የጎንደርን ህዝብ ትጥቅ ለማስፈታት በሚል በወረታ ፣ አዘዞ፣ ዳባትና እብናት የአጋዚ ጦር መስፈሩ ተነገረ

በጎንደር የአገዛዙን ግፍና በደል በመቃወም ህብረተሰቡ ከፍተኛ አመጽና የትጥቅ ትግል እያካሄደ መሆኑ ስርአቱን በእጅጉ አሳስቦታል ።

በተለይም በሰሜን ጎንደር የሚገኙ የነጻነት ሃይሎች በስርአቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆናቸው በአካባቢው ከፍተኛ የአጋዚ ጦር እየተሰማራ መሆኑ ተነግሯል ። ‘

በዚሁም ምክንያት በሰሜን ጎንደር ህዝቡን የጦር መሳሪያ ለማስፈታት ከፍተኛ የአጋዚ ወታደሮች በአዘዞ ደባት ወረታ እና እብናት እየሰፈሩ መሆናቸው ታውቋል ።

የአጋዚ ወታደሮቹ በሰሜን ጎንደር ያለውን የህዝብ ጦር መሳሪያ ለመግፈፍና ትጥቅ ለማስፈታት ዝግጅት እያደረጉ በመሆናቸው የአካባቢው ህብረተሰብ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ለኢሳት መረጃውን ያደረሱት የነጻነት ሃይሎች ጥሪ አቅርበዋል ። ህዝቡም ለነጻነት ሃይሎች ድጋፍ በማድረግ በአጋዚ ወታደሮች ላይ ጥቃት ከማድረስ ጀምሮ በመረጃም እንዲተባበር ጥሪ ቀርቧል ።


ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ የተነሳውን የህዝብ ትግል መቋቋም ያቃተው በህውሃት/ ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት የአካባቢውን ሰዎች በመግደልና እንዲሰደዱ በማድረግ ከፍተኛ በደል ሲፈጽም መቆየቱ ይታወሳል ። ትግሉ ግን ከመድከም ይልቅ እየጠነከረ በመምጣቱ የተበሳጨው የህውሃት አገዛዝ የወታደር ክምችቱን ቢያጠናክርም ::

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: