በባህርዳር ሁለተኛው ማስጠንቀቂያ ፍንዳታ ተሰምቷል

በባህርዳር ሁለተኛ ማስጠንቀቂያ የቦንብ ፍንዳታ በቀበሌ 14 መውጫ ላይ ትናንት ሚያዚያ 19 /2009 ዓ.ም ከምሽት 3 ሰዓት አካባቢ ፈንድቷል። ወደ ባህርዳር ዩንቨርስቲ ይባብ ካምፕስ ድባንቄ መድሀኒዓለም ቤተክርስቲያን አካባቢ በፀሀይ ቀለም ፍብሪካ ባለቤት ንብረትነት ባለ የነዳጂ ማደያ ስፍራ አካባቢ የተጣለው ቦንብ የ1 ሰው ህይወት ህልፈት ሲያደርስ የ4 ሰወች ከባድና ቀላል ጉዳት አድርሷል። በነዳጂ ማደያው ዘበኛ ላይ ከባድ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ሆስፒታል ውስጥ በህይወትና በሞት መካከል እንደሚገኝ ተረጋግጧል። ይህ የማስጠንቀቂያ ፍንዳታ በተጨማሪም በነዳጂ ማደያው አስተናጋጆች ላይ ቀላልና ከባድ ቁስለኛ ያደረገ ሲሆን የ1 ወጣት ማማሩ የተባለ የማደያው ሰራተኛ በአጋጣሚ ህይወት ለህልፈተ ሞት ዳርጓል።
የህወሓት አምባገነን ቡድን በባህርዳር ከተማ በሚያዚያ 21 ያሰበው ኮንሰርት በህዝቡ ተቀባይነት እንደሌለውና በኮንሰርቱ ለተዘጋጀው ድግስ የተጋበዙ ድምፃዊያንን አንፈልግም እንዳትመጡ ፤ በዚህ ህዝባዊ የነፃነት ትግል ከህዝብ ጎን ሁናችሁ የህዝብ አጋርነታችሁን አሳዩን በማለት ተደጋጋሚ መልዕክትና ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ይታወቃል። ይህ በወንድሞቻችን ደም የተጠመቀው የዳሽን ቢራ ተቀያሪ ስም ባላገሩ በማለት ለማስተዋወቅ የተዘጋጀው ኮንሰርት ካልተሰረዘ ጥቃቱ በህወሓት ንብረቶች በሙሉ ና የገቢ ምንጮች ጠቅላላ እንደሚቀጥል ና ወደ ኮንሰርቱ ለምትገቡ ወገኖች ቆም ብላችሁ እራሳችሁን እንድትመረምሩ ጥሪ የቀረበ ሲሆን በሚደርሰው አደጋ ሀላፊነቱ የራሳችሁ እንደሚሆን ምንጮች ይናገራሉ።
በተያያዘ በህወሓት አፍኝ ወንበዴ ቡድን ወጣቶችን በማፈንና በማሰር የተጠመደ ሲሆን እስካሁን በጎንደርና በባህርዳር ብዙ ወጣቶች ታፍነው እንደታሰሩ ለማወቅ ተችሏል። ህወሓት እንደ እሳት ጂራፍ የሚገርፈው ወቅታዊ መረጃ ለህዝብ ሲደርስ ነውና እያንዳንዱን የትግል እርምጃወች ለማፈን የሚያደርገው ጥረት ከፍተኛ ነው። ከብዙ በጥቂቱ ከህዝብ ለማሸሽ የሚያደርገው መንፈራገጥ መረጃወች እንዲታፈኑ ቢያደርግም ሁሉም ነፃነት ፈላጊ በተገኘው አጋጣሚ መረጃወችን በመለዋወጥ ህወሓትን እራቁቱን እናስቀር ዘንድ በተባበረ ክንድ ለትግል እንነሳ።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: