በሚሊዬን የሚቆጠር ህዝብ በተራበበት ኦሮሚያ፣ ኦህዴድ በዓሉን በከፍተኛ ወጪ እያከበረ ነው

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የተመሰረትኩበትን 27ኛ ዓመት ‹‹እያከበርኩ ነው›› አለ፡፡ ድርጅቱ የምስረታ በዓሉን የሚያከብረው ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ እንደሆነም መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ እንደ ምንጮች ገለጻ ከሆነ፣ ድርጅቱ የምስረታ በዓሉን ለማክበር በሚሊዬን የሚቆጠር ገንዘብ በጅቷል፡፡ በሚሊየን የሚቆጠር ህዝብ በተራበበት ኦሮሚያ በሚሊዬን የሚቆጠር በጀት በጅቶ፣ የፈንጠዝያ በዓል ለማክበር መዘጋጀት ከሞራል አንጻር አስነዋሪ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ፡፡
በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች የገባው ድርቅ አራት ክልሎችን ክፉኛ እየጎዳ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ድርቅ ከገባባቸው ክልሎች በተጊጂዎች ቁጥር ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘው ኦሮሚያ ክልል ሲሆን፣ በክልሉም 2 ነጥብ 3 ሚሊዬን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋል፡፡ ዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፉን እንዲያደርግ ተማጽኖ በሚቀርብበት በዚህ ወቅት፣ የክልሉን ህዝብ ‹‹አስተዳድራለሁ›› ባዩ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲዊ ድርጅት፣ ተመስርቶ የትም ላልደሰረ ድርጅቱ የምስረታ በዓል ብሎ የመደበው ገንዘብ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ሊውል እንደሚገባ አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ፡፡
በእነ አቶ ኩማ ደመቅሳ፣ በእነ አቶ አባዱላ ገመዳ እና በሌሎችም ተማራኪ የደርግ ወታደሮች አማካይነት ለህወሓት የፖለቲካ ዓላማ ሲባል የተመሰረተው ኦህዴድ፣ በዓሉን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ‹‹አሁን ላይ የኦሮሞ ህዝብ የህይወት መስዋዕትነት ከፍሎ የጭቆና ቀንበሩን ከጫንቃው አንስቶ፣ ሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች እኩል መብት የተጎናፀፉባትን ሀገር እውን አድርጓል፡፡›› ሲል ለመሳለቅ ሞክሯል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በራሱ አንድ የጭቆና ቀንበር መሆኑን የገለጹት አስተያየት ሰጪዎች፣ ገዳይ አዋጅ በጫንቃው ላይ እንዲሸከም የተፈረደበት ህዝብ ‹‹ከጭቆና ነጻ ወጥቷል›› መባሉ አስቂኝ መሆኑንም ይገልጻሉ፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም ኦህዴድ ራሱ ህወሓት በኦሮሞ ህዝብ ላይ የጫነው የጭቆና ቀንበር መሆኑንም ይገልጻሉ፡፡ በአስቸኳይ አዋጅ ስር በምትገኝ ሀገር ውስጥ የሚከበርም ሆነ የተከበረ የህዝቦች ነጻነት እንደማይኖር የሚገልጹ ወገኖች በበኩላቸው፣ በተለይ ደግሞ የከፋ ግድያ እና እስራት ከተፈጸመበት የኦሮሚያ ክልል መንግስት እንዲህ ያለው መግለጫ መውጣቱ እንደሚያበሳጭ ይገልጻሉ፡፡

BBN

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: