የህወሃት ደህንነቶች በሱዳን ኢትዮጵያውያኑን አርበኞች ግንቦት ሰባት እንዲሰልሉ እያስገደዱ ነዉ

ህዝባዊ ተቃውሞዎች በሀገሪቱ ዉስጥ ከተነሱበት ጊዜ ጀምሮ የህወሃት ደህንነቶች በሱዳን ውስጥ በሚገኙት 12 የስደተኞች ካምፖች ዉስጥ በመዘዋወር እና ኢትዮጵያውያኑን በግል በማስጠራት፤ አርበኞች ግንቦት ሰባት በሱዳን ከተሞች ውስጥም በስፋት እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ፤ አባለቱን በመሰለል እና በመጠቆም ትብብር የማታደርጉ ከሆነ እናንተንም ከአሸባሪ ለይተን አናያችሁም በማለት የማያውቁትን ነገር እንዲናገሩ እየተገደዱ መሆናቸውን ስደተኞቹ ተናግረዋል።


በሱዳን ካምፖች ውስጥ የሚኖሩና በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የህውሃት አገዛዝ ስለላዎችን በማካሄድ አብረውት እንዲሰሩ፣ ካለበለዚያ እንደሚታሰሩና እንደሚደበደቡ በማስጠንቀቅ ስደተኞችን በማጉላላት ላይ መሆኑን ከስፍራዉ የደረሰን ጥቆማ አመለከተ።

የህወሃት ደህንነቶች ስደተኞቹን በመሰብሰብና የስለላ ስልጠናዎችን በግዳጅ በመስጠት ግማሾቹን እዛው ሱዳን ውስጥ ተበታትነው በከተሞች ውስጥ የሚኖረውን ስደተኛ በማዋራት እና ጥያቄዎችን በመጠየቅ የአርበኞች ግንቦት 7 አስተሳሰብ የሚስተዋልባቸውን እና ህወሀትን የሚቃወሙትን እንዲጠቁሙ፤ እንዲሁም ግማሾቹ ወደ ትግል የሚቀላቀሉ መስለው በሱዳን በኩል ወደ ኤርትራ በመግባት ስለላዎችን ሲያደረጉ ቆይተው ከተወሰኑ ወራቶች በኋላ ተመልሰዉ በመውጣት ኤርትራ ውስጥ ያለውን የአርበኞች ግንቦት ሰባት እንቅስቃሴ በማጥላላት ለሚዲያ ፍጆታ እንዲውሉ የሚያደርግ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።

ከወራት በፊት ወደ ኤርትራ አምስት ስደተኞች ለስለላ ተልከው በዚያው በመቅረታቸዉ ደህንነቶቹ በሱዳን ካሰማሩዋቸው ሌሎች ስደተኞች ውስጥ የተወሰኑትን በመያዝ እዛው ሱዳን ውስጥ በሚገኝ ማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ በማስገባት አሰቃቂ ድብደባዎች እንደፈጸሙባቸምም ተናግረዋል። ከዛ በኋላ ወደ ኤርትራ የሚላኩ ስደተኛ ሰላዮችን የራሳቸው ከሆነ ታማኝ ግለሰብ ጋር መላክ መጀመራቸውንም ጠቅሰዋል።

አክለውም ባለፈዉ ሳምንት ወደ 10 የሚጠጉ ስደተኞችን ለስለላ ወደ ኤርትራ እንዲሄዱ ፈቃደኝነታቸውን ተጠይቀው ብዙም ሳያቅማሙ ፈቃደኛ በመሆናቸው ምክንያት ብትሄዱ እንደምትቀሩ ታስታውቃላችሁ ተብለው በእስር ቤት በስቃይ ላይ እንደሚገኙም ገልፀዋል።

በአማራ ክልል በአሁኑ ወቅት ባለው አለመረጋጋት እና በኑሮ ውድነት ምክንያት ወደ ሱዳን የሚጎርፈው ህዝብ ብዛት ቀን ተቀን እየጨመረ መምጣቱን እና ያንን ተከትሎም ህወሓት በርካታ ደህንነቶችን በተለይ ወደ ካርቱም በማስገባቱ ከተማዋ ከመጨናነቋ በተጨማሪ በየመንገዱ ኢትዮጵያውያን የሚደበደቡባት እና ወደ እስር ቤት የሚጋዙባት ሆናለችም ተብሏል።

የህወሃት አገዛዝ የሀገር ውስጡ አልበቃዉ ብሎ በካርቱም ዙሪያ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ እስር ቤቶች እንዲሰሩ ከሱዳን መንግስት ጋር እየተስማሙ እንደሆነም መረጃዎች አመልክተዋል።

 

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: