ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲሰደዱ በኮንጎ ህይወታቸው ያለፈ 19 ኢትዮጵያዊያን አስከሬን ቅዳሜ ሌሊት አዲስ አበባ መግባቱ ተነገረ

ስደተኞቹ በኬንያና በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አድርገው በዛምቢያ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ነበር ጉዞውን የጀመሩት።
ከኬንያ ሲነሱ አሳ እና ለውዝ በጫነ ኮንቴይነር ውስጥ የሞቱ 19 ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ 95 የተለያዩ አገራት ስደተኞች ለጉዞ አመቺ ባልሆነ ሁኔታ ነበር ታፍነው አስከፊውን የስደት ጉዞ የተያያዙት።
በኮንጎና ዛምቢያ ድንበር መካከል ከሉሳካ 300 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ በረሃማ አካባቢ ውጥናቸውን ሳያሳኩ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።
ከሞቱት አብዛኞቹ ወጣቶች ሲሆኑ ከነዚህም መካከል 14ቱ በሃዲያ ዞን ይኖሩ የነበሩና በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ለህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ከፍለው ነበር ጉዞውን ያደረጉት።
ከሟቾች መካካል የአንደኛው ስደተኛ አጎት አቶ ደባሱ ዋሌ እንደተናገሩት “ሟች በአገር ቤት የስምንተኛ ክፍል ተማሪ የነበረ ሲሆን በትምህርቱ ጎበዝና በደረጃውም አንደኛ የሚወጣ ነበር”።
ትምህርቱን አቋርጦ ደቡብ አፍሪካ ካለው ወንድሙ ዘንድ እሄዳለው በማለት ለጉዞ መነሳቱንና ቤተሰብ ከልክሎት እንደነበር ያስታውሳሉ።
ይሁንና ቤተሰብ ሳያውቅ በደቡብ አፍሪካ ከሚኖሩ ጓደኞቹ ጋር ተነጋግሮ ኬንያ ገብቶ “ሄጃለሁ” በማለት ለቤተሰብ ስልክ መደወሉን ይናገራሉ።

“ገና ሳይበላና ሳይጠጣ፣ በልጅነቱ ያሰበውን ቤተሰቦቹን የመርዳት ውጥን ሳያሳካ እለወጣለሁ ብሎ በለጋነቱ በረሃ ቀረ” ይላሉ አጎቱ።

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት አሽከርካሪዎችን ለዛምቢያ መንግሥት አሳልፎ እንዲሰጥ ጥያቄ መቅረቡንም አስታውቀዋል።

ስደተኞቹ ለደቡብ አፍሪካ ቅርበት ያላቸውን አገራት በህገ-ወጥ መንገድ እንደ መተላለፊያ በመጠቀማቸው ለሞትና ለእስር ይዳረጋሉ።
በቅርቡም በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ በታንዛንያና ዛምቢያ ፖሊስ ተይዘው ለወራት በእሥር ቤት የቆዩ 88 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: