ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ተከሰው በእስር የነበሩ ስድስት ሰዎች ከተከሰሱበት ክስ ነፃ ተባሉ

ከሽብርተኞች ጋር በመገናኘት፣ አሸባሪ ለሆነው የኢሳት ሪዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኞች ጋር ቃለ መጠየቅ በመስጠት” በሚል ክስ በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ ስር ከሚገኙት ተከሳሾች መካካል ዛሬ ሰኔ 9/2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት ፍርድ ቤቱ ሰባቱን ተከላከሉ ሲል የሚከተሉትን ስድስቱን በነፃ ለቋቸዋል።
***
1ኛ. 1ኛ ተከሳሽ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን
2ኛ. 4ኛ ተከሳሽ አቶ አወቀ ሞኙ ሁዴ
3ኛ. 8ኛ ተከሳሽ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ
4ኛ. 10ኛ ተከሳሽ አቶ ታፈረ ካሳሁን
5ኛ. 13ኛ ተከሳሽ አቶ እንግዳው ባዩና
6ኛ. 15ኛ ተከሳሽ አቶ አግባው ሰጠኝ ናቸው።

ፍርድ ቤቱ በዚሁ የክስ መዝገብ ተከሳሽ የነበሩትን 5ኛ፣ 6ኛ ና 7ኛ ተካሽሽን አቶ ዘሪሁን በሬ ፣ አቶ ወርቅየ ምስጋናው እና አቶ አማረ መስፍን ከዚህ በፊት ነፃ መልቀቁ ይታወቃል። ይሁን እንጂ አስራ አምስተኛ ተከሳሽ የሆነው የሰሜን ጎንደር የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የነበረው አግባው ሰጠኝ በነሐሴ 28/2008. ዓ.ም በቂሊንጦ እስር ቤት በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ “የሴራው አቀናባሪ ናችሁ” በሚል ከተከሰሱትና በመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ የክስ መዝገብ ክሳቸውን ከሚከታተሉት አንደኛው ስለሆነ ዛሬ ከክሱ ነፃ ቢሆንም ከእስር ግን አይለቀቅም። በዚሁ የክስ መዝገብ ውስጥ በገቡበት ክስ ነፃ ተብለው ከቂሊንጦው እሳት ጋር በማያያዝ ዳግም እንዲታስሩ ከተደረጉት ውስጥ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ይገኙበታል። ዛሬ በዋለው ችሎት ፍርድ ቤቱ ተከላከሉ ያላቸው ሰባት ተከሳዮች አቶ በላይ ሲሳይ፣አቶ አንጋው ተገኝ ፣ አቶ ቢሆነኝ ፣ አቶ አትርሳው ፣ አቶ አለባቸውና አቶ አባይ ዘውዱ ናቸው።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: