በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በሚገኙ 38 እስረኞች ላይ የተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አቤቱታ እንዲመረመር ተወሰነ

የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ 38 ተከሳሾች በተደጋጋሚ ሲያቀርቡ የቆዩት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አቤቱታ ምርመራ እንዲካሄድ ወሰነ።
የልብ ስፔሻሊስቱን ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ 38ቱ ተከሳሾች ባለፈው አመት በነሃሴ ወር በእስር ቤቱ ደርሶ ከነበረው የእሳት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ተደራራቢ ክስ ስር የሚገኙ ሲሆን፣ አቤቱታ አቅራቢዎቹ በተለያዩ ጊዜያት ከተፈጸመባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መካከል የምርመራ ቃላቸውን በግዳጅ እንዲሰጡ መደረጉንም ለፍርድ ቤት ገልጸዋል። ይኸው የፖሊስ ቃል በማስረጃነት እንዳይቀርብላቸው የጠየቁት ተከሳሾች በእስር ቤቱ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው እና በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲኖር መደረጉን አስረድተዋል።
የ24ቱ ተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት አቶ ወንድሙ ኢብሳ ደንበኞቻቸው በ24 ሰዓታት ውስጥ የፀሃይ ብርሃን እንዲያገኙ የሚደረገው ለ30 ደቂቃ ብቻ መሆኑን ለፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ማመልከታቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።
ከደምበኞቻቸው መካከል ሚስባህ ከድር የተባለ ተከሳሽ ደግሞ በካቴና ታስሮ እንደሚያድርና ሌሎችም ተከሳሾች በእስር ቤቱ አያያዝ ላይ ከፍተኛ ችግር እንዳለ በተደጋጋሚ ማመልከታቸውን ጉዳዩን በመመልከት ላይ የሚገኘው ፍርድ ቤቱ አስታውቋል።
በእስር ቤቱ ከሚገኙ አንዳንድ ተከሳሾች የእስልምና ተከታይ በመሆናቸው በቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር በደል እየተፈጸመባቸው መሆኑን ማስረዳታቸውንም ፍርድ ቤቱ አክሎ ገልጿል።
ይሁንና የቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር በ38ቱ ተከሳሾች እንዲሁም በጠበቆቻቸው በኩል የቀረቡትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዳልተፈጸሙና አቤቱታው የማረሚያ ቤቱን ስም ለማጥፋት ያለመ ነው ሲል ምላሽን መስጠቱን የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ አስረድቷል።
በተለያዩ ጊዜያት ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ተከሳሾች ቃል እንዲሰጡ እንዲሁም በፍርድ ቤት ሂደት ላይ እያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሚፈጸምባቸው ሲገልፁ ቆይተዋል።
ሂውማን ራይትስ ዎችን ጨምሮ በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ግለሰቦች በኢትዮጵያ በሚገኙ እስር ቤቶች ቃል ለመቀበል ስቃዮች እንደሚፈጸሙ በተደጋጋሚ እስረኞችን ዋቢ በማድረግ ሪፖርት አውጥተዋል።
ሂውማን ራይትስ ዎችን ጨምሮ በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ግለሰቦችን በኢትዮጵያ በሚገኙ እስር ቤቶች ቃል ለመቀበል ስቃዮች እንደሚፈጸሙ በተደጋጋሚ እስረኞችን ዋቢ በማድረግ ሪፖርት አውጥተዋል።
የ38ቱ ተከሳሾችን አቤቱታ ሲቀበል የቆየው ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች በግዳጅ ቃል እንድንሰጥ ተገደናል ያሉት የምርመራ ቃል በክርክር ወቅት ታይቶ ውሳኔ እንደሚሰጥበት ምላሽ መስጠቱም ታውቋል።
ተከሳሾች ይደርስብናል ያሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በእስር ቤቱ እንዳልተፈጸመ ተደርጎ ምላሽ የተሰጠበት በመሆኑ ጉዳዩ በሶስተኛ ወገን ማጣራት እንደሚካሄድበት በማስፈለጉ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በእስር ቤቱ ተገኝቶና አጣርቶ የደረስንበት ውጤት ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
38ቱ ተከሳሾች በእሳት ቃጠሎው ተጠያቂ ተደርገው ለ23 ሰዎችና 15 ሚሊዮን ብር ለሚጠጋ የንብረት ውድመት ተጠያቂ መደረጋቸውን በማስተባባላቸው ከሳሽ አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ከግንቦት 14 ቀን እስከ 24, 2009 አም አቅርቦ እንዲያሰማ ፍርድ ቤት ውሳኔም ማስተላለፉም ታውቋል።
የእሳት ቃጠሎው በእስር ቤቱ በደረሰ ጊዜ የአካባቢው ነዋሪዎችና በዕለቱ የነበረው ያልታጠቀ የጸጥታ አባል የቂሊንጦ እስር ቤት ጠባቂዎች ከእሳት አደጋው ለማምለጥ በሞከሩ ታሳሪዎች ላይ የተኩስ ዕርምጃ መውሰዳቸውን እማኝነት መስጠታቸው የሚታወስ ነው።
የእስር ቤቱ አስተዳደር ተከሳሾች የእሳት ቃጠሎው እንዲደርስ አድርገዋል ቢሉም የ38ቱ ተከሳሾቹ “ድርጊቱን አልፈጸምንም” ጥፋተኛም አይደለንም ሲሉ ለፍርድ ቤት ምላሽን እንደሰጡ ለመረዳት ተችሏል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: