ባለፈው አመት ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ለመግባት ከሞከሩ አፍሪካውያን መካከል 5ሺ የሚሆኑ በባህር ላይ መሞታቸው ተገለጸ

images

ባለፈው የፈረንጆች አመት 2016 አም ከሊቢያ የሜዲትራኒያን ባህርን አቋርጠው ወደ ጣሊያን ለመግባት ከሞከሩ ከ180ሺ በላይ ስደተኞች መከክል 5ሺ የሚሆኑት መሞታቸው ተገለጸ።
በቅርቡ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የኤርትራና የሶማሊያ ስደተኞችን አሳፍሮ ከሊቢያ ወደ ጣሊያን በማቅናት ላይ የነበረ ጀልባ በሜዲትራኒያን ባህር የመስጠም አደጋ አጋጥሞት 180 ሰዎች መሞታቸውን የጣሊያን የባህር ህያል ባለስልጣናት አመልክተዋል።
ከሊቢያ ወደ ጣሊያን በመሰደድ ላይ ያሉ የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ዜጎችን ድርጊት ለመቆጣጠር ጣሊያን የ200 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ማፅደቋን ሮይተርስ ረቡዕ ዘግቧል።
የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አንጀሊኖ አልፋኖ ባለፈው አመት ብቻ ወደ 181ሺ የሚጠጉ የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ስደተኞች ወደ ሃገሪቱ መግባታቸውንና ወደ 5ሺ የሚጠጉት ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን ለመገኛኛ ብዙሃን አስረድተዋል።
የስደተኞቹን ችግር ለመቅረፍ ሲባል ጣሊያን የተመደበው ገንዘብ ስደተኛ ለሚበዛባቸው ሃገራት ድጋፍ እንዲውል ሃሳብ ማቅረቧ ተመልክቷል።
የአፍሪካ ሃገራት የድንበር ቁጥጥራቸውን ከማጠናከር በተጨማሪ የተለያዩ ተጓዳኝ ስልጠናዎች እንዲሰጣቸው እንደሚደረግ የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አክለው ገልጸዋል።
ይሁንና አለም አቀፍ የሰደተኛ ተቋማት የአፍሪካ ሃገራት የድንበሩ ቁጥጥር እንዲጠናከር የሚያደርገው ጥረት ውጤት አለመምጣቱ የስደተኞቹ ቁጥር በመጨመር ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።
ሊቢያ፣ ቱኒሲያ፣ እና ኒጀር ጣሊያን ባቀረበችው የገንዘብ ድጋፍ በግንባት ቀደምትነት የታቀፉ ሲሆን፣ ናይጀሪያ፣ ሴኔጋል ግብፅና ኢትዮጵያም ካላቸው የስደተኛ ቁጥር መበራከት አንጻር በፕሮግራሙ ሊታቀፍ እንደሚችሉ የጣሊያኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይፋ አድርገዋል።
የአውሮፓ ህብረት 28 አባል ሃገራት ከሁለት ቀን በኋላ ጣሊያን ባቀረበችውና ተጓዳኝ በሆኑ ጉዳይ ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በርካታ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የጎረቤት ኤርትራና ሶማሊያ ስደተኞችን አሳፍሮ ከሊቢያ ወደ ጣሊያን በማቅናት ላይ የነበረ ጀልባ በሜዲትራኒያን ባህር ላይ የመስጠም አደጋ አጋጥሞት 180 ስደተኞች መሞታቸውን የጣሊያን የባህር ባለስልጣናት ሰሞኑን አስታውቀዋል።
የስደተኞቹ ጀልባ ከሊቢያ ከተነሳ ከአምስት ሰዓታት በኋል ሞረቱ ላይ በደረሰ ብልሽት አደጋው መድረሱን የገለጹት ባለስልጣናት ሁለት ኢትዮጵያውያንና ሁለት ኤርትራዊያን ከአደጋው መትረፋቸውን እንደተናገሩ ሲንሁአ ዘግቧል።
በባህሩ ላይ በድንበር ቁጥጥር ተሰማርተው የነበሩ የፈረንሳይ የባህር ሃይል አባላት አራቱ ኢትዮጵያውያንን እና ኤርትራዊያንን መታደግ የቻሉ ሲሆን፣ በእስከ አሁኑ ፍለጋ አራት አስከሬን ብቻ ሊገኝ መቻሉን የነብስ አድን ሰራተኞች አስታውቀዋል።
ከሊቢያ መውጫን አጥተው የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያንና የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ህይወታቸውን አደጋ ላይ በሚጥል ጉዞ ወደ አውሮፓ በተለይ ወደ ጣሊያን ለመግባት ሙከራ እንደሚያደርጉ የስደተኛ ድርጅቶች ይገልጻሉ።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: