በፍትህ ሳምንት ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በሽብር ክስ ተጨናንቆ ዋለ!!!

ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በፌደራል ዓቃቢ ህግ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው በቅሊንጦ እስር ቤት ጉዳያቸውን እየተከታተሉ ያሉት በእነ አቶ ጌታቸው መኮነን መዝገብ የተከሰሱት 13 ተከሳሾች በድጋሜ ተቀጠሩ፡፡የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በስራ መደራረብ ምክንያት በፊት በተሰጠው ቀጠሮ መሰረት አልመረመረክቱትም በማለት ለተከሳሾች ተናሯል፡፡ይህንን ተከትሎ ተከሰሾቹ በችሎቱ ያላቸውን ቅሬታ ተናግረዋል፡፡

የቀድሞ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከፍተኛ አመራር የነበረው አቶ ተስፋዬ ታሪኩ ምንድን ነው የምትፈልጉት ፍረዱብን እንጅ ፍረዱልን አላልንም ዘረኛ ቡድን ሀገሪቱን ተቆጠጥሮ ህይወታችንን አደጋ ላይ ጥሎታል ቤተሰባችን ተበትኗል፣3 ዓመት አመላለሳችሁን ተጨማሪ 3 ዓመት እንስጣችሁ እኛ እያቆሰሉን ሳናቆስል እእያደሙን ሳናደማ በሰላማዊ መንገድ እየታገልን የነበርን ሰዎች ነን በምን ብንለምናችሁ ነው የምሻለው በሚል በምሬት ተናግረዋል፡፡

አቶ አባይ ዘውዱ በበኩላቸው ችሎቱ ለስርዓቱ ተባባሪ ሆኖ እያመላለሰን ነው ዘር እየለየ እያጠቃ የፍትህ ሳምንት የሚያከብር ስርዓት በየትም ሀገር አይገኝም ብለዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም መዝገቡ መዘግየቱን እንደሚያምን ገልፆ ውሳኔ ለመስጠት ለግንቦት 23 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በእዚህ መዝገብ የተከሰሱት

መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን

አቶ በላይ ሲሳይ

አቶ አለባቸው

አቶ አወቀ

አቶ ተስፋዬ ታሪኩ

አቶ ቢሆነኝ

አቶ ታፈረ

አቶ አትርሳው

አቶ እንግዳው

አቶ አንጋው ተገኝ

አቶ አግባው ሰጠኝ

አቶ አባይ ዘውዱ ናቸው(ክሱ በእጃችን ስለሌለ ሙሉ ስማቸውን መግለፅ አልቻልንም)

በእነ ኮሚሽነር ያቆብ ሻላ መዝገብ የተከሰሱት 32 ተከሳሾች ለዛሬ የተቀጠሩት ተከሳሾች ክሱ ወደ ሌላ ፈርድ ቤት ይዛወርልን የሚል አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡ተከሳሾች ነዋሪነታችን ጋምቤላ ክልል በመሆኑ ቤተሰቦቻችን ወደሚገኙበትና የተፋጠነ ፍርድ እናገኛለን ብለን ወደ እምናምንበት ወደ ጋምቤላ ወይም ቤንች ማጅ ይዛወርልን ብለው አቤቱታ ማቅረባቸውን ዛሬ በችሎት ተናግረዋል፡፡ስምንት ተከሳሾች ይዛወርል የሚል አቤቱታ አለማቅረባቸው የእነሱን ህገ መንገስታዊ መብታቸውን ሊያሳጣ እንደማይገባም ተናግረዋል፡፡ተከሳሶቹ ከሶስት ዓመት በላይ ውሳኔ ሳያገኙ መመላለሳቸውንም ለችሎቱ ተናግረዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም አቤቱታውን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ በተከሰሹ ስድስት ተከሳሾች ላይ ምስክር መሰማት ተጀመረ

ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ንግስት ይርጋን በትራንስፖርት ችግር አላቀረብኳትም ብሏል፡፡

በ2008 ዓ.ም በአማራ ክልል በጎንደርና ጎጃም የተነሳውን ተቃውሞ አስተባብራችሁዋል ንብረት እንዲወድም አድርጋችሁዋል በሚል የሽብር ክስ ከተመሰረተባቸው ስድስት ተከሳሾች ውስጥ በሶስተኛ ተከሳሽ አቶ ቴዎድሮስ ተላይ ላይ ዓቃቢ ህግ ምስክሮቹን አሰምቷል፡፡ ቀሪ የዓቃቢ ህግ ምስክሮች መቅረባቸውን ለመጠባበቅና ከቀረቡ ለመስማት ለግንቦት 15 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በእዚህ መዝገብ የተከሰሱት

1. ንግስት ይርጋ

2. አለምነው ዋሴ

3. ቴዎድሮስ ተላይ

4. ያሬድ ግርማ

5.በላይነህ አለምነህ

6.አወቀ አባተ ናቸው፡፡

በእነ አብዲ አደም መዝገብ የተከሰሱ ስድስት ተከሳሾች የክስ መቃወሚያ አቀረቡ፡

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባላትን ጨምሮ በፌደራል ዓቃቢ ህግ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው ስድስት ተከሳሾች የክስ መቃወሚያቸውን አቅረበዋል፡፡ችሎቱም ዓቃቢ ህግ በመቃወሚያው ላይ የሚያቀርበውን መልስ ለመጠባበቅ ለግንቦት 14 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: