በጣልያኗ ሮም ከተማ 1,000 ገደማ ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከተጠለሉበት ህንፃ ተባረሩ

ከነዚህም 200 የሚሆኑት በጎዳና ለመተኛት መገደዳቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (UNHCR) አስታውቋል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች በሮም ከተማ ከቴርሚኒ ማዕከላዊ ባቡር ጣቢያ አጠገብ የሚገኘውን የስደተኞቹን መኖሪያ አስለቅቀዋል።

ስደተኞቹ ማንነታቸውን ለማረጋገጥ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው ነበር።

ከጎርጎሮሳዊው 2013 ዓ.ም. አንስቶ በስደተኞች ተይዞ የነበረው ሕንፃ እንዲለቀቅ አንድ የከተማዋ ዳኛ ውሳኔ ያሳለፉት ከሁለት ዓመት በፊት ነበር።

ከሕንፃው ከተባረሩት መካከል ሁለት ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ በርካታ እንስቶች እና ሕጻናት ይገኙበታል።

ለጉዳት የተጋለጡ ስደተኞች አማራጭ ማረፊያ እንደሚሰጣቸው የገለጠው የሮም ከተማ ማዘጋጃ ቤት እንስቶች እና ሕፃናት ግን ለጊዜው ወደ ሕንፃው እንዲመለሱ እንደተፈቀደላቸው ገልጧል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት እና የጣልያን ምክር ቤት የሰብዓዊ መብቶች ተመልካች ኮሚቴ ግን የሮም ከተማን እርምጃ ወቅሰዋል።

“ስደተኞቹ ወደ ተሻሉ መኖሪያዎች ሊዘዋወሩ ይገባል” ባይ የጣልያን ፖለቲከኞች በበኩላቸው ውሳኔውን አድንቀዋል።

Image may contain: 1 person, child and outdoorImage may contain: people sitting and outdoor

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: