አቃቢያን ሕግ ዶ/ር መረራ ጉዲና ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ እንደማይቀበሉት ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ

የኢትዮጵያ አቃቢያን ሕግ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ እንደማይቀበሉት ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ።
የፌደራል አቃቤ ሕጎች ማክሰኞ ሰኔ 13/ 2009 ለፍርድ ቤት ባቀረቡት የተቃውሞ አቤቱታ ዶ/ር መረራ ጉዲና ክሳቸው ከኢሳትና ኦኤምኤን ተለይቶ የሽብር ክሳቸው በሌላ መታየቱን እንደማይቀበሉ ገልፀዋል።
ዶ/ር መረራ ጉዲና በአቃቤ ሕግ የቀረበውን በርካታ ክሶች ከሽብርተኛ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም በሚል በጠበቆቻቸው አማካኝነት ከአንድ ወር በፊት ተቃውመው ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበው ነበር።
ስለዚህም በእሳቸው ላይ የቀረበው ክስ ከኢሳትና ከኦኤምኤን ተለይቶ እንደታየላቸው ያቀረቡትን መልስ አቃቤ ሕግ የሚቃወም መሆኑን ዛሬ ለፍርድ ቤት ባቀረበው መልስ አስታውቋል።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና የቀረበባቸው ክስ ቀሪ እንዲደረግና የዋስ መብታቸው እንዲከበር ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።
ዶ/ር መረራ ጉዲና ከአርበኞች ግንቦት 7 መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ከኦ ኤም ኤን ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀዋር መሐመድ ጋር ተያያዥነት ያለው የሽብር ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ከተጠረጠሩ ጀምሮ ያለዋስትና እስካሁን በእስር ላይ ይገኛሉ።
የዶ/ር መረራ ጉዲና መታሰር ተከትሎ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማትና የአውሮፓ ሕብረት የተቃውሞ መግለጫ በማውጣት በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በአስቸኳይ እንዲፈታቸው ጥሪ ቢያቀርቡም እስካሁን ምላሽ አላገኙም።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: