የኢትዮ ቴሌኮም ምክትል ስራ አስኪያጅ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ

የኢትዮ ቴሌኮም ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የኩባንያው የሶርሲንግ እና ፋሲሊቲ ዲቪዥን ሀላፊ አቶ አብርሃም ጓዴ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

አቶ አብርሃም ጓዴ ከከረዩ ቱር ኤንድ ትራቭል ስራ አስኪያጅ ጋር በመመሳጠር ኢትዮ ቴሌኮም ከፈፀመው የውል ስምምነት ውጪ የምርት ዘመናቸው ከአውሮፓውያኑ 2000 ዓመተ ምህረት እና ከዚያ በኋላ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ለኢትዮ ቴሌኮም መቅረብ ሲገባቸው ከአውሮፓውያኑ 2000 ዓመተ ምህረት በፊት የሆኑ ተሽከርካሪዎች መሆናቸውን እያወቁ የተሽከርካሪዎቹን ምርመራ ከሚያደርገው ድርጅት ጋርም በመመሳጠር ምርመራውን እንዲያልፉ በማድረግ በመንግስት ላይ ኪሳራ እንዲደርስ በማድረግ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ፖሊስ በዚህ መንገድ ኢትዮ ቴሌኮም 67 ተሽከርካሪዎችን እንደተከራየ ቢገልፅም በመንግስት ላይ የደረሰውን ኪሳራ መጠን አላስቀመጠም።

ተጠርጣሪው ታህሳስ 18 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት በቁጥጥር ስር ውለው በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ሁለተኛ የወንጀል ችሎት ዛሬ ቀርበዋል።

የተጠርጣሪው ጠበቃ መርማሪ ፖሊስ ምርመራውን በማጠናቀቁ በዋስትና ሊለቀቁ ይገባል ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ ምርመራየን ስላላጠናቀኩኝ ቢለቀቁ ሰነድ ሊሰወርብኝ ይችላል በሚል ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄውን እንዳይቀበል ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱም የሁለቱን ክርክር ካደመጠ በኋላም ብይን ለመስጠት ለፊታችን ሰኞ ጥር 8 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት ቀጠሮ ሰጥቷል።

Image result for ethio telecom

 

 

 

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: