የአውሮፓ ህብረት የስደተኞችን ፖሊሲ ሊቀይር ነው

ህብረቱ አዲስ የሚቀይረው ህግ ከተለያዩ ሃገራት ወደ አውሮፓ የሚገቡ ስደተኞችን የጥገኝነት ጥያቄ የተመለከተ ነው።

አንድ ስደተኛ መጀመሪያ እግሩ ባረፈበት ሃገር ጥገኝነት የመጠየቅ መብት እንዳለው፥ አሁን ያለው የህብረቱ የስደተኞች ፖሊሲ ይደነግጋል።

ይህ የደብሊኑ ስምምነት ግን እየጨመረ ከመጣው የስደተኞች ቁጥር አንጻር ማሻሻያ ያስፈልገዋል ተብሏል።

በዚህም ከ19 90ዎቹ ጀምሮ ስራ ላይ ያለውን ፖሊሲ መቀየርና ማሻሻል መፍትሄ መሆኑን ነው የህብረቱ መግለጫ የሚያሳየው።

የአሁኑን ደንብ ትንሽ ማሻሻል እና በብዛት ስደተኛ የሚቀበሉ ሃገራትን መደገፍና ማገዝ አንዱ አማራጭ ይሆናልም ነው የተባለው።

አልያም ከፖሊሲ ማሻሻያ ጋር ስደተኞችን ለሃገራት እኩል ማከፋፈልም ህብረቱ ሊከተለው የሚችለው አማራጭ ነው እየተባለ ነው።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የህብረቱ አባል ሃገራት የትኛውም አይነት አማራጭ እንደማይዋጥላቸው ገልጸዋል።

ምክንያቱም በቀደመው ደንብ መሰረት ስደተኞች ጥገኝነት የሚጠይቁት እግራቸው መጀመሪያ በረገጠበት ሃገር እንጅ ድንበር ተሻግረው ያረፉበት ሃገር አይደለምና።

በደብሊኑ ደንብ መሰረትም ጥገኝነት የጠየቁ ስደተኞችን ከሃገራቸው የማስወጣት እና ያለማስጠለል መብት አላቸው።

የጥገኝነት ጥያቄው መጀመሪያ እግራቸው የረገጠበትን እንጅ የገቡበትን ሃገር አይመለከትምና።

ይህን ደግሞ ብሪታንያን ጨምሮ በርካታ ሃገሮች ይፈልጉታል።

እናም የትኛውም አይነት አማራጭ ቢቀርብ የቆየውን ህግ ብቻ መተግበር ምርጫቸው እንደሆነ ነው ሃገራቱ የገለጹት።

በሳምንቱ መጀመሪያ ከመካከለኛው ምስራቅ ቱርክን ተጠቅመው ግሪክ የደረሱ ስደተኞችን ወደ ቱርክ የመመለሱ ስራ መጀመሩ ይታወሳል።

202 ስደተኞችም ከግሪኳ የሌዝቦስ ደሴት ቱርክ ዲኪሊ ደርሰዋል።

በርካታ የአውሮፓ ሃገራትም የስደተኞችን ፍልሰት ለመቀነስ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ።

ድንበራቸውን ከመዝጋት ጀምሮ የተጠናከረ ጥበቃ ማድረግና ለመግባት የሚሞክሩትን ባሉበት ማቆየት የሚጠቀሱ እርምጃዎች ናቸው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

በትላንትናው ምሽት የቱርኳ ዋና ከተማ አንካራ በፍንዳታ ተናጠች

በትላንትናው እለት ምሽት በቱርክ አንካራ በተከሰተ ፍንዳታ የ37 ሰዎች ህይዎት ሲቀጠፍ ከመቶ በላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ይህ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በከተማዋ ዕምብርት ላይ የደረሰ ሁለተኛው ጥቃት ነው ተብሏል። በመኪና ላይ የተቀነባበረው ፍንዳታ ከኩርድ አማጽያን (ነጻ አውጭ) ቡድን ጋር ግንኙነት ባላት ሴት እንደተፈጸመ ታውቋል። ባለፈው ወር የካቲት 9 / 2008 በተመሳሳይ መልኩ 28 ሰዎች ሲገደሉ 61 ያህል መቁሰላቸው የሚታወስ ነው። ሁለቱም ፍንዳታዎች የተፈጸሙት የበርካታ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መገኛ እና የከተማው ማዕከል በሆነው ”ክዝላይ” በተሰኘው ቦታ ላይ መሆኑ ተዘግቧል። ቀዳሚው ፍንዳታ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መስሪያ ቤት አጠገብ የተፈጸመ ሲሆን ፤ በወቅቱ ከስራ የውጡ ወታደሮች እና ሲቪል ዜጎችን ያሳፈሩ የሰራተኛ ማጓጓዣ አውቶቡሶች ላይ ያነጣጠረ ነበር።
የትላንትናው ፍንዳታ ደግሞ የከተማ ውስጥ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች መነሻ አቅራቢያ አሸባሪዋ የራሷን መኪና በተጠመደ ቦንብ በማፈንዳቷ መድረሱ ነው የታወቀው። ተሳፋሪ ጭኖ ለጉዞ ይንቀሳቀስ የነበረ አንድ አውቶቡስና ሌሎች በዙሪያው ያሉ በርካታ አውቶሞቢሎች ተቃጥለዋል። በጥቃቱ ሰለባ የሆኑት በሙሉ ሰላማዊ ዜጎች መሆናቸው ታውቋል። በተለይም በትላንትናው ዕለት በሀገሪቱ ሙሉ የተከናወነውን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና አጠናቀው ለመዝናናት ወደቦታው የወጡ ወጣቶችና ቤተሰቦቻቸው የጉዳቱ ተጠቂ እንደነበሩ የዜና ምንጮች ጠቁመዋል።
ፍንዳታውን ተከትሎ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኢርዶጋን በሰጡት መግለጫ ”መንግስታችን ለሚሰነዘርበት ማንኛውም የሽብር ጥቃት ፣ ራስን የመከላከል ህጋዊ መብቱን ተጠቅሞ ፣ ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት ወደኋላ አይልም” ካሉ በኋላ ህዝቡ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ ባንድነት እንዲቆም ጥሪያቸውን ማስተላለፋቸው ታውቋል።
በመግለጫቸው ”ቱርክ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና በተፈጠረው ያለመረጋጋት ምክንያት የሽብር ኢላማ እየሆነች ነው” ያሉ ሲሆን ፤ አስከትለውም ”የሽብር ቡድኖች እና እነሱን በሽፋንነት የሚጠቀሙ ኃይሎች ከጸጥታ ኃይሎቻችን ጋር በሚያደርጉት ትንቅንቅ ሽንፈትን ሲከናነቡ ፤ እጅግ አሳፋሪና ከስነ ምግባር ባፈነገጠ መልኩ ሲቪል ዜጎቻችን ለማጥቃት የትኛውንም አማራጭ መከተልን መርጠዋል” ሲሉ ተደምጠዋል። ያገራችን ሉዓላዊነት እንዲሁም የህዝባችንን አንድነት ዒላማ ያደረገው ይህን መሰል አጸያፊ ጥቃት በሽብር ትግሉ ላይ ያለንን ቁርጠኝነት ፈጽሞ አይቀንሰውም፤ ይልቁንም ጽናትን ያላብሰዋል ሲሉ አክለዋል ፕሬዝዳንቱ።
የቱርኩ ፕሬዝደንት በፍንዳታው ምክንያት ወደ አዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ ለመሄድ የነበራቸውን ዕቅድ መሰረዛቸው የታወቀ ሲሆን በሌላ በኩል ግን የሁለትዮሽ ስብሰባው ወደ ቱርክ ዙሮ በነገው ዕለት በአንካራ ከተማ ሊካሄድ መሆኑ ተዘግቧል። ይህ ስብሰባ ከወር በፊት ታቅዶ የነበረ ወሳኝ የትብብር ውሎች የሚፈረሙበት ሲሆን ባለፈው ወር በደረሰው ጥቃት ምክንያት የተራዘመ ነበር። ይህን ተከትሎም የአዘርባጃን ፕሬዝደንት ኢልሃም አሊየቭ ወደ ቱርክ ለመምጣት መወሰናቸው ለቱርክ ያላቸውን ድጋፍ እና ጥብቅ ጉድኝት ማሳያ ተደርጎ የሚታይ ነው። ለአምስተኛ ጊዜ በሚከናወነው በዚህ ከፍተኛ ስትራቴጂያዊ የትብብር ካውንስል ለሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ወሳኝ ስምምነቶች ይፈረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የሞከሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታሰሩ።

 

 

አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ አስመልክቶ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የሞከሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታሰሩ። ዛሬ ጠዋት ወደ አራት ሰዓት ገደማ ከአሜሪካ ኤምባሲ ፊት የተገኙት ተማሪዎች ቁጥራቸው ወደ 20 እንደሚጠጋ የዓይን እማኞች ይናገራሉ።

ወትሮውንም በከፍተኛ ጥበቃ ስር ያለው ኤምባሲ ከተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ ሙከራ በኋላ በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ተጨማሪ ጥበቃ ሲደረግለት ተስተውሏል። በስድስት ፒክ አፕ መኪና በተጫኑ የአዲስ አበባ እና የፌደራል ፖሊስ ኃይሎች አካባቢው ሲጠበቅ እንዳስተዋሉ የዓይን እማኞች ይገልፃሉ።

በአሜሪካ ኤምባሲ ይታይ የነበረው አይነት ያልተለመደ የፖሊስ ክምችት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ዋናው በር እና አምስተኛ በር ረፋዱ ላይ እና ከሰዓት ታይቷል።

ከዚህ ሁኔታ ጋር በቀጥታ ይገናኝ አይገናኝ ባይታወቅም ወደ አምስት ሰዓት ግድም በኤምባሲው “እሳት ተነሳ” በሚል ጉዳያቸውን ለማስፈፀም በቦታው የተገኙ ባለጉዳዮች ከየቢሮዎቹ ለግማሽ ሰዓት ያህል እንዲወጡ መደረጋቸውን በቦታው የነበሩ ምንጮች ያስረዳሉ።

 

 

 

ለሐሙሱ ምርጫ የሚጠበቁት ዕጩ ታሰሩ

በኡጋንዳ በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዩዌሪ ሙሴቪኒን ይቀናቀናሉ ተብለው ግምት የተሰጣቸው ፖለቲከኛ ከሰዓታት በፊት በካምፓላ ፖሊስ ታስረዋል ።ምርጫው የሚከናወነው የፊታችን ሐሙስ ነው ።
ዶክተር ኪዛ ቢሲጌ ከዚህ ቀደም ብዛት ባላቸው አጋጣሚዎች እየታሰሩ ቢፈቱም የአሁኑ ምርጫው ወደ ድምፅ መስጠት ሊሸጋገር ቀናቶች ሲቀሩት መሆኑ አነጋጋሪ ይሆናል ።
ቢሲጌ በሶስት ፕሬዘዳንታዊ ምርጫዎች ተካፍለው ሶስቴም በሙሴቪኒ መረታታቸው ተነግሯል ።በአራተኛው አሸናፊ ሆነው እንደሚወጡ ተስፋ በሰነቁበት ሰዓት ደግሞ ታስረዋል ።
የ71 ዓመቱ ሙሴቪኒ ኡጋንዳን ለ30 ዓመታት በመምራት ራሳቸውን ለአምስተኛው ዙር ምርጫ እያዘጋጁ ነው ።
አሁን የታሰሩት ቤሲጊ የሙሴቪኒ የግል ሀኪም በነበሩባቸው ዓመታት ከፍተኛ ሽልማቶች ሲበረከቱላቸው ቢቆዩም የሙሴቪኒን ወንበር መመኘት ከጀመሩበት ቅፅበት አንስቶ ወህኒ እየተወረወሩ ይገኛሉ ።

Dawit Solomon Yemesgen's photo.

በሳውድ አረቢያ በሂጅራ አቆጣጠር ረቢ አሳኒ 27 1437 አ•ሒ ጀምሮ በአይነቱ ልዩ የሆነ ከበድ ያለ ፍተሻ እንደሚደረግ ታወቀ

በመከ በሪያድ መዲና እና ጀዳ በሚካሄደው ተፍቲሽ ላይ የሳውድ አረቢያ የመከላከያ ሀይል የፖሊስ ሀይል ጀዋዛት የውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ቀይ ጨረቃ እንደሚሳተፉበት ተነግሮዋል

ፍተሻው የሚያተኩረው የኢቃማን ህግ በመጻረር ህጉ በማይፈቅደው የስራ መስክ ላይ በተሰማሩ ማለትም ሳዒቅ ኻስ ሆነው እያሉ አሚልነት የሚሰሩ እንዲሁም ኢቃማቸው የተበለገባቸው እና ኢቃማ በሌላቸው ሰዎች ላይ እንደሆነ ተጨምሮ ተገልጾዋል

ይህ በእንዲህ እንዳለ የመካ ሙከረማ ከተማ ፖሊስ ከረቢዐል አወል ወር መጀመሪያ ጀምሮ በአንድ ወር ግዜ ውስጥ ብቻ 98890 የኢቃማ ህግን የጣሱ እና ኢቃማ የሌላቸውን መጅሁሎች መያዙን አስታውቆዋል
ከተያዙት 98890 ሰዎች መሀከል 388 የስራ ህግን የጣሱ የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ሲሆኑ ፖሊስ ከሰራተኛ ጉዳዮች ሚኒስተር ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል

4090 የሚሆኑ የኢቃማ ህግን የጣሱ እንደሆነ ጨምሮ አስታውቆዋል

በሌላ በኩል ከዚህ በፊት በሌላ ስራ ዘርፍ በመስማራት የሚታወቁት ደውሪያ ወይም 999 ፖሊሶች የጀዋዛት ሹርጣዎች የሚሰሩትን ስራ እንዲሰሩ ህገወጥ ስደተኞችን መያዝ እንዲችሉ ተፈቅዶላቸዋል
ከዛሬ ሀሙስ 21/1/2016 ጀምሮ ሁሉም የሳውድ አረቢያ ፖሊሶች የውጭ ሀገር ዜጎችን እያስቆሙ ኢቃማ መጠየቅ እንዲችሉ ትዕዛዝ እና ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል

ማነኛውም የኢቃማ እና የስራ ህግን በመጻረር ሳውድ አረቢያ ላይ የሚኖሩ የውጭ ዜጎችን ለመያዝ ያስችል ዘንድ 987 የነጻ ስልክ ይፋ ማድረጋቸውን ይፋ አድርገዋል

%d bloggers like this: