በሶማሊላንድ የአማራና ኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ተያዙ

15354184_682255945273072_1620739714_o

ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን ከ250 ያላነሱ የአማራ እና ኦሮሞ ብሄር ተወላጆች በሶማሊላንድ ፖሊሶች ተይዘው የታሰሩ ሲሆን፣ ከእስሩ ጀርባ የህወሃት ኢህአዴግ መንግስት እጅ እንዳለበት ታውቋል።
የኦነግ እና የአርበኞች ግንቦት7 ወኪሎች በሶማሊላንድ መኖራቸውን መረጃ ደርሶናል በሚል የህወሃት/ኢህአዴግ የደህንነት አባላት ከሶማሊላንድ የጸጥታ አባላት ጋር በመሆን የተያዙት ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲተላለፉ እየጣሩ ነው። ብዙዎቹ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኝነት ወረቀት አላቸው።
ምንጮች እንደሚሉት በሶማሊላንድ የሚገኙ 4 የህወሃት አባላት የነበሩ ጡረታ የወጡ የጦር መኮንኖች ጀልባዎችን ገዝተው ከፍተኛ ገንዘብ እየተቀበሉ ሰዎችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ያሻግራሉ። እነዚህ ሰዎች በአገሪቷ የሚገኙከ3 ሺ ባላነሱ ኢትዮጵያውያን ላይ ክትትል የማድረጉንም ስራ በሃላፊነት ወስደው ይሰራሉ። አሁን በእስር ላይ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን እስር ጀርባም የእነዚህ ሰዎች እጅ እንዳለበት ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ሰዎች ይገልጻሉ።
በቅርቡ በሶማሊ ክልል ዋና ከተማ ጅጅጋ ላይ ተደርጎ በነበረው የደህንነት አባላት ስብሰባ ላይ ፣ በሶማሊላንድ የሚገኙ የመንግስት ተቃዋሚዎች እየተፈለጉ እንዲያዙና ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው እንዲሰጡ ውሳኔ ተላልፎ ነበር።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: