በቤንሽልንጉል ጉሙዝ ገሰንገሳ ተብሎ ከሚጠራው ሰማይ ጠቀስ ተራራ ላይ ለግዳጂ የተላኩ የህወሓት ወታደሮች ካደሩበት ስፍራ ተገለው ተገኙ።

ከቀናት በፊት በወንበራ ወረዳ ቦጎንዲ ተብሎ ከሚጠራው ከፍተኛ ስፍራ የተተከለው የመረጃ መሰብሰቢያ ቋት (ራዳር) በወያኔ አገዛዝ የተማረረ ወታደር ጉዳት ካደረሰበትና አንድ ፖሊስ ከገደለ ወዲህ ራዳሩን ሲጠብቁ በነበሩት የህዳሴ ዲቪዥን የፈጥኖ ደራሽ የፌድራል አባላት እርስ በርስ አለመተማመን የነበረ ሲሆን ከበላይ አዛዦች በተላለፈ መመሪያ መሰረት ገዳዩ ፖሊስ በከፍተኛ ስቃይ ሲመረመር ቆይቶ የተረሸነ ሲሆን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 11 የፌድራል አባላት እንዲታሰሩ ና ራዳሩን የሚጠብቀው ሃይል በአስቸኳይ እንዲቀየር ተደርጓል።በዚህ ወቅት ከፖዊ በግልገል በለስ አድርጎ ድባጢ ወረዳ አቋርጦ በቡለን ወረዳ ወደ ወንበራ ያቀነው የወታደር ሃይል ገሰንገሳ ከሚባለው ሰማይ ጠቀስ ተራራ ላይ በተከፈተበት ጥቃት 4 ወታደሮች መገደላቸው ይታወሳል። በዚህ እጂግ ከፍተኛ ቅዝቃዜ በሚስተናገድበት ስፍራ የተሰገሰጉ የነፃነት ሃይሎች አሉ በሚል ከሳምንት በፊት ወደ ስፍራው አዲስ ተዋጊ ሃይል የተላከ ሲሆን ከትናንት በስቲያ ሰኞ ዕለት 14 የቡድኑ አባላት ባደሩበት ተገለው ተገኝተዋል። የተገደሉት የህወሓት ወታደሮች በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ ቅዝቃዜ መቋቋም ካለመቻላቸው በላይ የአካባቢው መልከዓምድር እጂግ አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ሪፖርት ሲያደርጉ መቆየታቸው ታውቋል። 5ቱ ወታደሮች በሳንጃ ተወግተው የተገደሉ ሲሆን 9ኙ ግን የተመታ አካል እንደሌላቸው ተረጋግጧል። ከአሳሽ ቡድኑ ውስጥ 2 ወታደሮች ያሉበት አለመታወቁም የሁኔታው አደገኝነት በግልፅ እንደሚያሳይ ለመረጃው ቅርብ የሆኑ ሰወች ይናገራሉ።

ናትናኤል መኮንን16427630_1823259841262824_7449098933742497578_n

በዳባት ወረዳ በአጅሬ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በክትባት ሰበብ አስደንጋጭ ፍጅት በህፃናት ላይ የደረሰ ነው ተባለ

ዛሬ በዳባት ወረዳ በአጅሬ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በክትባት ሰበብ 4 ህፃናት ሲሞቱ 8 ደግሞ በከፍተኛ ህመም ላይ ናቸው። ይህ የመኪና መንገድ የሌለው አካባቢ የሚሩረት ወገኖች በሄሊኮፍተር እርዳታ ካልደረሰላቸው ብዙ ህፃናት የሞት አደጋ ላይ ናቸው። ዳባት ከተማ ውስጥም በተመሳሳይ መንስኤ 1ህፃን ቅዳሜ ሞቷል።
የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከየካቲት 16/2009 ዓ.ም ጀምሮ በመላ አገሪቱ ስለሚሰጥ ህጻናትን ያስከትቡ በሚል በይፋ የተጀመረው ዘመቻ ህፃናት እየጨረሰ ነውና ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ።
ህዝቡ በዚህ አስደንጋጭ ሆን ተብሎ በተቀነባበረ ወንጀል ቁጣውን እየገለፀ ነው። ከአሁን በሁዋላ አናስከትብም ብሏል። የአካባቢው የወያኔ መንግስት የካቢኔ አመራርና የጤና ሰራተኞች ደንግጠዋል። ይህ ወንጀል በቀጥታ ከወያኔ የበላይ አመራር መጥቶ በአፋኙ የኮማንድ ፖስት ተግባራዊ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ይህ አካባቢ የወያኔ የጭቆና አገዛዝ በቃኝ በማለቱ ላለፉት 6 ወራት የጦር ቀጠና እንደሆነ በተከታታይ ስንዘግብ መቆየታችን ይታወቃል።
ሙሉነህ ዮሃንስ

14369897_632974823553373_2956361535740993228_n

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ6 አየር ሃይል አባላት ላይ የእስራት ቅጣት አስተላለፈ

የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የአርበኞች ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሲያቀኑ በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉ ስድስት የአየር ሃይል አባላት ላይ ከሶስት እስከ 10 አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት አስተላለፈ።
ከሳሽ አቃቤ ህግ በሰኔ 2007 አም ተከሳሾቹ የአየር ሃይልን በመክዳት ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሊያመሩ ሲሉ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ላይ እንደተያዙ በክሱ አመልክቶ እንደነበር ይታወሳል።
የቀድሞው የአየር ሃይል አባላት ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል የማፍረስ አላማ ይዘው በሽብር ድርጅት ውስጥ አባላት በመሆንና በሽብር ድርጊት ተግባር ላይ ለመሳተፍ በማሰባቸው የሚል ክስን አቅርቦ እንደነበርም በወቅቱ መዘገባችን አይዘነጋም።
ይሁኑ የክስ ሁኔታ ሲመለከት የቆየው ፍርድ ቤቱ በስድስቱ ተከሳሾች ላይ ከሶስት አመት እስከ 10 አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ማስተላለፉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ፣ መ/አ ብሩክ አጥናዬ፣ መ/አ ዳኔኢል ግርማ፣ መ/አ ጋዘኸኝ ድረስ እንዲሁም አቶ ተስፋዬ እሸቴ እና አቶ ሰይፉ ግርማ ስድስቱ ተከሳሾች ናቸው።
ከአንደኛ እስከ አራተኛ ያሉት መቶ አለቀ ተከሳሾች በ10 አመት አምስተኛና ስድስተኛ ተከሳሾች ደግሞ በሶስት አመት ከስድስት ወር እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ መወሰኑ ታውቋል።
ከተከሳሾቹ መካከል መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤና ስደተኛ ተከሳሽ ሰይፉ ግርማ በሃምሌ ወር በቂሊንጦ እስር ቤት ደርሶ ከነበረው የእሳት አደጋ እጃቸው አለበት ተብሎ ተደራራቢ ክስ ከተመሰረተባቸው በርካታ እስረኞች ጋር እንደሚገኙበትም ለመረዳት ተችሏል።
የፍርድ ውሳኔው ሰኞ በተላለፈበት ወቅት አንደኛ ተከሳሽ ከግንቦት ወር 2008 አም ጀምሮ በጨለማ ክፍል እንዲቆዩ መደረጋቸውንና ከቤተሰቦቻቸው ጋርም ተገናኝተው እንደማያውቁ ለችሎት አስረድተዋል።
ከእነዚህም በተጨማሪ በምርመራ ወቅት ከባድ ድብደባ ሲፈጸምባቸው መቆየቱንና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲፈጸምባቸው እንደነበር አቤቱታቸውን አሰምተዋል።

15542125_1875786285986970_8207959935562296567_n

በሊቢያ የውሃ ዳርቻ ሴቶችና ህፃናትን ጨምሮ ከ200 በላይ ስደተኞች ከመስመጥ አደጋ መትረፋቸው ተዘገበ ፡፡

በሊቢያ የውሃ ዳርቻ ሴቶችና ህፃናትን ጨምሮ ከ200 በላይ ስደተኞች ከመስመጥ አደጋ መትረፋቸው ተዘገበ ፡፡

ኢትዮጵያውያንስ ይገኙበት ይሆን?፡፡CGTN Africa ዝርዝሩን ይከታተሉ

ከእነ አቶ በቀለ ገርባ ጋር ተመሳጥረዋል የተባሉ ፖሊሶች ክስ ተመሰረተባቸው

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩት አቶ በቀለ ገርባ እና ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ጋር ምስጢራዊ ግንኙነት ሲያደርጉ ነበር የተባሉ የቂሊንጦ ወህኒ ቤት ፖሊሶች ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ ተከሳሾቹ የፖሊስ አባላት መሳይ በላይ፣ ጌታቸው ሰይድ፣ ዋና ሳጅን ሐጎስ ወልደ ሥላሴ፣ ፍላቴ ቁለምና ምክትል ኢንስፔክተር ገመቹ ዳንዳአታኮ የሚባሉ ሲሆኑ፣ በተለያዩ ጊዜያትም ለተለያዩ እስረኞች በአማርኛ፣ በኦሮሚኛ እና በእንግሊዝኛ የተጻፉ መልዕክቶችን ወደ ውጭ በማውጣት ለጋዜጠኞች መስጠታቸውን ዓቃቤ ህግ በክሱ ላይ ገልጿል፡፡
በሙስና ወንጀል ተከሰው በቂሊንጦ ከሚገኙት ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ እና የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ከሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ጋር ተከሳሾች የተለየ ግንኙነት ነበራቸው ሲል የገለጸው ዓቃቤ ህግ፣ ከዶ/ር ፍቅሩ 1 ሺህ ብር በመቀበል የሞባይል ስልክ ወደ ቂሊንጦ አስገብተው እንዲደውሉ አድርገዋል ሲል ዓቃቤ ህግ አክሎ ገልጽዋል፡፡ እንደዚሁም በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት አቶ በቀለ ገርባ 40 ሺህ ብር እንዲያስገቡላቸው ሲጠይቋቸው በመስማማት፣ ጎተራ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ድረስ በመሄድ ማንነቱ ካልታወቀ ግለሰብ ተቀብለው፣ ገንዘቡን እኩል ቦታ ከከፈሉ በኋላ ወደ ወህኒ ቤቱ አስገብተዋል ያለው ዓቃቤ ህግ፣ ተከሳሾቹ ገንዘቡን ላስገቡበት ውለታም 10 ሺህ ብር ተቀብለዋል ብሏል፡፡
‹‹ተከሳሾቹ ከማረሚያ ቤቱ የቀጠሮ እስረኞች ጋር ያልተገባ ግንኙነት በመፍጠር ቅርፅና ይዘታቸው ያልታወቁ መጣጥፎችን ለጋዜጠኞች ከማድረሳቸው በተጨማሪ፣ ከ200 ብር በላይ ወደ ማረሚያ ቤቱ እንደማይገባ እያወቁ ለእስረኞች እስከ 70 ሺህ ብር ድረስ አስገብተዋል፡፡ ለራሳቸው ደግሞ ከ300 ብር እስከ 30 ሺህ ብር ድረስ ተቀብለዋል፡፡›› በማለት በመሰረተው የክስ ዝርዝሩ ላይ የገለጸው ዓቃቤ ህግ፣ በአጠቃላይ ተከሳሾቹ ፖሊሶች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1ሀ)፣ 38 እና የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9(1ሀ) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ ሥልጣንን ያላግባብ መጠቀም ወንጀል ተከስሰዋል ብሏል፡፡

%d bloggers like this: