የኢትዮጵያ ሶማሌ ዘጠኙም ዞኖች ሙሉ በሙሉ የድርቁ ሰለባ ሆነዋል!

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሁለት ወራት ውስጥ ባወጣቸው ተከታታይ ሪፖርቶች ምስራቅ አፍሪካ የከፋ ድርቅ መከሰቱንና ዓለም የዕርዳታ እጆቹን ለአገራቱ እንዲዘረጋ በተከታታይ ሪፖርቶቹ ተማጽኗል፡፡ እንደ በዘገባው ከሆነ ድርቁ የከፋባቸው ተጠቃሽ አገራት ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያና ኢትዮጵያ ናቸው፡፡

ከኢትዮጵያ ውጭ የተጠቀሱት መንግሥታት ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ የዕርዳታ እጃቸውን በመዘርጋት፤ በተባበሩት መንግሥታት በኩል የአውሮጳ ህብረትና ሌሎች ለጋሾች በከፋ ድርቅ ላይ ለሚገኙት አገራት ዕርዳታ እየሰጡ ናቸው፡፡ በተባበሩት መንግስታት ሪፖርት መሰረት አገራቱ በእርስበርስ ጦርነት የሚታመሱ እና በውስጥ ችግራቸው የፖለቲካ አለመረጋጋት የሚታይባቸው የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ሙስናና ብልሹ አሰራሮች የነገሰባቸው ናቸው፡፡ በመሆኑም ድርቁ ዜጎቻቸውን ለስደት ከመዳረግ አልፎ አገራቱን ለከፋ ማህበራዊ ቀውስና ለውስጥ አለመረጋጋት እየዳረጋቸው እንደሆነ ሪዘገባው ያመለክታል፡፡

“(ረሃቡ) በራስ አቅም የሚፈታ ችግር ነው” ህወሃት

ከዜጎች ችግር በላይ ለአገር ገጽታ ግንባታ የሚጨነቀው ህወሃት/ኢህአዴግ ኃላፊነት በሚሰማዉ መልኩ ከዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመንቀሳቀስ ድርቅ በተከሰተባቸው የኢትዮጵያ ክልሎች ተገቢ ድጋፍ ከማድረግ ይልቅ ችግሩን “በራስ አቅም የሚፈታ ችግር ነው” በሚል ባሳየው ዳተኝነት ድርቁ ወደ ረሀብ እንዲያድግ ከማድረግ ውጪ ይህ ነው የሚባል መፍትሄ ሲሰጥ አልታየም፡፡

ከህወሃት/ኢህአዴግ ፍላጎት ውጪ ቢሆንም አዲሱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ፤ ኢትዮጵያ የተረጋገጠባትን ድርቅ እንድትቋቋም ዓለአቀፉ ማኅበረሰብ በጋራ እንዲቆም በተደጋጋሚ ጥሪ አቀርበዋል፡፡ ያም ሆኖ ዕርዳታው በሚፈለገው መጠን ሊገኝ አልቻለም፡፡ ለዜጎች ስቃይ ደንታ ቢስ የሆነው የህወሃት አገዛዝ በዓለምአቀፍ መድረኮች የእርዳታ ጥሪ ከማቅረብ ይልቅ፤ የአገሪቱ “አዳኝ መሲህነቱን” መስበኩን ተያይዞታል፡፡ ውጤቱም የዜጎችን ነገ በማጨለም የረሀብ ቤተሰብ የሆነ ተስፋ የለሽ ትውልድ ማፍራት ሆኗል፡፡

“ልማት የረሃብ አደጋን ያጠፋል” (መለስ፣ 1887)፣

“ራሱን የቻለ በራሱ የሚቆም ከልማት ጋር ያልተቆራኝ የረሀብ ማጥፋት ፖሊሲ ያስፈልገናል” (መለስ፣ 1992)፣

“ዕድገታችን የረሀብ አደጋን ቀንሶልናል” (መለስ፣ 2004)፣

“ማንኛውንም ድርቅ ለመቋቋም የሚያስችል አቅም መገንባት ችለናል” (ኃይለማርያም፣2008)፣ …

እየተባለ በህወሃት/ኢህአዴግ ሲስተጋባ የኖረው ፕሮፓጋንዳ በእዉን የማይጨበጥና የማይዳሰስ መሆኑን እየታዘብን ነዉ፡፡ በአገሪቱ “አለ” የተባለዉ “ዕድገት”ም በምግብ እህል ራስን ለማስቻልም ሆነ ከዉጭ እርዳታና ድጎማ ለማላቀቅ የቻለ አይደለም፡፡ የመንገድ እና የፎቅ ግንባታውም የድሃውን ጉሮሮ የሚዘጋ የዕለት ጉርስ ወደመሆን ሲቀየርና ህይወቱ ሲያሻሽል አልታየም፡፡ የተለመደው የድርብ አኻዝ “ዕድገት” ግን አሁንም ይደሰኮራል፡፡

በቀደሙት ሁለት ተከታታይ ዓመታት የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተከሰተዉን ድርቅ ለመቋቋም 16.5 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን “የብሔራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን” በህዳር/2009 ዓ.ም. ይፋ ያደረገዉ ሪፖርት ያመለክታል፡፡ በ2007/2008 ዓም አስቸኳይ ምግብ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው የነበሩ የአገሪቱ ዜጎች ቁጥር 11.2 ሚሊዮን እንደነበረ የሚገልጸው ሪፖርት በ2009 ዓ.ም ወደ 5.6 ሚሊዮን ዝቅ እንዳለ ይናገራል፡፡
goolgule.

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: