በቦረና እና ጉጂ የተከሰተው ድርቅ ከ1977ቱ የባሰ እንደሆነ አርሶ አደሮች ተናግረዋል

በኢትዮጵያ በአምስት የተለያዩ ክልሎች ከደረሰው ድርቅ የቦረና ዞኑ የከፋ በመሆኑ ከብቶች መሞት መጀመራቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። በጥቂት ቀናት ውስጥ ዝናብ መጣል ካልጀመረ ደግሞ ለከፋ አደጋ እንደሚጋለጡ በመግልጽ አሁን ያለውን የግጦሽ መሬት መድረቅ በ1977 ዓ.ም ከደረሰው አስከፊ ድርቅ ጋር ያያይዙታል።

በኢትዮጵያ በኦሮሚያ፣በሶማሌ፣በአማራ በደቡብ ፣በአማራ እና በአፋር በአጠቃላይ በአምስት ክልሎች በደረሰው ድርቅ 5.6 ሚሊዮን ሰው አስቸኳይ የዕለት ደራሽ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ከዚህም ውስጥ 36 በመቶ የከፋ የድርቅ አደጋ የደረሰበት በኦሮሚያ ክልል በቦረናና ጉጂ ዞን መሆኑን መንግሥትና ለጋሽ ድርጅቶች አስታውቀዋል።

1796634_222183061305326_875283870_n

የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሣ በበኩላቸው በአሁኑ ሰዓት 5.6 ሚሊዮን ሕዝብ የዕለት ደራሽ እርዳታ እንደሚፈልግ፣ የከብቶችን እልቂት ለመቋቋም በአስቸኳይ ለገበያ የማቅረብ እርምጃ ለመውሰድ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል ።

በድርቁ ምክኒያት ትምሕርት አቋርጠው የነበሩ ተማሪዎችን በትምሕርት ቤት ውስጥ በመመገብ ወደ ትምሕርት ገበታቸው እንዲመለሱ ማድረግ እንደተጀመረም ተናግረዋል ሲል የዘገበው የአሜሪካ ድምጽ ነው፡፡

በኢትዮጵያ በሶማሌ ፣ በኦሮሚያ ፣ በአማራ ፣  በደቡብ እና በአፋር ክልል ድርቅ በመከሰቱ 5.6 ሚሊዮን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው መንግስት እና የእርዳታ ሰጪዎች መግለጻቸውን ያስታወሰው ዘገባው ከዚህ ውስጥ በባሰ ሁኔታ በድርቁ የተመታው በኦሮሚያ ክልል በቦረና እና ጉጂ ዞን መሆኑም ይህም በ36 በመቶ እንደሆነ መታወቁም ተገልጿል፡፡

ዘገባው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ጽ/ቤት በድረገጹ ያወጣውን ሪፖርት ጠቅሶ እንዳለው በቦረና የተከሰተው ድርቅ የከፋ በመሆኑ ከብቶች መሞት መጀመራቸውን እና በሶማሌ ክልልም በአርብቶ አደር ቀበሌዎች የምግብ እና የውሃ እጥረት መባባሱን አመልክቷል፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: