ይርጋለም ከተማ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ታሰሩ

በደቡብ ክልል ይርጋለም ከተማ ከ15 በላይ የፋይናንስና የማዘጋጃ ሰራተኞች በሙስና በሚል ተሰብስበው ታስረዋል።

እርምጃው የተወሰደው በቅርቡ በክልሉ የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ ነው።

የድርጅተ ሰራተኞች እንደገለጹት በሙስና የተዘፈቁት ዋናዎቹ አመራሮች ሆነው እያለ እነሱን ወደ ሌሎች ቦታዎች በማዛወር፣ ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ተራ ሰራተኞች ይዘው አስረዋል።

 

እስሩን ተከትሎ በሰራተኞች ዘንድ አለመረጋጋት መፈጠሩን ሰራተኞች ተናግረዋል።

የከተማው ከንቲባና ዋና ዋና የድርጅቱ አባላት ከአካባቢው እርቀው ወደ ሌሎች ቦታዎች እንዲመደቡ በማድረግ፣ በደሃ ሰራተኞች እርምጃ በመውሰድ ህብረተሰቡን ለመሸንገል ሙከራ እያደረጉ ነው ሲሉ ሰራተኞች በሃዘን ገልጸዋል።

ከሰአት በሁዋላ በደረሰን መረጃ ደግሞ የተያዙት ሰራተኞች ወደ ሃዋሳ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: