የህወሓት ምንም አይነት ድራማ ስርዓቱን አያድነውም::

ህወሓት ከተቃዋሚዎች ግር ክርክር እና ድርድር ሊያደርግ ዝግጅቱን ጨርሶ በዚህ ሳምንት ይጀምራል:: ተቃዋሚ ተብለው የተፈረጁት ዝግጅታቸውን አጠናቀው እየተጠባበቁ እንደሆን እየተዘገበ ነው:: አየለ ጫሚሶ፣ ለደቱ አያሌው፣ ትግስቱ አወሉ እና ሌሎችም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል:: ይህ ትዕይንት የተጣ የተደረሰው፣ የታለመው፣ የሚተገበረው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት ውስጥ በተቁአቁአመው የዴሞክራሲ ግንባታ መስሪያ ቤት ነው:: ይህ መስሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ የህወሓት ነው:: መሪውም የኢህአዴግ ባለስልጣን ነው:: ለየት የሚያደርገው ልደቱ አያሌው የዚህ አካል ነው:: ስለዚህ ሲቀርብ ተከራካሪ ወይም ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን የሚፈለገውን ውጤትም እያወቀ ነው:: የታሰበው ውጤት ደግሞ ስርዓቱን ለመለወጥ፣ የህወሃትን የበላይነት ለማረቅ፣ እውነተኛ ተቃውሚዎች እንዲሳተፉ፣ ዴሞክራሲ ሰላም እርቅ ለማምጣት አይደለም:: የታቀደው ውጤት ሁለት ፈርጆች ያሉት ይመስለኛል::

1 የህዝብን ቀልብ ለመሳብ እና የተነሳውን አመፅ ለማለሳለስ እና በኮማንድ ፖስቱ የሚካሄዱቱን ግድያዎች፣ አስር፣ ከስራ ማባረር ወዘተ ለመሸፍን ነው:: የህወሓት እምነት ታሪካዊ ጠላቶቻችንመነሳታቸው አይቀሬ ነው ይህንን ለመግታት የኃይል ተቁአማትን ሙሉበሙሉ መቆጣጠር ሲነሱም በኃይል መጨፍለቅ ነው:: በኮማንድ ፖስቱ ይህ ሲደረግ ከተቃዋሚዎች ጋር ድራማ መስራት ሕዝባዊ ትኩረቱን ይቀይርናል ነው::

2 ከውጭ መንግሥታት ሊደርስባቸው የሚችለውን ጫና መቀነስ ነው:: የውጭ መንግሥታት ለህወሓት ያላቸው ድጋፍ መሰረቱ ጥንካሬ ማሳየት ነው:: ጥንካሬ ካሳዩ በተለያዩይ አገሮች የሚያካራዩትን ጦር መቀጠል እንደሚችሉ ያስረግጣሉ:: አሜሪካ አውሮፓ ደግሞ ብሔራዊ ጥቅማቸው የኢትዮጵያዊና ነፃነት ሳይሆን የአካባቢው ሰላም ነው:: ስለዚህ የህወሓት ጠንካራ መስሎ መቅረብ ትልቁ የገንዘብ የዲፕሎማሲ የፖለቲካ ድጋፍ መሰርት ነው:: በሌላ አባባባል ህወሃትን ባዳከምን መጠን የህወሓት ሰረዊት በሀገር ውስጥ እንቅስቃሴ ተወጥሮ የምዕራባውያንን ስራ ለመስራት ባልቻለ ግዜ የውጭ አገሮች ድጋፍ ይሟጣጠል::

ህወሓት ይህን ያውቃል፣ ህይለማርያም ወይንም ወርቅነህ ወይንም ደመቀ አላልኩም:: ያልኩት አባይ ስብሐት አረከብ በረከት ማለቴ ነው::

ከዚህ ጋር የተያያዘ ሌላው ጥያቄ መድረክ እና ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲዎች ምን አቁማ ይወስዳሉ ነው:: የድራማው አካል ይሆናሉ? ከሆኑስ ስትራቴጂያቸው ምንድነው? ለሕዝቡስ ያቀርቡታል?

አንድ ነገር ግልፅ ነው የህወሓት ምንም አይነት ድራማ ስርዓቱን አያድነውም:: ህወሓት በሰላም ስላጣን አይለቅም:: ጎንደር ጎጃም አርሲ ኮንሶ ጋምቤላ ያለው አመፅ በታማኝ ተቃዋሚዎች ትያትር አይገታም:: መነሻችን ይህ ከሆነ የድራማውን ሂደት ከተወጠነለት የህወሓት ብልጣብልጥነት አግጣጫ ወደ ትግል መሣሪያነት መለወጥ የግድ ነው:

 

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: