ህወሀት/ወያኔና ቤተ አማራ ምንና ምን ናቸው ( በአሰግድ ታመነ )

በቅንጅት መፍረስ ጊዜ በሁለት ጎራ ተከፍለው የወያኔን የፖለቲካ ቁማር የሚጫወቱ ቡድኖች ነበሩ:: የኃይሉ ሻውል ደጋፊ ነን የሚሉ እና የፕ/ ብርሃኑ ነጋ ደጋፊ ነን የሚሉ::

እነዚህ ግለሰቦች ከዚህ በፊት በምንም የፖለቲካ ተቃውሞ ውስጥ ያልነበሩ ያልተሳተፉ ሲሆኑ በስርሀቱ ድጋፍ እየተደረገላቸው የሚንቀሳቀሱ አላማቸው የትግሉን አቅጣጫ ከወያኔ ላይ አንስቶ እርስበርስ እንዲሆን ማድረግና ሕዝቡም ጠንካራ በሚላቸው ተቃዋሚዎች ላይ እምነት እንዲያጣ ማድረግ ነበር ታድያ እነዛ ሰዎች አሁን የት እንዳሉ የሚያውቅ የለም እንደጉም በነው ጠፉ።
በኦሮሞና በወልቃይት የማንነት ጥያቄን ተከትሎ በተፈጠረው ህዝባዊ ተቃውሞ አንድነቱንና ህብረቱን ያሳየበት ወቅትም ነበር::

በተለይ ኢሳት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ስለህዝቡ ንቅናቄ በቂ የሆነ መረጃና ድጋፍም ያደርግ እንደነበር ይታወቃል።

እንዲሁም አርበኞች ግንቦት ሰባት ከሚያራምደው ሁለገብ ትግል መርህ ጋር በዚህ የህዝባዊ ነውጥ ላይ ብንቀበልም ባንቀበልም ተሳታፊ ነበር። በትጥቅ ትግሉም ቢሆን የወያኔን ሰራዊት ከማጥቃት አልቦዘነም ።

ይህን የሚያቀው ወያኔ/ህወሀት ኢሳትንና አርበኞች ግንቦት 7 ን እስካላጠፋ ድረስ ህልውናው አስጊ እንደሚሆንበት ተገንዝቧል።

በዚህም ምክንያት ወያኔ ህወሀት አዲስ ስልት ይዞ መቅረቡም ታውቋል ከዚህ በፊት አርበኞች ግንቦት 7 ን የአማራ ድርጅት ነው ብለው እንዳልተናገሩ አሁን ደግሞ አማራን ለማጥፋት የሚታገል ድርጅት ነው የሚሉ ለአማራ ተቆርቃሪ የሚመስሉ ግለሰቦች ፕሮፋይላቸው የማይታወቅ አድራሻ የሌላቸው ከዚህ በፊት ታይተውም ሆነ ሲንቀሳቀሱ የማይታወቁ ለአማራ ተቆርቃሪ የሚመስሉ የበግ ለምድ ለባሾች ነገር ግን አማራን ለወያኔ አሳልፈው እየሰጡ የህዝቡን የመከራ ጊዜ የሚያስረዝሙ በዝተዋል።

በእውነት ወያኔን ለመጣል ሳይሆን በህዝብ ዘንድ መለያየትን መፍጠርና ወያኔን እየተፋለመው ያለውን ለህወሀት የእግር እሳት ሆኖ እያቃጠለው ያለውን ኢሳትንና አርበኞች ግንቦት 7 መሳደብ ብሎም የህዝብ አመኔታ ማሳጣት ነው ግባቸው ።
ሀብታሙ አያሌው እንደነገረን በአስር ሺ የሚቆጠሩ የፋሺስት ወያሄ ህወሃት አፈቀላጤዎች በውጪ አለም ለዚሁ ስራ ተሰማርተዋል ። እነማን ናቸው ¨ ህዝቡ ሊመረምር ይገባል።
እንደኔ እይታ አርበኞች ግንቦት7  ለመላው የኢትዮጵያን ህዝብ ከተጫነበት የባርነት ቀንበር ነፃ ለማውጣት በበረሀ ህይወታቸውን እየገበሩ ይገኛሉ ። ከሞቀ ቤታቸው ቤተሰባቸውን ጥለው ህይወታቸውን እየገበሩ ያሉት ለኔም ላንተም ላንቺም ለናንተም ለሁላችንም የተከበረችና አንድነቷን የተጠበቀን ሀገር ለማቆየት ነው።

ታድያ አርበኞች ግንቦት7ን  የአማራ ጠላት አድርጎ መፈረጅና ከወያኔ የባሰ እያሉ አፍን መክፈት ለህዝባችን ይጠቅመዋል?

ባሁኑ ሰሃት የወያኔ/ህወሀት ቀንደኛ ተቃዋሚ ሆኖ የቀጠለው አርበኞች ግንቦት 7 ብቻ ነው። ሌሎች ጠንክረው እየወጡ የነበሩትን ፓርቲዎችማ ቅንጅት፥ አንድነት፥ ሰማያዊ እንዳፈራረሳቸው የቅርብ ግዜ ትውስታችን ነው።

ታዲያ ወያኔን እየታገሉ ያሉትን ጥፉ ሙቱ ምናምን እያሉ የሚሳደቡት ቤተ አማራ ነኝ ባዮች ህውነት ኢሳት የአማራ ጠላት ሆኖባቸው ነው?

አርበኞች ግንቦት 7 ከወያኔ የባሰ ነው የሚሉት እውነት እንደሚሉት ሆኖ ነው??

ነገርግን ከህወሀት ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው አፋቸውን በኢሳት ላይና በአግ7 በማድረግ የህዝብ አመኔታን በማሳጣት ትግሉን ማኮላሸት ነው ትልቁ ግባቸው። በመሆኑምና ይህም ሊሳካ የሚችለው በትግራይ ስም  በኦሮሞም ስም ሳይሆን ህዝቡ ሊቀበለው የሚችለው በአማራ ስም ለአማራው ብቸኛ ተቆርቋሪ በመምሰል ስናንጫጫቸው ነው በሚል የተጠነሰሰ የወያኔ ህወሀት አዲስ ስልት ነውና እንጠንቀቅ።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: