የጎንደርን የሕዝብ እንቢተኝነት ለማፈን የተለያዩ እርምጃዎች ቢወሰዱም አልተሳካም

በህወሃት የሚመራው መንግስት ከህዝብ የቀረቡትን መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎች ለማፈን በሶስት መንገዶች ትኩረት ሰጥቶ ከፍተኛ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን ሲአደርግ መሰንበቱ ተገለፀ። የተከተላቸውም ሶስት መንገዶች

በተለመደው የማታለያ ዘዴው የህዝቡን ቁጣ ለማብረድና ለመብቱ የሚአደርገውን ትግል ለማዘናጋት የተንዛዙ ህዝባዊ ስብሰባዎችን በተለያዩ ቦታዎች አካሂዷል። ይህ ጥልቅ ተሃድሶ በሚል መርሆ ሲካሄድ የሰነበተ ቢሆንም ወያኔ ያሰበውን ውጤት ከማስገኘት ይልቅ ሕዝቡ “በጥልቅ መታደስ አለብን ባላችሁበት የምትነግሩን የመንግስት ገድል፤ የምታበስሩን የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ አስታሳሰብ ስኬት ከወዴት የተገኘ ነው?ወይስ ለእኛ የማይታይ ለእናንተ የተከሰተ ብቻ። ህዝቡ እንደሚለው ለጥቂት ግለሰቦች ብቻ ጥቅም የዋለውን ልማትና እድገት ነው የምትነግሩን?ይህ ከሆነ ስብሰባው አያስፈልግም። 25 ዓመታት ሲነገር ቆይቷልና በከንቱ የግልና የመንግስት የስራ ሰዓት አናባክን። በግልፅ እንነጋገር ከተባለ እንደ ድርጅትም ያቀረባችሁት የሕዝብ ጥያቄ አገሪቱን መምራት አልቻላችሁም። የምትሉት ልማትና እድገት ከእናንተ አልፎ ለእኛ አልደረሰንም። ዘላቂና ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልገናልና በዚህ ጉዳይ ከሆነ እንነጋገር” በማለት አክሽፎታል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጉዳይ በዚሁ ባሳለፍነው ሳምንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በዳባትና በደባርቅ ከተማዎች በመገኘት ለወያኔ ከፍተኛ ስጋት የፈጠሩበትን በቆላማው ሕዝብ የተወከሉ የጎበዝ አለቆች ጋር ሽማግሌዎች በመላክ ትጥቅ ለማስፈታት ያደረገውም ሙከራ ባለመሳካቱ ካለውጤት መመለሱንም የተለያዩ የሚዲያ ምንጮች ዘግበዋል።

ሁለተኛው በትኩረት የተንቀሳቀሱበት መንገድ ያው ጥርሳቸውን ነቅለው ያደጉበትን የማከፋፈል ሴራ ተግባራዊ ማድረግ ሲሆን የወሎና የሸዋን አርሶ አደሮች መሳሪያ እናስታጥቃችኋለን፤መሳሪያውም በግል ንብረትነት ይፀድቅላችኋል በሚል መደለያ በጎንደር የነፃነት ታጋዮች ላይ ለማዝመት ዝግጅቱ የተጀመረ ሲሆን ዉጤቱ ገና የሚታይ መሆኑ ተገልጿል። በቅማንትና በአማራ መካከል በወያኔ የተጀመረውም ቅራኔ ለጎንደር ሕብረት መፈጠር ምክንያት በሆኑት በኢትዮጵያዊነታቸው ድርድር በማያዉቁት ውድ ልጆቿ ቢከሽፍም ልዩነት ለመፍጠር የማይተኛው ወያኔ በአለፈው ሳምንት በተካሄደው በዳባትና ደባርቅ የእግር ኳስ ቡድን ጨዋታ ዉጤት ጋር ተያይዞ በተደረገው ልማዳዊ የአሽናፊ ጭፈራ መካከል የወያኔ ካድሬዎች ሰርገው በመግባት ጠብ ጫሪ ቃላትን በመጠቀም ሁከት ለመፍጠርና ለማድረግ ያሰቡትን ሁኔታዎች ለማመቻቸት ቢሞክሩም በሕዝቡ መንቃት ከሽፏል።
ሦስተኛው በስፋት በአርበኛች ግንቦት7 እና በኢሳት እንደተዘገበው የአለፈው ሳምንት የወያኔ እንቅስቃሴ ያተኮረው በጎንደርና በጎጃም ብዛት ያላቸውን ወጣቶች በሌሊት ከየቤታቸው እየወሰደ ወደተለያዩ እስር ቤቶች ማጓዝ ሲሆን ብዙ ተማሪዎች እንዲሁም የባንክ ማኔጀሮች ሳይቀሩ መታሰራቸው ተገልጿል።ከዚሁ ከጉልበቱ እርምጃ ጋር በተደጋጋሚ የሚሞክራቸው የነፃነቱን ኃይል ለማንበርከክ ወጣ እያለ የሚአደርጋቸው የአሰሳ ሙከራዎች ሲሆኑ በዚህ ረገድ በለስ እንዳልቀናው በተለያዩ ምንጮች ተዘግቧል። በአለፈው እሁድ የአርበኛች ግንቦት 7 ዘገባ ከትግራይ ተነስቶ በሽራሮ በኩል አድርጎ ወደወልቃይት ፀገዴ ይጓዝ የነበረው የወያኔ ወታደራዊ ኮንቦይ አድፍጠው ይጠባበቁ በነበሩ የአካባቢው ጀግኖች ጥቃት ደርሶበት 16 የወያኔ ወታደሮች ተገድለው ወደ 30 የሚጠጉ ቁስለኛ መሆናቸውን እና ወያኔ ይጠቅሙኛል ብሎ ያስታጠቃቸው የአካባቢው ሚሊሺያ ታጣቂዎች ከሕዝቡ ጎን ተሰልፈው መፈናፈኛ እንዳሳጡት ጨምሮ ገልጿል። በዚህ የደፈጣ ዉጊያም ብዛት ያላቸው ቀላልና የቡድን መሳሪያዎች መማረካቸውም ተገልጿል።
አባይ ሚዲያ

15123252_226347067794606_1099607009416258927_o

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: