የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ በአቶ ዮናታን ተስፋዬ የጥፋተኝነት ብይን ማስተላለፉ ተነገረ

የፈደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩን በእስር ላይ ሆኖ ሲከታተል የነበረው የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላለፈ፡፡አቶ ዮናታን ተስፋዬ የሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተበት በፌስ ቡክ አመጽ ቀስቃሽ መልክቶችን አስተላልፈሃል በሚል ነው፡፡ተከሳሹ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ያስተላለፋቸው መልክቶች ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ህገ መንግስታዊ መብቴን በመጠቀም እንደሆነና መልክቶችም አመፅ ቀስቃሽ እለመሆናቸውን፣ በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ተቃውሞ በመልካም አስተዳደር ችግር እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለፓርላው በሪፖርታቸው ላይ መግለፀፃቸውን በመግለፅ ጥፋተኛ እንዳለሆነ ሲከራከር ቆይቷል፡፡ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም አቶ ዮናታን የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 አንቀፅ 6ን ተላልፈው ተገኝተዋል በማለት ጥፋተኛ ናቸው ሲል ፍርድ ሰጥቷል፡፡የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለግንቦት 17 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 አንቀፅ 6 ከ10 ዓመት እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ያስቀጣል፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: