የብሀዴን ሊቀመንበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከስልጣል ሊነሱና በምትካቸው አቶ አለምነው መኮንን ለቦታው መታጨታቸው ተነገረ( abbaymedia.com)

 

ዘግይቶ የደረሰው ዜና እንደሚለው በዛረው ለት የብሀዴን ህወሀት ስብሰባ ላይ የብአዴን ም/ሊቀምበር እና የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሆነው ሲሰሩ የነበሩት  አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከስልጣል ሊነሱና በምትካቸው አማራን ሲዘልፍና ሲነቅፍ የሚሰማው ኦድ አደሩ አቶ አለምነው መኮንን ለቦታው መታጨታቸውና ቦታውን እንደሚረከቡ ኢሳት ዘግባል ::

በተጨማሪም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስ እና በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መካከል የድነበር ግጭት በተከሰተበት በሁለቱ ጠገዴ በአማራው እና በትግራዩ ጠገዴ እየተባለ ሚጠራው ልዩ ስሙ ግጨው ተባለውን ቦታ ወያኔ የኔ ነው በማለት ወደ ትግራይ ሊካለል ይገባል በሚል ከመጠን ያለፈ ስግብግብነት በተነሳ የተከሰተው ግጭት 4ቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ማለትም 1ኛ/ ህውሀት 2ኛ/ ብአዴን 3ኛ / ደህዴን 4ኛ/ ኦህዴድ በተሰበሰቡበት በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰተው ተወስኖ ችግሩ ሁለቱን ክልሎች እየመሩ የሚገኙት ህውሀትና ብአዴን እነዲፈቱት ተወሰነ ::

ከዚያም የብአዴን ሊቀመንበር እና ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮነን ፤ የብአዴን ም/ሊቀምበር እና የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ፤አቶ አዲሱ ለገሰ ፤ አቶ በረከት ስምኦን ፤ አቶ ካሳ ተክለብርሀን ፤ አቶ አለምነው መኮነን እነዚህ ሰዎች በተሀኙበት የጠገዴ ወረዳ አመራር እና የብአዴን አባል የሆኑ

1ኛ / አቶ ደምለው ጀጃው የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸውና የብአዴን አባል እና የወረዳው አመራር

2ኛ / አቶ ዋኘው ደሳለኝ የት/ት ደረጃ 2ኛ ዲግሪ (ማስተርስ ) ያላቸው የወረዳው አመራር ሆኑ

3ኛ/ አቶ ተሸገር መለሰ የት/ት ደረጃ ቸው የመጀመሪያ ዲግሪ እና ወረዳው አመራር የሆኑ እነዲሁም የብአዴን አባል የሆኑ ኣና ብአዴንን ወክለው በድነበሩ ዙሪያ እንዲወያዩ ከላይ በተጠቀሱት የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ተመርጠው  ወደ ስራ ሲገቡ ህውሀት 3 ተወካዮች ልክ እንደ ብአዴን ተወካይ መርጠው ስራው ሲጀመር ብአዴን የወከላቸው ሰዎች ህውሀት ከመተን በላይ ያሳየውን ስግብግብነት በመቃወማቸው እና ለህውሀት አልመች በማለታቸው ከፍተኛ ተፅእኖ ተፈጠረባቸው ይህን ችግር ለብአዴን ቢያሳውቁም አቶ አለምነው መኮነን ተስማምታችሁ ስሩ ችግሮች ቢኖሩም አንዳንድ ጊዜ የሰጥቶ መቀበል መርህ ተመልከቱ ህውሀትን እንደ ጠላት አትዩት በአጋርነት እና በእህት ድርጅትነት እዩት ወዘተ በማለት ይመልሱላቸው ነበር

ከዚያም እነዚህ የብአዴን ተወካይ ሁነው የድነበር ተደራዳሪዎች ህወሀት እየሰራው ለው ህገ ወጥ ስራ በማጋለጣቸው መስከረም 25 ቀን 2009 ዓ/ም አቶ ዋኘው ደስአለኝን እና አቶ ተሸገር መለሰ የተባሉትን በህውሀት አመራሮች በተለይም የምእራብ ዞን አስተዳዳሪ በሆነው ኢሳያስ ታደሰ ትእዛዝ ጎንደር በመገኘት የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ተወካይ አቶ አሸናፊ ተስፋሁን እና አቶ ይዘዝ ተሾ አማካኝነት በመከላከያ በቁጥጥር ስር ውለው አዘዞ ካምፕ ድብደባና ግፍ እየተፈፀመባቸው የህውሀትን ፍላጎት በድበር ዙሪያ ልትቀበሉ ይገባል እየተባሉ ቢደበደቡም ለብአዴን ሪፖርት ቢደረግም ብአዴን የተያዙት የተያዙት በፌደራል መረጃ በመሆኑ እኛ መፍትሄ ልንሰጥ አንችልም አሉ ከዚያም እነዚህ ሰዎች የህውሀትን ፍላጎት አንቀበልም ሲሉ ወደ ብር ሸለቆ ተላኩ ከዚያም ከብር ሸለቆ ወጥተው አርብ ጥር 26 ቀን 2009 ዓ/ም ወደ ጎንደር ሲመጡ አሁንም ማክሰኝት ከተማ ሲደርሱ የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አባላት በሽፍን መኪና በመከተል ከነበሩበት መኪና በማስወረድ ዋኘው ደስለኝ የተባለውነ ሰው አፍነው አስካሁን ድረስ የት እንዳለ ማወቅ አልተቻለም ይህ በእንዲህ እዳለ አንደናው የኮሚቴ አባል የነበረው አቶ ደምለው ጀጃው ተባለውነ ጥር 18 ቀን 2009 ዓ/ም ምሽት ላይ ከመኖሪያ ቤቱ እነዚህ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት በአቶ አሸናፊ እና አቶ ይዘዝ አማካኝነት ከህውሀት አባሉ የምእራብ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኢሳያስ ታደሰ አዛዥነት ታፍኖ ከተወሰደ እነሆ 11ኛ ቀኑ ነው ያለበትን አድራሻ ሊታወቅ አልቻለም በአሁኑ ሰኣት የብአዴን ተወካዮች ታፍነው አድራሻቸው ጠፍቶ ህውሀትን የወከሉት ብቻቸውን እንደፈለጉ ድነበሩን እያሰመሩ ይገኛሉ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴዎች የክልሉ ከፍተና አመራሮች ምንም አይነት ምላሽ ያልሰጡ እና ለቤተሰቦቻቸው ኮማንድ ፖስቱን ጠይቁ በማለት መልስ መስጠታቸው ከፍተና መነጋገሪያ ሆኗል ፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: