ወያኔ /ህወሓት ወታደሮቹና የፌድራል ፖሊሶቹ በቡድንም ሆነ በነጠላም እየተሰወሩ መሆኑ ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ ከቶታል !

በጥር 29ና 30 – 2009 ዓ.ም መኖሪያው በአማራ ክልል በአዊ ዞን በቻግኒ ከተማ ከሆነው በፈጥኖ ደራሽ ህድሴ ዲቪዥን 1ኛ ሻለቃ 2ኛ ጋንታ 4ኛ ሃይል መኖሪያ ካምፕ ውስጥ እና ከዚሁ ሃይል መኖሪያ ጎን ካለው ከ12 ክ/ጦር የወጣች አንድ ሃይል ውስጥ በቡድን ና በነጠላ መሰወራቸው ታውቋል። ከወታደሮቹ ውስጥ ብቻውን በጥር 29 /2009 የተሰውረው ወታደር ተካ ሲሆን እሱን ለመፈለግ ከፈጥኖ ደራሹና ከወታደሩ በተውጥጣ ሃይል ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ መውጫወች በስፉት አሰሳ የተደረገ ሲሆን በዚሁ አሰሳ 4 ወታድሮችና 2 ፌድራል ፖሊሶች መስወራቸው የወያኔን የመከዳት ትኩሳት ጨምሮታል። በተያያዘ በደቡብ ጎንደር ዞን አርባያ ከተማ 7 የፌድራል ፖሊሶች የደምብ ልብሳቸውን ከመንገድ ላይ በመጣል ከነሙሉ ትጥቃቸው መሰወራቸው ታውቋል። የህወሓት አምባገነን ቡድን በተለያዩ ጠረፉማ ቦታወች ላይ በየጊዜው ወታደሮችን እንዲቀያይር የሚገደድበት ሁኔታ አንዱ ከፍተኛ የመክዳት ሁኔታ በወታደሩ መፈጠሩ መሆኑ ይታመናል። ዘረኛው ወያኔ የትግራይ ተወላጆች ካልሆኑ በስተቀር አፍኖ ካልያዛቸው እያንዳንዱ ወታደር እንደሚከዳው ያውቃል። በዚህ አፍኝና አምባገነን ወታደራዊ መዋቅር ዕዝ እንኳን ለቁጥር የሚያዳግቱ በተለያዩ ግምባሮች እንደከዱት ይታወቃል ።ለዚህም ነው በወያኔ የፍራቻ መጠን መናር ምክንያት ካካባቢው ጋር እንዳይላመዱና ነባራዊ ሁኔታውን እንዳይረዱ እንዳያውቁት በመፈለጉ በየጊዜው ሊያዘዋውራቸው የቻለው በቅርቡ እንኳ በቋራ በረሃወች ና በቤንሻንጉልና በጅዊ ጠረፉማ አካባቢወች በማያውቁትና ምንም አይነት መረጃ ስለአካባቢው በሌላቸው አዲስ የተዛወሩ ወታደሮች በማስገባት በውሃ ጥምና መንገድ በመጥፉት ለሞት እንዲዳረጉ ያደረጋቸው። በቤንሻንጉልና አማራ ክልል ጠረፋማ አካባቢወች እስካሁን ውጥረቱ እንዳየለ ሲሆን በተለያዩ ነባርና አዳዲስ ኬላወች ፍተሻው እንደቀጠለ ነው ።

1e4dbe582b6848de918933e085ce1b61_18

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: