ህወሓት የፌስቡክ ወታደሮችን ለማሰልጠን ከመቀለና ሌሎች የትግራይ ከተሞች እየመለመለ ነው ተባለ

መመልመያ መስፈርት የትውልድ አከባቢ፣ ከባለስልጣን ጋር ያላቸው የዝምድና ቅርበት፣ ባጠቃላይ የፖለቲካ ታማኝነት ነው። ሰልጣኞቹ ቁሳዊ ጥቅም ያገኛሉ፣ በየደረጃው ስልጣን ይሰጣቸዋል፣ የደህንነት መስሪያቤት አባል ይሆናሉ።

ከስልጠና በኋላ … ህወሐትን የሚቃወሙ ሰዎችን (በማህበራዊ ሚድያ በኩል) ይሳደባሉ፣ ያሸማቅቃሉ። ማንነታቸውን ደብቀው አማራ ወይ ኦሮሞ በመምሰል የትግራይ ህዝብን ይሳደባሉ- የትግራይ ህዝብ ከህወሐት ጎን ለማሰለፍ። የብዕር ስም ተጠቅመው ፅንፈኛ ተቃዋሚ መስለው ፌስቡከኞችን መሰለልና ተቃዋሚ ድርጅቶችን ማፍረስ ወዘተ። ከተወሰነ ግዜ በኋላ ከትግራይ የተመለመሉ ፌስቡከኞች አማራ ወይ ኦሮሞ ስም ይዘው የትግራይን ህዝብ ሲሳደቡ እናያለን።

የሚያሳዝነው ነገር ለመሳደብ መሰልጠናቸው አይደለም። ብዙ የትግራይ ተወላጆችን መሸወዳቸው እንጂ። ትግርኛ ተናጋሪ የህወሐት አባላት ሁነው የሌላ ብሄር ተወላጆች መስለው የትግራይን ህዝብ ሲሳደቡ ብዙ የትግራይ ተወላጆች ይሸወዳሉ።

እኔ ግን እላለሁ፡ እነኚህ ልጆች ጥላቻ ሳይሆን መቻቻልን ቢሰለጥኑ፣ ስድብ ሳይሆን ሐሳብን ቢማሩ፣ ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማለያየት ሳይሆን ለማቀራረብ ቢሰሩ መልካም ነው።

ደግሞ እነዚህ ቃላት shared, retweeted, taged ወዘተ ምን ማለት እንደሆኑ አስረድዋቸው።

ከብዙ የጥላቻ ስብከት በኋላ ግን ወደኛ ጎራ መቀላቀላቸው ግድ ነው። ህወሐቶች ስድብ ያስታጥቋችኀል፣ እኛም ሐሳብ እንመግባችኀለን። በመጨረሻም ሐሳብ ያሸንፋል።

It is so!!! Abraha Desta

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: