ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው የዋስትና ይግባኝ ክርክሩን አሰምቷል ተባለ

የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ተከሶበት ከነበረው የሽብር ወንጀል ነጻ ተደርጎ በመደበኛ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 257/ሀ/መ/ ስር የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት እንዲከላከል የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የሰጠውን ብይን ተከትሎ፣ ተከላከል የተባለበት አንቀጽ ዋስትና ስለሚፈቅድ የዋስ መብቴ ይከበርልኝ በሚል ያቀረበውን ጥያቄ ይኸው ችሎት ታህሳስ 25/2009 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ውድቅ ማድረጉን በመቃወም ይግባኝ ማለቱ ይታወሳል፡፡

 

በዚሁ መሰረት ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው የዋስትና ጥያቄው ላይ ለፌደራሉ ጠ/ፍ/ቤት የይግባኝ ክርክሩን ዛሬ ጥር 29/2009 ዓ.ም በችሎት ቀርቦ አሰምቷል፡፡
ይግባኝ ባይ ጌታቸው ሺፈራው የስር ፍርድ ቤት የዋስ መብቱን ለመከልከል የጠቀሰው ‹‹በዋስ ቢወጣ ከሽብር ቡድን አመራሮች ጋር ግንኙነት ሊያደርግ ይችላል፣ በህጋዊም ሆነ በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ይችላል በሚል ግምት›› መሆኑን በማስረዳት፣ ፍ/ቤቱ በዋስ ብወጣ ቀጠሮየን አክብሬ እንደማልቀርብ የሚያሳይ ማስረጃ አለመቅረቡንና አይቀርብ ይሆናል ብሎ ለመገመት ብቃትም አግባብነትም የሌላቸውን ጉዳዮች በማንሳት ህገ-መንግስታዊ የዋስ መብቴን መከልከሉ አግባብ አይደለም ሲል ቅሬታውን አስመዝግቧል፡፡

 

‹‹በዋስ ቢወጣ ከሽብር ቡድን አመራሮች ጋር ሊገናኝ ይችላል…›› የሚለው ‹ግምትም› ቢሆን ቀደም ብሎ ቀርቦብኝ የነበረው ክስ ሆኖ በአቃቤ ህግ ማስረጃ ባለመደገፉ የስር ፍ/ቤት ራሱ ከሽብር ወንጀል ነጻ መሆኔን በይኖ እያለ ዋስትና ለመከልከል እንዲህ ያለውን ግምት መውሰዱ አግባብ አለመሆኑን ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ ይገንዘብልኝ ሲል ቅሬታውን አሰምቷል፡፡
በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት ትዕዛዝ ተሽሮ በዋስ ሆኖ እንዲከራከር እንዲፈቀድለት ጌታቸው ጠቅላይ ፍ/ቤቱን ጠይቋል፡፡

 

መልስ ሰጭ የፌደራል አቃቤ ህግ በበኩሉ ይግባኝ ባይ በዋስ ቢወጣ ከሀገር ሊወጣ ይችላል የሚለው እምነቱ አሁንም መኖሩን በመጥቀስ የይግባኝ ባይ ጥያቄ ውድቅ እንዲደረግለት አመልክቷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ 1ኛ ችሎት የቀረበውን ክርክር መርምሮ ብይን ለመስጠት ለየካትቲ 03/2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ: የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት

 

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: