ጥቂት ስለአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊ አርበኛ ሃና – ከጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

የማህሌትንና የኤዶምን ከህወሀት ማጎሪያ እስር ቤት ነጻ መሆን ውስጤ የፈጠረውን ደስታ እያጣጣምኩ እያለ ድንገት በትዝታ አምስት ወራት ወደ ሁዋላ ሄድኩኝ- -ከኤርትራ በረሃ:: ይህቺን ኢትዮጵያን ከህወሀት እስር ቤት ነጻ ለማውጣት ብረት ያነሳችውን እህታችንን ላስተዋውቃችሁ::
አርበኛ ሀና ትባላለች:: የ23 ዓመት ወጣት ናት:: የአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊ ወታደር ስትሆን በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ተሳትፋለች:: በኤርትራ በረሃ ስማቸው ከጀግንነት ጋር ከሚነሳላቸው አርበኞች መሃል ሀና ግንባር ቀደም ናት:: ስሟ በአርበኞች መንደር ገኖ ይነሳል::
………አንድ ጊዜ ላይ እንዲህ ሆነ::

ሀና የምትገኝበት ወታደራዊ ክፍል ግዳጅ ይሰጠዋል:: እስከ 30 የሚጠጋ አርበኛ የሚገኝበት ይህ ቡድን የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጦ በመግባት በአንድ የህወሀት ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽሞ የመመለስ ግዳጅ ተሰጥቶት ይሰማራል:: ሀና መትረየሷን ታጥቃለች:: ጠዋት ከመነሻቸው ወደ ኢላማ ቦታው ገሰገሱ:: እንደታቀደው ድንገተኛ ጥቃቱ ተሰንዝሮ የታሰበውን ጉዳት አድርሰው ወደ ካምፓቸው ሊመለሱ እያለ ድንገት በህወሀት ሰራዊት ይከበባሉ:: ምን ይደረግ? ብዙ ቁጥር ያለውንና እስከአፍንጫው የታጠቀውን የህወሀት ሰራዊት መክቶ ወደ ካምፕ መመለስ ከባድ ሆነ:: የዚህን ጊዜ ነበር አንድ ጀግና ታሪክ የሰራችው:: ….ሀና::

መትረየሷን መተረች:: ገዢ መሬት ያዘች:: ቦታዋን አስተካከለች:: ….እሷ መስዋዕት ሆና የትግል ጓዶቿን ልታስመልጥ ወሰነች:: ምሽት እየመጣ ነው:: ጓዶቿ ተስናበቷት:: ዳግም በህይወት እንደማያገኟት ታወቃቸው:: …እሷ መትረየሷን ወደ ህወሀት ሰራዊት ለቀቀችው:: ለጓዶቿ ሽፋን በሚሰጥ ስልት አስካካችው:: …ፍልሚያው በአንዲት ሀና እና በህወሀት ሰራዊት መሃል ሆነ:: የሀና መትረየስ ያስካካል:: ጓዶች በዚያ ሽፋን ወደ ጦር ካምፓቸው እየተመለሱ ነው:: የሀና የመትረየስ ድምጽ እየራቃቸው ነው:: እነሱ ይተርፉ ዘንድ አንድ አርበኛ መስዋዕት መሆን ግድ አለ:: በተሰጣቸው ግዳጅ ውጤታማነት እየተደሰቱ የሃናን መስዋዕትነት እያወደሱ ከካምፓቸው ምሽት ላይ ደረሱ:: በአርበኞች መንደር ህይወት እንዲህ ናት:: ታጋይ ይሰዋል:: ትግል ይቀጥላል::

…እኩለ ሌሊት ከመድረሱ በፊት ነው:: ጭው ካለው የኤርትራ በረሃ አንድ ሰው ወደ አርበኞቹ መንደር ከኢትዮጵያ ድንበር አቅጣጫ ይገሰግሳል:: በርቀት የተመለከቱት የሌሊት የካምፕ ተረኛ ዋርዲያዎች(ጠባቂዎች) መሳሪያቸውን አስተካክለው ጣት ከቃታ አገናኝተው ወደ ካምፑ እየገሰገሰ ያለውን ሰው ይጠብቃሉ:: ውድቅት ሌሊት ስለነበር ማንነት መለየት አልተቻለም:: የሚገሰግሰው ሰው እየቀረበ ሲመጣ ዋርዲያዎቹም ኢላማቸውን አስተካክለው እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጁ:: ….ሰውዬው ቀረበ:: ሴት ናት::ሃና:: ዋርዲያዎቹ አላመኑም:: የዕለቱን የይለፍ ቃል ጠየቋት:: መለሰችላቸው:: ደክሟታል:: ተአምር የሚያሰኘው ከዚይ የህወሀት ሰራዊት ከበባ ማምለጧ አይደለም:: ሁለት የጦር መሳሪያዎችንም ማርካ ተሸክማለች:: ከሷ መትረየስ ጋር ሶስት:: ዋርዲያዎቹ በሚያዩት ነገር ተደንቀዋል:: በአርበኞች መንደር ስለ ሃና እርም ወጥቷል:: ጉድ ተባለ::

….ሃናን በአካል ሳገኛት በጣም ቁጥብ ነበረች:: ብዙ አትናገርም:: ታሪኳን እንድታጫውተኝ ያደረኩት ጥረት አልተሳካም:: ሲበዛ ዝምተኛ ናት:: ጀግና አይናገርም::
…ሃና ከሰሞኑ ውጊያዎች በአንዱ እንደተሰለፈች እገምታለሁ:: ልብን በኩራት በሚያሞቀው ጀግንነቷ ሁሌም አስታውሳታለሁ:: የጣይቱ ልጅ!!!!!

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to ጥቂት ስለአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊ አርበኛ ሃና – ከጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

 1. Mamush Daniel says:

  አቶ መሳይ መኮንን በመሰረቱ ስለ ጦርነትና ውትድርና ወይም ሽምቅ ውጊያ ያለው ዕውቀት ለተረት ተረት የማይበቃና ባዶ ነው። ይህን ባዶነቱን በዚህ ጽሁፍ ላይም ማየት ይቻላል።
  በዚህ ተረት ውስጥ ወደ 30 የሚሆኑ የአርበኛ ተዋጊዎች ብዙ ቁጥር ባለውና እስከ አፍንጫው በታጠቀ የህወሀት ሰራዊት መከበባቸውን ይነግረናል። ሃና ብቻዋን መከታ ሆናቸው ሌሎች አመለጡ፣ ሃናም አመለጠች ይለናል። ሃና ይህን ማድረግ የምትችለው ብዙ ቁጥር ያለውና እስከ አፍንጫው ታጠቀ የተባለውን የህወሀት ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ከደመሰሰች ብቻ ነው። ነገሩ ሃቅ ቢሆን ኖሮ ትልቅ ዜና የሚሆነው የሃና ማምለጥ ሳይሆን የዚህ ሁሉ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ሰራዊት በሃና መደምሰሱ ነው።
  አቶ መሳይ ከዚህ በፊት አስመራ ደርሶ ወደ አሜሪካ ሲመለስ በኤርትራ በረሃ ውስጥ የመሸገው ግንቦት ሰባት ጦር ብዛት በመቶ ሽህ የሚገመት ነው ብሎ ኢሳት ላይ የተናገረ ግለሰብ ነው።
  በዚህ የአቶ መሳይ ቁጥር መሰረት ግንቦት ሰባት ለአንድ ተዋጊ ራሽን በቀን 20 ናቅፋ ቢያወጣ የአንድ ቀን ጠቅላላ የራሽን ወጭው ከሁለት ሚሊዮን ናቅፋ በላይ ይሆናል ማለት ነው። በወር ከ60 ሚሊዮን በላይ፣ በዓመት ደግሞ ከ720 ሚሊዮን ናቅፋ በላይ ይደርሳል። ለዓመታትስ…… የአቶ መሳይ ውሸት እዚህ ላይ የደርሳል…..ሰው ምን ይለኝ ማት ያልጎበኘው የህጻናት ለከት የሌለው ውሸት….

  Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: