በማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ለመፍጠር የሚረዱ ነጥቦች by Dr Tadesse Biru Kersmo

1. ቀጣይነት
ጽሁፎችን በቋሚነት በተከታታይ ማውጣት ያስፈልጋል። እንደመስቀል ወፍ አልፎ አልፎ ብቻ ብቅ የሚሉ ጽሁፎች ትኩረት ላይስቡ ይችላሉ። ሆኖም ግን ሁሌ በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ብቻ መሟዘዝ አንባቢዎችን ያሰለቻል።
2. ትዕግሥት
እርግጥ ነው ማኅበራዊ ሚዲያ ፈጣን ነው፤ ሆኖም ግን እንደገባህ የፈረስህን ልጓም ለቀህ ሽምጥ የምትጋልብበት ሜዳ መስሎ ቢሰማህ መልካም አይደለም። የሚታዘቡህ ሰዎች አሉ። ስምህ ለውጠህ፤ ጭንብል አጥልቀህ መግባትህ የተለየ ነፃነት የሚሰጥህ ከመሰለህ የምታታልለው ራስህን ነው። በማኅበራዊ ሚዲያ አማካይነት የሰዎችን አስተሳሰብ አንተ/አንቺ ትክክለኛ ነው ብለህ ወደ ምታምንበት አቅጣጫ የመለወጥ ዓላማ ያለህ/ሽ ከሆነ እንደማንኛውም የአመራር ሥራ ጊዜና ትዕግስት ይጠይቃል።
3. ቋንቋ
ማኅበራዊ ሚዲያዎች የየራሳቸው ቋንቋ አላቸው። በፌስ ቡክ ላይ የምንጽፍበት የአፃፃፍ ዘይቤ ለቲውተር ወይም ለሊንክድኢን አይሆንም። ምስሎችንም ዩቱብ እና ኢንስታግራም ላይ በተመሳሳይ መንገድ አንጠቀምም። የዋትስአፕ፣ የቫይበርና የኢሞ ቡድኖችም ቢሆንም የየራሳቸው ባህል አላቸው። በማኅበራዊ ሚዲያ የምንጽፈው ሌሎች ሰዎች እንዲያነቡት እንጂ ለራሳችን አይደለም፤ ይህንን የምንቀበል ከሆነ ደግሞ የቋንቁ አጠቃቀማችን አንባቢዎቻችንን የሚመጥን መሆን አለበት።
4. ማንበብ
በአንድ ጽሁፍ ላይ ሀሳብ ከመስጠትህ በፊት በደንብ አንብበው፤ መልዕክቱን ለመረዳት ሞክር። ከቀረበው ሀሳብ ጋር ተያያዥነት የሌለው ሀሳብ ብትሰጥ ራስህን ግምት ውስጥ ትጥላለህ። ለምትተቻቸው ሰዎችም ጭምር አክብሮት ይኑርህ/ሽ። ማኅበራዊ ሚዲያን ደጋፊዎች መሰብሰቢያ፣ ወዳጆችን ማፍሪያ ቦታ እና ከተፃፃሪ ሀሳቦች መብለጫ ቦታ እንጂ ትርጉም የለሽ ቃላት መወርወሪያ ቦታ አታድርግ።
5. መማር
ተማር፤ ሁሌ ተማር። ቁም ነገሮችን በቀልድና በለሰለሰ መንፈስ ማቅረብን ልመድ።

Image result for tadesse biru

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: