በሰሜን ጎንደር ዞን በአርማጭሆና በመተማ የተለያዩ የቦንብ ፍንዳታዎች ደረሱ

ኢሳት ዜና :- ትናንት እና ዛሬ በመተማ ወረዳ ገንዳ ውሃ በተባለው ቦታ ሁለት የእጅ ቦንቦች የፈነዱ ሲሆን፣ ነጋዴ ባህር በተባለ ቦታ ላይም ተመሳሳይ ቦንብ ፈንድቷል። ይህን ተከትሎም አካባቢው በወታደሮች የተከበበ ሲሆን፣ በርካታ ወጣቶችም ታፍሰዋል። ከትናንት ጀምሮ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መስፈኑን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ነዋሪዎች ጥቃቱ በነጻነት ሃይሎች መፈጸሙን ከመግለጽ ውጭ በዝርዝር ጥቃቱን ስለፈጸሙት ሃይሎች አልተናገሩም። አንደኛው ቦንብ በህወሃት የጥድ ማዳመጫ ላይ የተወረወረ ሲሆን፣ ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ መቃጠሉም ምንጮች ገልጸዋል።
ጃኑላና ጫኮ ሚካኤል በተባለ ቦታ ላይም እንዲሁ የእጅ ቦንብ መፈንዳቱን ተከትሎ የጥምቀት በአል በአካባቢው ህዝብ ሳይሆን በወታደሮች ብቻ ታጅቦ መከበሩን፣ የአይን እማኞች ገልጸዋል። ፍንዳታውን አካባቢውን የተቆጣጠረው የኮማንድ ፖስት ሆን ብሎ እንዳደረሰው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። በገዢው ፓርቲ በኩል ግን እስካሁን የተሰጠ መግለጫ የለም። በአሁኑ ሰአት ህዝቡን ቅማንት አማራ በማለት ለመለያየት ሙከራ እያደረገ ሲሆን፣ በርካታ ሰዎችም ተይዘው ታስረዋል።
እነዚህ አካባቢዎች አገዛዙ ቀይ መስመር ብሎ የሰየማቸው ቦታዎች ሲሆኑ በተደጋጋሚ በነጻነት ሃይሎች እየተደፈሩ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

14457537_1779246709011447_6947376628893828324_n

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: