የወያኔ ስርሃት በቆሼ ለተጎዱ ቤተሰቦች ከተሰበሰበው ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ታቅፎ ከመቀመጥ በስተቀር ከአደጋው ለተረፉት ሰለባዎች ድንቡሎ የሰጠው ነገር እንደሊለ ተጎጂዎቹ በምሪት ገልጸዋል።

ሰባት የቢተሰብ አባላቱን ያጣው ቲዲ-“ለቀብር ማስፈጸሚያ ተብሎ የተሰጠን አስር ሺህ ብር በስተቀር ምንም ያየነው ነገር የለም” ሲል ለቪኦ ኤ ተናግራል ሆኖም ቲዲ ” እጅግ አዛኝ እና ሩህሩህ በሆነው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ያልተቃረጠ ጥረት ነው አሁን እየኖርን ያለነው። ሕዝቡ ለሰጠን ፍቅርና ድጋፍ ከፍተኛ የሆነ ምስጋና ነው እምናቀርበው..” ሲልም መልሳል።

ከትናንት በስቲያ በኮልፊ ቆሺ ሰፈር ህይወታቸውን ያጡ ከ113 በላይ ኢትዮጵያውያን የ40 ቀን መታሰቢያ እለት ነበር። አደጋው ከደረሰ 40 ቀንም በሃላ መንግስት ከፈጥኖ ደራሽ ኢትዮጵያውያን የተለገሰውን ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ታቅፎ ከመቀመጥ በስተቀር ከአደጋው ለተረፉት ሰለባዎች ድንቡሎ የሰጠው ነገር እንደሊለ ተጎጂዎቹ በምሪት ገልጸዋል። እንደ አቶ ባዪ አገላለጽ “መንግስት ለምንድነው እኛን እንደዚህ እንደጠላት የሚያየን፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በደረሰብን አደጋ ልቡ ተንክቶ ያደረገልንን ችሮታ መንግስት ሰብስቦ ይዞ መቀመጥ ለምን አስፈለገው” ሲሉ በምሪት ይናገራሉ።
ባለፈው መጋቢት ወር ውስጥ በኮልፊ ቆሺ ሰፈር በቆሻሻ “መናድ” ከመቶ በላይ [አንዳንዶች ቁጥሩን 200ያደርሱታል]ወገኖቻችን ህይወት በአሰቃቂ ሁኒታ ማለፉ ይታወቃል። በአደጋው ማግስትም ኢትዮጵያውያኑ ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብና ድጋፍ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ [ሺክ አላሙዲን 40ሚሊዮን የአማራ ክልል 5ሚሊዮን] መዋጣቱ ይታወቃል። የታዋጣው ገንዘብ በአዲስ አበባ መስተዳድር እጅ እንዳለም ታውቃል። መስተዳድሩ በበኩሉ የአደጋው ሰለባዎች በኮሚቲ ተዋቅረው የማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ክፍል በኩል መረዳት እንደሚችሉ ገልጻል። በዚህ የማቾችን 40ኛ ቀን ለመዘክር በታሰበበት እለት የቪ ኦ ኤ ጋዚጠኛ የአ.አ.መስተዳድር ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የሆኑትን ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስን በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር ለሁለት ሳምንት ያህል ያደረገው ሙካራ እንዳልተሳካለት ገልጻል። “መንግስት እኛን እንደጠላት አይየን-ማድረግ ያለበትን እና ህዝብ የረዳንን እግዚአብሒርን ከፈራ ይርዳን-ይስጠን..”ሲሉ ይመጸናሉ። “እግዚአብሒርን ይፍሩና እኛን እንደሰው ይዩን-ያስተናግዱንም.” ይላሉ አቶ ባዪ። “ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ቀበሊው መጋዘን ተጠራን-ከወገኖቻችን የተላከልን ዘርፈ ብዙ የእርዳታ አይነት ተከምራል። ጫማና ልብስ ምረጡ ነገ እንሰጣችሃለን ብለው ሲያስመርጡን ዋሉ-በማግስቱ ግን ሃሳባቸውን ቀይረው አንሰጣችሁም አሉ። ለምን ስንል ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው አሉን” ብላል ሰባት ቢተሰቡን ያጣው ወጣቱ ቲዲ።

ኢትዮጵያውያን በአደጋው ማግስት ከያሉበት እየተረባረቡ የረዱት መንግስት ተብዪው በተበዳይ ስም ሰብስቦ እና በመጋዘን ቆልፎ የተስፋ ወሪ ብቻ ሊነፋ ነውን? ለምንድነው በተበዳይ ቢተሰብ ላይ አላስፈላጊ ቢሮክራሲ በሉት የስርቆት ሀሳብ -ወይም የክህደት ሀሳብ በባለስልጣናቱ እየታሰበ እና እየተፈጸመ ያለው?
እነዚህ የአደጋው ሰለባዎች ከወገኖቻቸው የተቸራቸውን እርዳታ በአፋጣኝ ለማግኘት የግድ የትግራይ ተወላጆች መሆን አለባቸው?

በኢትዮጵያ ውስጥ የዚግነት መብቱ ተከብሮለት በአግባቡ ለመኖር ዋናው መስፈርት ከትግራይ መወለድ ወይም ከፋሽስቱ ስርዓት ጋር መሞዳሞድ አስፈላጊ በሆነበት ዘመን የእነዚህን ወገኖቻችንን እንባ እንዲት አድርገን ነው ማበስ እሚቻለን ብለን እራሳችንን ከመጠየቅ አንቆጠብም። ከዚህም አሳፋሪ እና ምግባረቢስ እርምጃቸው ምክያት የተነሳ ባለስልጣናቱ በጉዳዩ ላይ ለመገናኛ ብዙሃን ለመነጋገር ፍቃደኛ መሆን ያለፈለጉት። ምንድነው እየሸሹ ያሉት?

በፓርቲ ቁጥጥር ስር ያለው ኢቢሲ-ፋና እና መሰል መገናኛዎች መንግስት ለተጎጂዎቹ የአንድ ሚሊዮን ብር ቢት መስሪያ፣መሪት በነጻ ሰጥታል ሲሉ ከበሮ ደልቀው ነበር። ለአንድ ዓመት የቢት ኪራይ፣ላማች ከ40-100ሺህም እንደታደለ ገልጸው ነበር።
ሆኖም አባባሉ ላም አለኝ በሰምይ እንደሆነባቸው ነው የአደጋው ሰለባዎች እየተናገሩ ያሉት።
“እኛም እንደ እናንተ በወሪ ደረጃ በቲቪ እና ሪዲዮ ሰምተናል-የአንድ ሚሊዮን ቺክ አላየንም ወረቀት ግን ተሰጥቶናል…የካርታውም ጉዳይ ተመሳሳይ ነው.መሪቱን አስረክበው ካርታ አልሰጡንም ፣ግን ይሂ የተሰጣችሁ መሪት ካርታ ነው ብለው ወረቀት ሰጥተውናል። ” ይላሉ ቲዲና አቶ ባዪ-
የመሪት ተመሪነት አልባ የመሪት ካርታ ወርቀት አድሎ መሪት ሰጥቻለሁ ብሎ መለፈፍ በእውነት ከሆነ በስቃያቸው ላይ መሳለቅን እየፈጸመ እንደሆነ ነው እምንረዳው። የአንድ ሚሊዮን ሆነ የአንድ ሺህ ብር ችሮታ የሚሰጠው ወይ በካሽ አሊያም በቺክ ነው እንጂ በተራ ወረቀት ቁጥር ጽፎ በመስጠት ነውዲ? ለምን እቁጩን አልሰጣችሁም ምን ታመጣላችሁ አይላቸውም? ህወሃታውያን ዘርፈው በማፍጠጥ የተካኑ ናቸው። ለምንድነው ሁለተኛ ሞት፣ሁለተኛ ስቃይ እንዲሰቃዩ የተደረገው?

ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያዊ ስብዓና ህወሃት ጠቅልላ የቀበረችው ያህል ህዝባችንን በለከት የለሽ ደረቅ ፕሮፖጋንዳ እና ገደብ የለሽ ጭካኒ እያሰቃየች ነው።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: