ኦህዴድን በቅርቡ ሽባ ማድረግ፤የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማራዘም፣ከዚያም ብአዴንን መምታት….በሚሉ ጉዳዮች ላይ ህወሃት ውስጥ ለውስጥ እየሰራ ነው

ህወሀት የኦሮሞን ህዝብ እና የአማራን ህዝብ በእጅ አዙር ሳይሆን በቀጥታ በረጅም ዱላ ለማስተዳደር ያመቸው ዘንድ ኦህዴድና ብአዴን የሚባሉ ድርጅቶችን አዋቅሮ ህዝብን መግዛት ከጀመረ በርካታ አመታትን አስቆጥሯል።

በባለፈው ዓመት በተለይ የኦሮሞ ተቃውሞ እንቅስቃሴውን ለመምራት የኦህዴድን የውስጥ መዋቅር እንደተጠቀመ የገመገመው ህወሃት እጅግ አደገኛ ወጥመድ ውስጥ መግባቱን አውቆ ተመጣጣኝ መፍትሄ ያለውን የከፍተኛ አመራር ለውጥ ቢያደርግም ችግሩ ግን እስካሁንም በዘላቂነት አልተፈታም።ወደፊትም የሚፈታ አይመስለኝም።

በአማራ በኩልም ህወሃት አንዳንድ የብአዴን አመራሮች አሉበት ባለው የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን ተከትሎ ባገረሸው የህዝቡ ስርዓት ለውጥ ፍላጎት (በእርግጥ #ግጨውን_ከመጠየቅ ውጭ ብአዴኖች እጃቸው የለበትም ይባላል) ምክንያት ማን ላይ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ግራ ተጋብቶ ቀን እየጠበቀ ይገኛል።ከግድያ ሙከራ እስከ እስራት ተሲሮበት የነበረው ለህወሃት “አልገዛም አለ” የሚባለው ከፍተኛ አመራርን ጨምሮ አንዳንዶች በሙስና ወንጀል ክስ ተዘጋጅቶላቸውም ቀን ብቻ እየጠበቁ ነው ይባላል።

እናም ህወሃት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጠቀም እወስዳቸዋለው ያላቸው ርምጃዎች በተለይ በሁለቱ ድርጅቶች በኩል ጠንከር ያለ ተቃውሞ መግጠሙና ለህወሃት በር የሚከፍት አለመሆኑ ህወሃት ከዚህ በፊት ይጠቀምበት የነበረውን የፈለገውን ሰው የማሰር ወይም የማንሳፈፍ ተግባር እንዲያጤነው አድርጎታል ተብሏል።ብአዴን ሁለቱን ከፍተኛ አመራሮቹን ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የገመገመና ሁለቱም ግን በመምራት ላይ ያሉ ናቸው። (በኢህአዴግ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶህ በአመራርነት መቀጠል አትችልም)።ሆኖም ግን ህወሃት ይህንን እያወቀ ምንም ማለት ሳይፈልግ እያስታመማቸው ይገኛል።

የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር ምንም እንኳን ተቃውሞው ጠንክሯብኛል ባለው በአማራ ክልል ውስጥ ባለፉት ሶስት ወራቶች ቁልፍ የሚባሉ የድርጅቱን ሰዎች ሳያስር ወይም ሳያባርር እያሽከረከራቸው ቢሆንም ሙሉ በሙሉ በሚፈልገው ወጥመድ ውስጥ ለማስገባት ግን የቻለ አይመስልም።እነዚህ ሰዎች ለህዝብ አስበው ከህዝብ ጋር ባይቆሙም እንኳን ራሳቸውን ለመከላከል ሲሉ ህወሃት እንደበፊቱ አንዱን አማራ በመጠቀም ሌላው አማራ እንዲወነጅል የፈቀዱለት አይመስልም። በተለይ በክረምት ወቅት ፀረ አማራ የነበሩና ስማቸው በተደጋጋሚ ይነሳ የነበሩት ሁሉ የህዝብን ጥያቄ መመለስ ባይችሉም ወደ ህወሃት መላላካቸው የቀነሰ ይመስላል።

በኦህዴድ በኩልም የስልጣን ሽግሽግ ካደረገ በኋላ ይቋረጣል ያለው የሀገር ውስጥ ትግልና የራሱ የድርጅቱ የውስጥ ትግል ከውጩ ጋር የፈጠረው ትስስር (የእነርሱ ግምገማም ነው) ለህወሃት ራስ ምታት ሆኖበታል።እንደሚታቀው ህወሃት መምራት የሚችለው ኦህዴድና ብአዴን እርስ በርስ ሲጋጩና አንዱ ሌላውን ለማሸነፍ በሚየደርጉት ውዝግብ ነው።ወይም መጠሁባችሁ እያለ ውስጥ ውስጣቸውን በማመስና በማስፈራራት ነው።
አሁን ላይ ብአዴንና ህወሃት የታሪክ ባለቤትነታቸውን መሰረት አድርገው የፈጠሩት መሻከር ወደ ልዩነት አድጎ “ትምክህት” ማለት ለብአዴን ሳይሆን ለህወሃት ነው ወደሚል መገማገሚያ ተሸጋግሯል።በሁለቱ አለመግባባት ተጠቃሚ የሆነው ኦህዴድ የራሱን አቅም ያጎለበተ ሲሆን ይህ ደግሞ በሌላ ጎኑ ህወሃትን አስደንግጦታል እየተባለ ነው።ኦህዴድን ማፈን ወይም ማግባባት የሚችለው በዋናነት ብአዴን ነው።ብአዴን ደግሞ አሁን ከኦህዴድ ጋር ምንም አይነት ልዩነት ሳይፈጥር ፊቱን ወደ ህወሃት አዙሯል።
ስለዚህ ህወሃት ያለው ምርጫ ከብአዴን ጋር መስማማት ወይም ባልተለመደ መልኩ ኦህዴድን ተጠቅሞ ብአዴንን መምታት ነው።በተለይ ባለፉት ሁለት እና ሶስት ሳምንታት የፖለቲካ_ሚዛኑ ወደ ኦሮሚያ በኩል መጠንከሩን ያወቀው ህወሀት ለኦህዴድ መላ እንደዘየደ ሲነገር በብአዴን ላይም ሌላ እቅድ አውጥቷል ተብሏል።

ኦህዴድ ላይ ግን ኦሮምኛ ተናጋሪ የትግራይና አማራ ተወላጅ ካድሬዎችን በተለይም በምክትልነት በስፋት ይሾማል ተብሏል።አሁን ላይ ከአማራ ያልተናነሰ የኦሮሞ እንቅስቃሴ እንዳሰጋው የገመገመው ህወሃት በኦህዴድ ላይ መካከለኛ አመራሩን ሰፊ ትኩረት ያደርግበታል ነው የተባለው።ከዚህ በተጨማሪም የውጭ ነዋሪው ጋር ያለውን ግንኙነት ሊያጠና የሚችል ልዩ የደህንነት አካልም ሊያሰማራ ይችላል ተብሏል።

በብአዴን በኩል ህወሃት በአጭር ጊዜ ውስጥ ይተገበረዋል የተባለ የአመራር ማስወገድ ተግባር በከፍተኛውም ሆነ በመካከለኛው የተያዘ አይመስልም።ይልቁንም ጊዜ ሰጥቶ (ምናልባትም የአስቸኳይ_ጊዜ_አዋጁንም አራዝሞ) ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት በሚፈጅ ጊዜ ከፍተኛ የደህንነት ስራ መስራት የሚል ነው እንደ መፍትሄ ህወሃቶች ያስቀመጡት።በስልላ ስራው ከቤተሰብ እስከ ሾፌርና ልዩ ጥበቃ የተጠና ክትትል ማድረግ ታስቧል፤ ምናልባት በዚህ ሂደት ውስጥ የተጠና አፈና/ግድያ በጣት በሚቆጠሩ አመራሮች ላይ ብቻ ሊወሰድ ይችላል።በህዝብ ውስጥ ያሉ የጎበዝ አለቆችን ግን አሁን እያደረገ እንዳለው እስራትም ግድያም በስፋት እንደሚሰራበት ያመለክታል።

በዚህ የጊዜ ውስጥም ቀደም ብሎ የሚተገበረው በኦህዴድ መካከለኛ አመራር ላይ የተሚሞከረው ውጤታማ ከሆነና ህወሃት ኦህዴድን በእጁ ሙሉ በሙሉ ማስገባቱን ካረጋገጠ ቀጣዩ ብአዴንን በጅምላ የመምታት ስራ መጀመር ይሆናል።ይህ ህወሃት በተከታታይ ባለፊት ጥቂት ሳምንታት እንደ አማራጭ በውስጡ እያብላላው ያለ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ህወሃት የፖለቲካ ምህዳሩን ለመዘወር ቢያንስ በአማራ በኩል በስፋት ሲስተጋባ የነበረውን የወልቃይትን ጥያቄ እንኳን በህጋዊ ስርዓት እንዲያልፍ በሚል ጊዜ ይገዛበታል እንጅ በቀጥታ ወደ እናት ግዛቱ አማራ ህዝቡንም ወደ ወገኑ አይመልስም፤ወደ ህዝበ ውሳኔም አያቀርበውም የሚል መላ ምት አለ።ሌላው የህወሃት የበላይነት ይብቃ የሚለውን መፈክር ጉዳይ ብአዴን እንዲያስተባብል መስከረም ላይ ስለቀረበለት ቢያስተባብልም ህወሃት ግን አሁንም እንደ ቀላል አልተመለከተውም።በተለይም በሰራዊቱ ውስጥ አሁን እየታየ ካለው የውስጥ ለውስጥ የብሄርተኝነት እንቅስቃሴ ጋር ተዳምሮ “የህወሃት የበላይነት ነግሷል” የሚለውን የህዝብ ብሶት እና የአቻ ድርጅቶቹ ጉምጉምታ ህወሃት በትኩረት እየተመለከተው ያለው ጉዳይ ነው።ይህንን አቅጣጫ ያስቀይራል ያለውን ሁሉ በየጊዜ አጀንዳ እየቀረፀ የሚለቅ ሲሆን የአማራ ሚዲያ፣ እና በውጭ ያለውን እንቅስቃሴ ከቀሪው ህዝብና ከሌላው ብሄር ጋር የመነጣጠል፣ የክልል ድንበር ቁርሾዎችን ለሶስተኛ ወገን እየሰጡ ትኩረት መሳብንም ይተገብረዋል ተብሎ ይጠበቃል።ከዚህ ውጭ ምንም አይነት የፖሊሲም ይሁን የስትራቴጅ ለውጥ እንደማይከተል ግን ከሁሉም ድርጅቶቹ ጋር የተግባባበት ነው።እየተከተልነው ያለው የአብዮታዊ መስመር “የጠራ” ነው፤ችግሩ ያለው ከአመራሩ ነው የሚል ቀጭን ትዕዛዝም አስተላልፏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ በፊት ይስተዋል የነበረው በህወሃት በራሱ ውስጥ የነበረ ቡድንተኝነት አሁን እንደማይታይ ታውቋል።”ከዚህ ወቅት የከፋ በጋራ ሊያቆመን የሚችል ጊዜ የለም” በማለት ተማፅኖ ለአቻዎቻቸው ያቀረቡት የህወሃት ነባር “ታጋዮች” ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው ለህልውናቸው ሲሉ መተባበር ብቻ አማራጭ እንደሆነ በሀይለ ቃል ነው የተነጋገሩት።እጅግ ወሳኝ የተባሉ የህወሃት ሰዎች ቢያንስ በሳምንት ሁለት ጊዜ እንደሚገናኙም ለማወቅ ተችሏል።

በአጠቃላይ የኦህዴድና የብአዴን ራሳቸው ለመታደግ ሲሉ የመጥንከር አዝማሚያ ማሳየትና በየስብሰባዎች የህዝብን ብሶት ማስተጋባት መጀመር ህወሃት የፖለቲካ ሚዛኑ ከእጁ እየወጣ መሆኑን አስገንዝቦታል።ስለሆነም የመጀመሪያ ዱላውን ኦህዴድ ላይ ለማሳረፍ እየሰራ እንደሆነ ታውቋል።

No automatic alt text available.No automatic alt text available.
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: