ኢህአዴግ ካልተስተካከለ ይህች አገር በእሣት ትቃጠላለች”ሲሉ አቶ አባይ ጸሀዬ ተናገሩ

የህወኃቱ መሥራች አባይ ጸሀዬ ስብሰባ ላይ መንግስትንና አስፈጻሚዎችን በቁጣ የዘለፉበት ንግግር ኢሳት እጄ ገብታል ሲል መዘገቡ ታውቃል።
ኢሳት እንደዘገበው ከሆነ አቶ አባይ ጸሀዬ

እምነት ያጣንበት ሚኒስትር ዳግም እየተሾመ ነው :: የመንግስት አሠራር ካልተቀየረ ይች ሀገር በእሳት ትቃጠላለች።የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ጸረ ዲሞክራሲ የተጠናወተውና ጸረ ዲሞክራሲ የገነገነበት ነው ።

ይህ የኔ አስተያዪት ሳይሆን በጥቅል ተሀድሶው የደረስንበት ድምዳሜ ነው።አመራሩ እንኳን ያቀረብከውን ሹመትና በጀት አልተቀበልንህም ሊባል ቀርቶ -ጠንከር ያለ ጥያቄ ሲቀርብለት የሚያኮርፍ፣ የሚያንገራግርና አካኪ ዘራፍ የሚል አምባገነን ነው። በጥልቅ ተሀድሶው ደቡብ ላይ በርካቶችን አንስተን ሌሎችን ተክተናል።

ይህን አሠራር ከፍተኛው አመራር ላይ እዚህ ሲመጣ መተግበር ያቃተው ለምንድነው፧ ይህ ደብል ስታንዳርድ ነው!………. የሚያጠፋ አካል ይመከር፣ ይስተካከል፤ ሆኖም የማይመከርና የማይስተካከል ከሆነ የሚወገድበትና ከዚያው ፓርቲ ሌላ ግለሰብ የሚተካበት አሰራር የሚከተል ምክር ቤት ሊሆን ይገባል!!” ብለው መናገራቸው ተዘግባል::
ንግግራቸውን ኢሳት ዜና ላይ ያዳምጡ

 

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: