ኢትዮጵያ እና ሱዳን በድንበር ጉዳይ ጎንደር ውስጥ ስብሰባ ተቀምጠዋል

ኢትዮጵያ እና ሱዳን በድንበር ጉዳይ ጎንደር ውስጥ እየተወያዩ እንደሚገኝ ተጠቆመ፡፡ ውይይቱን ለማካሔድም ከሱዳን በኩል ከሰሜን ጎንደር ድንበር ጋር
አጎራባች ከሆኑ አራት የገዳሪፍ ግዛት የድንበር ዞኖች የተውጣጡ የልኡካን ቡድን አባላት ትላንት ጎንደር መግባታቸው ታውቋል፡፡ እንደዚሁ በሰሜን ጎንደር
በኩል ደግሞ የዞኑ አመራሮች ስብሰባው ላይ ተገኝተዋል፡፡


ሱዳን እና ኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች የድንበር ግጭቶች ውስጥ ገብተው የነበረ ሲሆን፣ በተለይ ደግሞ ከሱዳን የሚነሱ ኃይሎች ድንበር ጥሰው
በመግባት የአማራ ክልል ገበሬዎችን ሰብል አውድመው ሲወጡ ቆይተዋል፡፡


ይህ ድርጊት በተደጋጋሚ መፈጸሙን ተከትሎ ገበሬዎቹ ለክልሉ መንግስትም ሆነ ለፌደራሉ መንግስት አቤት ቢሉም ምንም ዓይነት መፍትሔ ሳያገኙ ብዙ
ጊዜ ተቆጥሯል፡፡ በአንድ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በፓርላማ ጥያቄው ተነስቶላቸው፣ ለሱዳን ወግነው ሲከራከሩ እንደነበር
አይዘነጋም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ጥፋተኞቹ የኛ ገበሬዎች ናቸው፡ የሰው ድንበር ጥሰው በመግባት ጥቃት የፈጸሙት፡፡›› ሲሉ እጅግ አስነዋሪ ንግግር
ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡


ይህን መሰል የድንበር ጉዳዮችን ለመፍታት በተለያዩ ወቅቶች ሙከራ ቢደረግም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ዛሬ የተጀመረው የሁለቱ ሀገራት ውይትትም
በሱዳን የበላይነት ሊጠናቀቅ ይችላል የሚል ስጋት አሳድሯል፡፡

ሱዳኖች ‹‹በሰሜን ጎንደር በኩል ሁለቱን ሀገራት የሚያዋስነው መሬት የኛ ነው›› የሚል ስሞታ ማቅረብ ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡

ምንም እንኳን የመሬቱ ትክክለኛ ባለቤት ኢትዮጵያ ብትሆንም፣ በመንግስት በኩል ግን ምንም ዓይነት ወገናዊ ስሜት
እንደማይንጸባረቅ ለመመልከት ተችሏል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ሱዳን የምታነሳው የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ትክክለኛ ነው ብሎ ያምናል፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: