ወያኔ የመንግስት ባንኮችን በመላው አገሪቷ እያራቆተ ነው።

በኦሮምያና አማራ ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ በአገሪቱ የሚታየው የውጭ ምንዛሬ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ ፋብሪካዎች ድርጅቶቻቸውን እስከመዝጋት እየደረሱ ነው።
የአገሪቱን የፋይናስ ስርዓት በተገቢው መንገድ ይመራል ተብሎ የተቋቋመው ብሄራዊ ባንክ ለንግድ ባንክ ከግል ባንኮች በተለየ የሚሰጠው የዶላር አቅርቦች የግል ባንኮች ለደንበኞቻቸው በቂ የውጭ ምንዛሬ እንዳያቀርቡ በማድረጉ ባንኮቹ የህለውና አደጋ ተደቅኖባቸዋል።
አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደሌለ በተደጋጋሚ ቢናገሩም፣ እውነታው ግን ከዚህ የተለየ መሆኑን ነጋዴዎች ይገልጻሉ። የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የሚወስደው የጊዜ እርዝመት በርካታ አስመጪዎችን ተስፋ እያስቆረጠ ነው።
ቀደም ብሎ ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ሆነው የሚያገለግሉት የውጭ ገበያ፣ ቱሪዝምና እርዳታ በህዝባዊ አመጹ ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። የውጨ ገበያው ከመቼውም ጊዜ በላይ መቀነሱ፣ ከሰላምና መረጋጋት ጋር በተያያዘ በተለይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘሙ የቱሪዝሙን ገበያ በከፍተኛ ሁኔታ የጎዳው በመሆኑ፣ ለውጭ ምንዛሬ እጥረት ዋነኛ ምክንያቶች ሆነዋል።
ከወጪ ንግድ በተጨማሪ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ማስገኛ ሆኖ የሚያገለግለው በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚልኩት ገንዘብ በተለያዩ ፖለቲካዊ ምክንያቶች መቀነሱ ለችግሩ መባባስ አንድ ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል። ባለፉት 3 ሳምንታት ገዢው ፓርቲ የዲያስፖራ አባላት ቤት እንዲሰሩ ለማግባባት እና የውጭ ምንዛሬ እጥረቱን ለመሸፋፈን በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ የዲያስፖራ አባላት ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሁኔታ ቃል የተገባላቸውን መሬት በፍጥነት እና በሚፈልጉት ሁኔታ ባለማግኘታቸው እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚታየው አለመረጋጋት ስላሰጋቸውና አገዛዙን ከሚቃወሙ ከሌሎች የዲያስፖራ አባላት የሚደርስባቸውን ትችት በመፍራት ፣ ኢህአዴግ ላቀረበው ጥሪ ቀዝቃዛ መልስ እየሰጡ ነው።
በወጪና በገቢ ንግዱ መካከል ያለው ልዩነት ከ13 ቢሊዮን ዶላር በላይ እየሰፋ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።
በውጭ ምንዛሬ እጥረት ስራ ካቆሙ ድርጅቶች መካከል የተለያዩ ቆርቆሮዎችን፣ ቧንቧዎችንና የብረታብረት የእርሻ መሳሪያዎችን በማምረት የሚታወቀው ነባሩ አቃቂ ብረታብረት ኢንዱስትሪ ሆኗል። በርካታ ስራተኞችን ያቀፈው ድርጅቱ በውጭ ምንዛሬ እጥረት የተነሳ ስራውን ለማቆም በመገደዱ፣ ለሰራተኞቹ በነጻ ክፍያ እየፈጸመ ነው።
ገዢው ፓርቲ ያለውን አነስተኛ የውጭ ምንዛሬ ራሱ ለሚያስገነባቸው ፕሮጀክቶች እቃ መግዣ በማዋሉ፣ በሌሎች የግል ባለሀብቶች በሚገነቡ ፕሮጀክቶችም ላይ ተጽእኖ አሳርፏል።

bank_of_ethiopian_

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: