የህወሓትን አምባገነን ስርዓት በመክዳት የሚጠፉት ወታደሮች ቁጥር ጨምሯል።

በሰሜን ዕዝ 25ኛ ክ/ጦር አባላት በቡሬ ግምባር እና በማንዳ አካባቢ ካሉ የመከላከያ አባላት ስርዓቱን በመክዳት እየጠፉ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ከህዝቡ ጋር ተቀላቅለው ገብተዋል። የህወሓት ወታደራዊ አዛዦች ታማኝ ቅጥረኞች የጠፉትን ለመፈለግ ወደ ተለያዩ ከተሞች በውሎ አበል ወጥተዋል።
ትግሬ ወያኔ ካልሆኑ በስተቀር በተለይ ለአማራ እና ለኦሮሞ ተወላጆች የአመት ዕረፍት እና ቤተሰብ ጥየቃ የማይፈቀድበት የሰሜን ዕዝ ቡሬ ግምባር ስርዓቱን በመክዳት በተለያዩ መንገዶች ወደ ታጋይ አርበኞች ለመቀላቀል ያልቻሉ እራሳቸውን በመሰወር ላይ ሲሆን የስርዓቱ ወታደራዊ ጀነራሎች ከፍተኛ መቃወስ ውስጥ ገብተዋል።በቤተሰብ ወዳጂ ዘመድ ጉትጎታ እና ስርዓቱ እያደረሰው ባለው ጭቆናና ግፍ ተማረው 6 የአማራ ተወላጆች በተለያየ ቀን ተከፋፍሎ በሳምንት ውስጥ ከቡሬ ግምባር ለማምለጥ ችለዋል። ከኢትዩ-ኤርትራ -ጂቡቲ ድንበር አሊ ሙሳ ተራራ ጀምሮ በተመደቡበት ሁሉ በከፍተኛ ምሬት ውስጥ የሚገኙት የመከላከያ አባላት በስርዓቱ የሚደርስባቸው በደል ግፍ መጀመሪያም አማራጭ አጠን የገባንበትን ወታደራዊ ሙያ እጂጉን እንዲያስጠላን አድርጓል ይላሉ። በወያኔ ወታደራዊ አዛዦች የሚደርስብን በደል ለስርዓቱ የስልጣን ወንበር ጠባቂ አድርጎን በጥይት አረር ውስጥ እየጣደን እስከመቼ በዝምታ እንመልከት በማለት ከህዝባቸው ጋር ለመታገል መወሰናቸውን ተናግረዋል ። ለምግብ(ሬሽን ) በየወሩ ከ350 ብር እስከ 400 ብር ከተራው ወታደር እየተቆረጠብን ፣ ወደ ኪሱ የሚገባው ከ700 ብር በታች ነው። በዚህም ላይ በየአራት ወሩ ደሞዝ አይሰጥም ይህም ለወታደታዊ ልብስ(ሬንጀር ) ፣ቲሸርት ፣ጫማ ወዘተ ተብሎ ይወሰዳል ። በተለያየ ጊዜም በወታደራዊ ትግሬ አዛዦች ውሳኔ ብቻ ያለእኛ ፈቃድ ለመለስ ፖርክ ፣ፍውንዴሽን እየተባለ በአክሱም አካባቢ ት/ቤት ለማሰራት እየተባለ ፣መሰል ምክንያቶችን ደርድረው ከ700 ብር በታች ከምግብ ተቀንሳ የምትደርሰንን ደሞዝ ቆራርጠው ይወስዱታል በማለት በምሬት ይናገራሉ።
በአብዛኛው ወታደሮች ጠፍተው ለመውጣት ሱና ፣ ሪዳር፣ ዲሽቶ፣ ሚሊ የመሳሰሉ ኬላወችን ለማለፍ ከ13 ሺ እስከ 16ሺ ብር በአሽከርካሪወች ይጠየቃሉ ይሄም እድል ካለ ነው። ከዚህ ላይ እድል ሁኖ በኬላወቹ የተያዘ ፣ እንዲሁም ለማደን በሚወጡ ታማኝ ቅጥረኞች ተይዞ ወደ ካምፕ የሄደ ለመላ ወታደሮች እስር እንደተፈረደበት ለመቀጣጫ ይነገር እና ከተወሰነ ጊዜ የስቃይ እስር በኋላ ተባሯል ይባላል። ይህም ማለት ተረሽኗል ማለት ነው።
ብዛት ያላቸው ወታደሮች ወደ ተለያዩ አቅጣጫወች ሲጠፉ የተያዙ እና ተስፋ ቆርጠው በየካምፑ እስር ቤቱ የነበሩ ወታደሮች በአብዛኛው የት እንዳሉ አይታወቅም። ብዛት ያላቸው ወታደሮች ግን በስርዓቱ በመማረር በዚህ 2 ሳምንት ውስጥ ጠፍተዋል ፤አሁንም ጠፍተው ለመውጣት ብዙወቹ ቆርጠው ምቹ ሁኔታን ይጠባበቃሉ።ከእጃቸው የምትገባ ትንሽ ብርም በምሬት በየካምፑ አቅራቢያ በሚገኙ ትንንሽ መንደሮች በሲጋራ እና ጫት ሱስ ተጋልጠዋል።

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a comment