶቹ 11 ሺህ 88 ተመዝጋቢዎች የነበሩ ሲሆን ሁሉም ሙሉ በሙሉ የሚጠበቅባቸውን ክፍያ የፈጸሙ ናቸው ተብሏል ። የአዲስ አበባ አስተዳደር የቤቶች ልማትና ቁጠባ ድርጅት 972 ቤቶችን ገንብቶ ከነዋሪዎች ተቀማጭ ገንዘቡን ለሚሰበስበው ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስረክቧል ። ቤቶቹን ለመገንባት እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2013 ሲታቀድ ለባለ አንድመኝታ ቤት 228 ሺህ 900 ብር ፣ ለባለ ሁለት መኝታ ቤት 330 ሺህ ብር ፣ለባለሶስት መኝታ ቤት ደግሞ 386 ሺህ ብር በስኰር ሜትር ለማስከፈል ስምምነት ተደርሶ ነበር ። ይህም ሆኖ ግን በመሰረተ ልማት ፣ በሰራተኛ ዋጋ መጨመርና በቤቶች የዲዛይን ለውጥ ምክንያት የቤቶቹ ዋጋ ላይ በ56 በመቶ ጭማሪ መደረጉን አስተዳደሩ ይፋ አድርጓል እናም በአዲሱ ዋጋ ተመን መሰረት ለባለ ሁለት መኝታ ቤት 614 ሺህ 602 ብር ፣ ለባለ ሶስት መኝታ ቤቶች 735 ሺህ 241 ብር ፣ ለባለ አራት መኝታ ቤቶች ደግሞ 829 ሺህ 568 ብር እንዲሆን መደረጉን ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል ። ይህ ሲሆንም ለባለ 4 መኝታ ቤት ብሎ የተመዘገበ ነዋሪ ባለመኖሩ ለ3 መኝታ ቤት የተመዘገቡ አቅማቸው የሚፈቅድ ከሆነ ወደዚሁ ደረጃ እንደሚሸጋገሩ የአዲስ አበባ የቤቶች ልማትና ቁጠባ ድርጅት አስታውቋል። ይህ ካልሆነ ግን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተመዝጋቢ የሌላቸውን ባለ አራት መኝታ ቤቶች ለአስተዳደሩ መልሶ እንደሚሸጣቸው ማሳወቁን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል ። ቤቶቹ ሲተላለፉ አቅም የሌላቸው ከተገኙ በተጠባባቂነት የተወስውዱ 20 ባለእጣ እድለኞች በተተኪነት መያዛቸውንም ለማወቅ ተችሏል ። ይህ በእንዲህ እንዳለም የ2013 የቤት ተመዝጋቢዎች ከዚህ ቀደም ከነበረው ዋጋ ተጨማሪ ክፈሉ መባሉ እንዳስቆጣቸውና ከነዋሪዎች ጋር ምክክር ሳይደረግ የዲዛይን ለውጥ ተደርጎ ብትፈልጉ ውሰዱ መባሉ አግባብ እንዳልሆነ መናገራቸውን የኢሳት መንጮች ገልጸዋል ። የቤቶቹ እጣ ሲወጣ 20 በመቶ ለመንግስት ሰራተኞች 3 በመቶ ለዲያስፖራ ቀሪዎቹ 77 በመቶ ደግሞ ለሁሉም ተመዝጋቢዎች ተደርጎ መከናወኑንም አስተዳደሩ አስታውቋል ። በ2013 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለማግኘት 165 ሺህ ሰዎች ሲመዘገቡ ከነዚሁም መካከል 140 ሺዎቹ በየወሩ እየቆጠቡ እድሉን ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ዘገባው አመልክቷል ። ይሁንና በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የገንዘብ እጥረት ስለገጠመው ቤቶቹን ለመገንባት የበጀት ችግር አለብኝ በሚል ለፓርላማ ባለፈው ሰሞን ማሳወቁ ይታወሳል ።

%d bloggers like this: