በደቡብ ወሎ ኩታበር የወረዳ መሥሪያ ቤቶችና የብአዴን ጽ/ቤት መቃጠላቸው ተነገረ

በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ በአንድ ግቢ ውስጥ የሚገኙት የወረዳው ምክር ቤት፣ ማዘጋጃ ቤትና የብአዴን ጽ/ቤቶች የእሳት ቃጠሎ ደርሶባቸዋል፡፡

መጋቢት 26 ለ27 ሌሊት 2009 ዓ.ም ሦስቱም በአንድ ግቢ ውስጥ ያሉ መሥሪያ ቤቶች እንዲቃጠሉ መደረጋቸውን የተናገሩት ምንጮች ሁሉም በጋራ የሚጠቀሙበት መዝገብ ቤቱ ሙሉ በሙሉ መውደሙን አሰምተውናል፡፡


ይህን ተከትሎ በኩታበር ከፍተኛ ውጥረትና መደናገጥ የተፈጠረ ሲሆን ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ግለሰቦች በጥርጣሬ መታሰራቸውን ከቦታው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአብዛኛው የወሎ አካባቢዎች ወጣቱን ማሳደድ ካልቆመ ብሎም የዐማራ ሕዝብ ሕጋዊ ጥያቄዎች መልስ እስካልተሰጣቸው ድረስ የተለያዩ ጥቃቶች በየቦታው መሠንሰራቸው የማይቀር እንደሆነ የመረጃ ምንጮችን በአጽንኦት ተነናግረዋል፡፡

በተያያዘ ዜና ዛሬ ባህር ዳር ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ከባድ ቶክስ እንደነበር ተነገረ፣፣

መብራት ሁሉ ጠፍቶ አንድ የመብራት ሀይል መቆጣጠሪያ በእሳት ተያይዞ እየነደደ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ነዋሪው ለመውጣት በጣም አስፈሪ እንደሆነባቸው ተነገረ ፣፣ ህዝቡ በድንጋጤ ውስጥ እንዳለ ተነግራል፣፣

አባይ ሚዲያ ዜና

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: