በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር በመድፍ የታጀበ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ነው

በትግራይ ና ኤርትራ ድንበር  በኢሮብ ወረዳ ማጭዓ ከሚባል አከባቢ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ:: የኢትዮጵያ መንግስትም  ሆነ የኤርትራ መንግስታት ስለተፈጠረው የተኩስ ልውውጥ ምንም ያወጡት መረጃ ባይኖርም ከሕወሓት መራሹ ኢትዮጵያ መንግስት በኩል ተዋጊ ጀቶች በባህር ዳር በኩል ወደ ሰሜን ሲሄዱ እንደተመለከቱ የዓይን እማኞች ገልጸዋል::

ትግራይ ድንበር በኤርትራና በወያኔ ጦር መካከል ጦርነት ተቀስቅሷል ጦርነቱ በከባድ መሳሪያ ሁሉ እንደታጀበ ይነገራል ።

ኢትዮጵያ

በኢሮብ የተጀመረው የተኩስ ልውውጥ በመድፍ ጭምር የታገዘ እንደሆነ ምንጮች የገለጹ ሲሆን ምን ያህል ሰው እንደተጎዳና መነሻው ምን እንደሆነ ለማረጋገጥ አልተቻለም::

የኤርትራ ሠራዊት ከማጭዓ ምብላዕ ሓኽለ እስከ እንዳ ማካኤል ቤተክርስቲያን ድረስ በመግባት ምሽጎችን መቆፈሩን የሚገልጹት የመረጃ ምንጮች የኤርትራ ሠራዊት ድንበር ጥሶ በመግባት ምሽግ እስከሚቆፍር ድረስ የድንበር ጠባቂዎች የት ነበሩ? የሚል ጥያቄን አስነስቷል::

ሕወሓት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ድንበር ሠራዊቱን እያስጠጋ ሲሆን ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ በጎንደር ዳባት አቅጣጫ ወደ ሰሜን መስመር በኦራል መኪኖች የተጫኑ ሠራዊቶች ሲሄዱ መታየታቸውን የዓይን እማኞች ገልጸውልኛል ሲል አክቲቭስት ሙሉነህ ዮሐንስ ዘግቧል::

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: