የዐማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛዎች በዳኛ ቢኒያም ዮሐንስ ላይ የተወሰደውን እርምጃ ተቃወሙ፤

13819494_611651515666849_1114674654_n
፩ ትናንት የካቲት 14 ቀን 2009 ዓ.ም. በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት አቶ ቢኒያም ዮሐንስ ችሎት ላይ እንዳሉ የወያኔ ደኅንነቶች አፍነው መውሰዳቸውን ተከትሎ የዐማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ዛሬ ተቃውሟቸውን መግለጻቸው ተሰምቷል፡፡

ዳኞቹ የፍርድ ቤትን አሠራርንና ሕገ መንግሥትን በጠራራ ፀሐይ ሙልጭ አድርጎ የጣሰ የማፍያ ሥራ መሆኑን ለፍትኅ ቢሮ አስታውቀዋል ተብሏል፡፡ ወያኔ ምንም እንኳ በዳኞች ውሳኔ ላይ ጣልቃ በመግባት ይህ የመጀመሪያው ባይሆንም እንዲህ ያለው ዐይን ያወጣ የማፍያ ሥራ ግን በታሪክ ታይቶ አይታወቅም ሲሉ ተችተዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ዳኞች መደበኛ ሥራቸውን እንዳላከናወኑ ተገልጧል፡፡
አቶ ቢኒያም ዮሐንስን እንዲታሰር ያደረገው አዲሱ የጎንደር ማረሚያ ቤት ሹም የትግራይ ተወላጁ ጀማል ሰኢድ ሲሆን በዳባት ማረሚያ ቤት በነበረ ጊዜ ለበርካታ ወጣቶች እንግልትና ሞት ተጠያቂ እንደሆነም መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a comment